ወንጀለኛ የህወሃት ጀሌዎችን በህግ ለመፋረድ ድጋፍዎን ይስጡ

ወንጀለኛ የህወሃት ጀሌዎችን በህግ ለመፋረድ ድጋፍዎን ይስጡ
ኢትዮጵያዊያን በሀገራቸው ጭቆና፣ አድልኦ፣ ግፍና በደል አንገሽግሿቸው ተሰደው በሚኖሩበት ምድር ሁሉ ክብራቸውና ነጻነታቸው ተጠብቆ
መኖር እንደሚገባቸው ፈጽሞ አጠያያቂ አይደለም። የህግ ልእልና በሰፈነባቸው አገሮችም ይህንን መሰረታው መብት ለማስጠበቅ ከህግ በላይ
ምንም ሀይልና ጉልበት ያለው መሰሪያ የለም።
ህወሃት መራሹ የኢትዮጵያ መንግስት “አሰረን አሳደደን” በማለት በአውሮፓና በአሜሪካ የፖለቲካ ጥገኝነት በመጠየቅ
በስደተኛ ስም በተለያየ የማምታቻ ሽፋን ተደብቀው ኢትዮጵያዊያን ያለስጋት የነጻነት አየር እየተነፈሱ እንዳይኖሩ
ለማድረግ የሚጥሩ ሰላዮችና የጨቋኙ ስርአት አቀንቃኞች መኖራቸው በተለያየ ጊዜ የተረጋገጠ ሃቅ ነው።
ምንም እንዃን በርካታ ኢትዮጵያዊያን በተደጋጋሚ የነዚህ ወንጀለኛና አሸባሪ ግለሰቦች ሰለባ ቢሆኑም
እስካሁን ጠንካራ ህጋዊ እርምጃ እንዲወሰድባቸው በቂ ጥረት አልተደረገም።
ባለፈው ግንቦት 10 2004 (May 18, 2012) ጋዜጠኛ እና የሰብአዊ መብት ተሟጋች የሆነው አበበ ገላው
የቀድሞው አንባገነን መለስ ዜናዊን ወንጀሎች በአለም መሪዎች ፊት ስላወገዘ እና ስላጋለጠ እንዲሁም የታፈነ
የኢትዮጵያን ህዝብ የነጻነት ጩኸት ስላሰማ በተለያዩ የህወሃት ጀሌዎች የሽብር ፈጠራ ወንጀል ሰለባ ሆኗል።
በቅርቡ ከነዚህ በህገወጥ የወንጀልና የስለላ ተግባር ከተሰማሩ የህወሃት ጀሌዎች መሃል ጥቂቶቹን ያጋለጠው ጋዜጠኛ አበበ ገላው፣ ጠበቃ ይዞ
በህግ ለመፋረድ እንቅስቃሴ ጀምሯል።
ይሄንኑ አላማ ለማሳካት እና ወያኔዎች የፈጠሩትን የጸጥታ ስጋት አቅም በፈቀደ መንገድ ለመቅረፍ ጥቂት የECAD የፓልቶክ መድረክ አባላት
በራሳቸው አነሳሽነት ባዋጡት ገንዘብ ለዚሁ አላማ ማስፈጸሚያ የሚሆን ልዩ የባንክ ሂሳብ ተከፍቷል::
ነጻነትና የህግ ልእልና በሰፈነባቸው አገሮች ከህግ በላይ ወንጀለኞችን የመፋለሚያ መሳሪያ ባለመኖሩ፣ ጉዳዩ ይመለከተናል የሚሉ ኢትዮጵያዊያን
ሁሉ የገንዘብ ድጋፍ በማድረግ ይህንን ጥረት አቅማቸው የፈቀደላቸውን ያህል እንዲያግዙ ወገናዊ ጥሪ ቀርቧል።
ህግን ተጠቅሞ ህገወጦችን መፋረድ አንድ የትግል ስልት በመሆኑ ለአንድ ሰው ብቻ የሚተው ጉዳይ አለመሆኑ ለማንም ግልጽ ነው። እርስዎም
ለዚሁ እንቅስቃሴ የገንዘብ ድጋፍ ማድረግ አስፈላጊነቱን ካመኑበት ከታች ከተዘረዘሩት አማራጮች በአንዱ መንገድ አስተዋጽኦ ማድረግ
ይችላሉ:::
1/ በማንኛውም አሜሪካ በሚገኝ የWells Fargo ቅርንጫፍ AG Legal Fund, Acc. No. 3525090746 በቀጥታ ገንዘብ ማስገባት
ይቻላል።
2/ አሜሪካ በሚገኝ ማንኛው Bank of America ቅርንጫፍ በኩል በቀጥታ ገንዘብ ማስገባት ይቻላል:
AG Legal Fund, Acc. No. 485010192701
3/ ከሌሎች አሜሪካ የሚገኙ ማንኛውም ባንኮች ለማስተላለፍ (wire) ለማድረግ AG Legal Fund, Acc. No. 485010192701 , ABA
121000248 መጠቀም ይቻላል::
4/ ከአሜሪካ ውጭ ከሚገኙ ባንኮች ገንዘብ ወደ AG Legal Fund ለማስተላለፍ Acc. No. 3525090746 SWIFT- WFBIUS6S
መጠቀም ይቻላል::
5/ በኢንተርኔት አማካኝነት በ Paypal አስትዋጾ ማድረግ ከፈለጉ ከታች ያለውን ድር (link) በመጫን አስተዋጾ ማድረግ ይችላሉ።
https://www.paypal.com/cgi-bin/webscr?cmd=_s-xclick&hosted_button_id=UHPF5RPB2PBSN
6/ ከዚህም በተጨማሪ በWestern Union ከላይ በተጠቀሱት የባንክ ሂሳቦች በአንዱ አማካኝነት ገንዘብ ማስተላለፍ ይችላሉ።
ስለጉዳይ ተጨማሪ መረጃ ከፈለጉ በስልክ ቁ. (001) 5718829882 በመደወል ወይንም በ ethlegalfund@gmail.com ኢሜይል ማድረግ ይችላሉ።
እናመሰግናለን!!