በላይ ዘለቀ ከስብሐት ገብረ እግዚአብሔር-(የካቲት መጽሔት፣ 3ኛ ዓመት ቁጥር 7፣ ሀምሌ 1972)

© አፈንዲ ሙተቂ

በላይ ዘለቀ
ከስብሐት ገብረ እግዚአብሔር
(የካቲት መጽሔት፣ 3ኛ ዓመት ቁጥር 7፣ ሀምሌ 1972)

----------------------------------------
ማስታወሻ፡- ከታች እንደምታነቡት ጋሽ ስብሐት በዚህ ጽሁፍ ውስጥ “በላይ ዘለቀ ፎቶ ተነስቶ አያውቅም” የሚል ነገር አስፍሮ ነበር። ይህም የሆነው ታሪኩን ለስብሐት የነገሩት ሰዎች በወቅቱ በላይ ፎቶ መነሳቱን መረጃው ስላልነበራቸው ነው። ይሁንና እዚህ የምትመለከቱት ፎቶ የበላይ ዘለቀ መሆኑ በብዙ ምንጮች ተረጋግጧል። ታዲያ ይህ ፎቶግራፍ በጽሑፉ ውስጥ ስለበላይ ዘለቀ ቁመና ከተነገረው ገለጻ ጋር አንድ ዓይነት መሆኑ በጣም አስደንቆኛል (ጽሑፉ በታተመበት ወቅት የበላይ ቁመና በስዕል ነበር የተገለጸው)።
እኔ ይህንን ጽሁፍ ለመጀመሪያ ጊዜ ያነበብኩት በነሐሴ ወር 1982 ነው። ጸሑፉ የበላይ ዘለቀ እውነተኛ ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ ይፋ የወጣበት በመሆኑ ለረጅም ጊዜ ስፈልገው ነበር። በቅርቡ በኢንተርኔት ላይ ተጭኖ ሳገኘው አስደሰተኝና ለናንተ ላካፍላችሁ ወሰንኩ። መልካም ንባብ!
አፈንዲ ሙተቂ
----------------------------------------
ፊታውራሪ ተሻለ አለሙ የ74 አመት አዛውንት ናቸው ::"እኔና በላይ ዘለቀ የወንድማማች ልጆች ነን "አሉኝ ::"በእድሜ 4 አመት እበልጠዋለሁ ::" እንግዲህ ደጃዝማች በላይ ዘለቀ ይኼን ጊዜ 70 አመታቸው ነበር ማለት ነው :: ፊታውራሪ ተሰማ ላቀው 67 አመታቸው ነው :: "የበላይ ዘለቀ ያባቱ ትንሽ ወንድም ነኝ” አሉኝ :: ፊታውራሪ ቀለመወርቅ መዝጊያ 62 አመታቸው ነው ::የደጃዝማች በላይ ዘለቀ ዋና ጸሀፊ ነበሩ ::የሚከተለውን ታሪክ የነገሩኝ እነዚህ 3 አዛውንቶች ናቸው ::

በላይ ዘለቀና ወንድሞቹ

ዘለቀ ላቀው (የበላይ ዘለቀ አባት ) የልጅ እያሱ አንጋች ነበሩ ። ልጅ እያሱ ሲገለበጡ ዘለቀ ላቀው ወደ ሚስታቸው አገር ወደ ጫቀታ ሄደው ልጆቻቸውን ይዘው ወደ አገራቸው ወደ ለምጨን (ቢቸና ወረዳ ) ተሻገሩ ። (ቢቸና ጎጃም ውስጥ ጫቀታ ወሎ ውስጥ ከአባይ ወንዝ ማዶ ለማዶ ናቸው ። ይገበያያሉ ፡ ይጋባሉም። )

በ1916 አ.ም. ማለት በላይ ዘለቀ የ14 አመት ልጅ ሳለ ፊታውራሪ እምቢ አለ የተባለ የራስ ሀይሉ ሌባ አዳኝ (ጸጥታ አስከባሪ) ዘለቀ ላቀውን ከበባቸው። ዘለቀ ላቀው እጄን አልሰጥም ስላሉ ተኩስ ተከፈተ። ዘለቀ ላቀውና አብረዋቸው የነበረ አለሙ መርሻ የተባሉ ወንድማቸው ከአስር ሰው በላይ ገድለው ብዙ ሰው አቆሰሉ።

«እኛ ልጆች ተኩስ ካባራ በኋላ ተየጫካው ስንመለስ ሁለቱም ሞተዋል። የዘለቀ ላቀው ሬሳ እቤቱ በራፍ ላይ ተሰቅሎዋል» አሉ ፊታውራሪ ተሻለ አለሙ ። እንግዲህ በላይ ዘለቀና ተሻለ አለሙ እኩል አባቶቻቸውን አጡ። አብረው የሀዘንን ጽዋ ቀመሱ ፡ እኩል በቀልን እያሰላሰሉ አደጉ ፡ በሁዋላም አብረው ጠላትን ተዋጉ ።
ዘለቀ ላቀው ሲሞቱ ልጆቻቸው ወደ እናታቸው አገር ወደ ጫቀታ ተመለሱ። በላይ ዘለቀ ያባቱን ደም ለመመለስ ተኩስ እየተማረ አደገ። አደገና ያባቱን «ናስ ማሰር» (ባለ ነሐስ ማሰርያ ) ውጅግራ ጠመንጃ ይዞ ወደ አባቱ አገር ወደ ለምጨን (ቢቸና) ተሻገረ ።

አባቶቻቸው የተገደሉባቸው ጎረምሶች ዳኝነት እንዳይሹ ዳኛው ራስ ሀይሉ ሆኑባቸው። የቀራቸው ምርጫ በቀል ነው ።
መሳርያ እየገዙ እየተዘጋጁ ለምጨን ቀንጦ ማርያም እያረሱ ፡ ቀን ይጠብቁ ጀመር።
እንዲህ ሲል ጥልያን መጣ ...በሚያዝያ 28 ቀን (1928 አ.ም.) ለቀኛዝማች መሸሻ ጥልያን መሳርያ በአየር አወረደላቸው። (ለጥልያን ገቡ ) ካለው ሰበካ ያዙ። በረንታ ወረዳ (ቢቸና አውራጃ ) ደረሱ። የዱሀ ከተማ ሰፍረው ህዝቡን መሳርያ እየነጠቁ (ጥልያንን እንዳይወጋ ) ጥልያን ደግ መንግስት ነውና እንገዛለን እያሉ ይሰብካሉ (እንዲሾማቸው)።

«ልጅ በላይ ዘለቀ ግን እዋጋለሁ እንዋጋ እያለ እኛን ወንድሞቹን አነሳሳን» አሉ ፊታውራሪ ተሻለ አለሙ «ቀሰቀሰን ከሰላሳ እስከ ሀምሳ የምንደርስ ያንድ አያት ልጆች ...የገልገል ቂልጡ ልጆች ...ታጥቀን ተነሳን። ከቀኛዝማች በላይ መሸሻ ሰዎች መሳርያ እየነጠቅን በረሀ ገባን ።»

«ጦር ሲያሳድደን ...ስንሸሽ ...ቤት ሲያቃጥልብን ... ከሁዋላው ወይም ከጎኑ በድንገት እየመታነው መሳርያ ነጥቀን ስናመልጥ .....እንዲህ ስንል አንድ ቀን የማናልፈው ጉዳይ መጣ። ግንባር መግጠም ግድ ሆነ ። ጠላት መሸሻ አሳጣና ።»
«የዛሬን ጦር ማን ይምራው ?» አለን ልጅ በላይ
«አንተን መርጠናል ...እስከ መጨረሻው» አልነው።
"ሁላችሁም ወንድማማች ናችሁ ።" አልኳቸው ፊታውራሪ ተሻለን "በላይ ዘለቀን እርስዎ እንኩዋን በ4 አመት እበልጠዋለሁ ብለዋል ። እንግዲያው በምኑ ነው አለቃችሁ እንዲሆን የመረጣችሁት ?"
"እንዴ ! በደግነቱ ፡ በጀግንነቱ ! ጠባየ መልካም በመሆኑ ! እኔ ይቅርብኝ ብሎ ለሌላው ስለሚያዝን !" (ያን ጊዜ ፡ 1928 አ.ም. ልጅ በላይ 3 ወልደዋል ። ልጅ ተሻለ ግን ገና በታህሳስ ነው ያገቡት)።

ወይዘሮ ድንቅነሽ ሀይሉ (የራስ ሀይሉ ልጅ ) ጥልያን ሾመዋቸው የለምጨን ጉልተ ገዥ ሆነው ሄዱ። ህዝቡን መሳርያ አግባ ብለው አሰባሰቡ። በላይ ዘለቀና ወንድሞቹ በድንገት ገብተው መሳርያዎቹን ነጥቀው ሴትየዋን ሳይጎዱ ሳያጎሳቁሉ ወደ መጡበት መልሰው ላኩዋቸው ። የነጠቁዋቸውን መሳርያ 35 ያህል ጠመንጃ ዋሻ ደበቁት። ለራሳቸው በቂ መሳርያ ይዘዋላ።
ከዚህ በሁዋላ ደብረ ማርቆስን ጥልያን እየያዘ በላይ ዘለቀን ያሳድነው ጀመር ። ከ1928 አ.ም. ሚያዝያ እስከ ግንቦት 29 ቀን ድረስ ሁኔታው ተመሳሳይና ተደጋጋሚ ነበር። ጦር ይመጣል ...ያስሳል .....እነ በላይ ዘለቀ ይሸሻሉ ...በሁዋላ ቀስ ብለው መጥተው ጥቂቱን ገድለው መሳርያ ነጥቀው ....እልም ! መሳርያ በየዋሸው ያከማቻሉ።
እንደዚህ ብዙ አሰሳ ተሞከረ። ባንዱ አሰሳ የበላይ ዘለቀ ቤትና የለምጨን ቤቶች በሙሉ ተቃጠሉ። ከብቱም ተዘረፈ ። ጠላት ለምጨን 3 ጊዜ ነው ያቃጠለው።

"እስከ ታህሳስ 29 ቀን ድረስ አሰሳው የሚካሄደው በባንዳ ነበር ።" በታህሳስ 8 ቀን 1929 ግብጣን ደበቡ የተባለ ጥልያን ቢቸና ገባ ቢሉን ከዲማ ገስግሰን ቢቸና አደጋ ልንጥል ስንል ካህናት ጽላት ይዘው ስእል መስቀል ይዘው "አገሩንና ታቦቱን ያቃጥልብናልና አትውጉት ። እሱን እኛ ተመለስ እንለዋለን ።" ብለው መለሱን ። ግብጣን ደበቡም በላይ ዘለቀ መጣብህ ቢሉት ወደማርቆስ ተመለሰ ።"

በየካቲት 29 ጥልያን አገሩን አስነስቶ ወረረን ። ከያውራጃው ግብጣን ደበቡ አስከተተ ። ጦር ሲመጣባቸው እነ በላይ ዘለቀ ሸሹ ። አጥቷቸው ሲመለሱ እያደፈጠ በጎን አደጋ እየጣሉ ብዙ መሳርያ ነጠቁት ።
"የግንቦት እርገት ለት ..በ29 ነበር የዋለ ..ጥልያን ራሱ መጣ" የበላይ ዘለቀን ዘመዶች ከለምጨን እየደበደቡ ወደ አርበኞቹ እንዲመሩዋቸው አስገደዱዋቸው ። "ጦሩ ሲመጣ አሳለፍነው ። ከጎን አደጋ ጣልንበት ። በላይ ዘለቀ አንዱን ትሊንቲ ገደለው ኩረኔሉን አቆሰለው ። ብዙ ባንዳዎች ሞቱ ።"

ታስሮ እየተደበደበ ሲመራ የነበረው አዛዥ ቢያዝን ዱብዳ የተባለው የበላይ ዘለቀ ዘመድም ቆሰለ ።
በሰኔ 29 (1929) ጠላት በቅምቧት በደጀን በገበያ በሽበል በበረንታ የነበረውን "ደንበኛ " በሙሉ አከተተው ። (ደንበኛ የሚባለው "የመንግስት " የደንብ ብረት የያዘ ነፍጠኛ ነው ) ቀኛዝማች ስማ ነገዎ አዝማች ሆኖ ይህን ሁሉ አስከትቶ አባይ ወረደና አባራ ጂወርጂስ ሰፈረ ። ሀሳቡ እነ በላይ ዘለቀ ወደ ጫቀታ እንዳይሻገሩ በር በሩን ለመዝጋት ነበር ።
"እንውጋው " አለ በላይ ዘለቀ

"ጦሩ በጣም ብዙ ነው አንችለውም " አሉት ሌሎቹ። "ግድ የለም ።ጦሩ በየመንደሩ ይመራል ። አዝማቹ ላይ አደጋ እንጣልበት ።"
እነ በላይ ዘለቀ ፡ ቀኛዝማች ለማ ነገዎ ያደረበትን በለሊት ከበቡት ። ሲነጋ ለማ ነገኦን ከነወንድሞቹ ደመሰሱት ። ጦሩ በሙሉ እጁን ሰጠ ። መሳሪያውንና በቅሎውን ሁሉ አስረከበ ። ድል አድራጊዎቹ መሳርያውን ዋሻ ውስጥ ደበቁት ። በቅሎዎቹን ወደ ጫቀታ ልከው በጥይት ለወጡዋቸው ።" ይሄ የሆነው ሰኔ 10 ነበር። ሰኔ 12 በአውሮፕላን ይደበድቡን ጀመር ። በረንታ ጎይ ጂወርጂስ ላይ 12 ሰው ሞተብን ። እኛም ተመልሰን ወደ በረሀችን ሸሸን ።" ፊታውራሪ ለማ ሞገስ የጣልያን የጦር እንደራሴ ሆኖ ከማርቆስ ተልኮ ወጥቶ ዲማ አጠገብ ገድ ወንዝ ዋሻ ውስጥ እንዳለ ከበባቸው ። ወጥተው ገጠሙ ። ድል ነሱት ።
ብዙ ሰው ሞተበት ። እሱ ግን አመለጠ ።
በላይ ዘለቀ 60 ያህል ምንሽርና አልቤን ማረከ ። ምንሽርና አልቤን ሲያገኙ የመጀመርያ ጊዜያቸው ነበር ። እስካሁን ግን ሲዋጉ በናስማስር ፡ በውጅግራ ፡ በለበን ብቻ ነበር ።
"ድፍን ሀምሌን ተከበብን ። ለምጨን አንድ ዋሻ ገብተን ተደበቅን ። እኛን ሲያጣን ጊዜ የጎይ ጂወርጂስና ያካባቢውን ህዝብ ጎይ ላይ ሰብስቦ በላይ ዘለቀን ካላመጣችሁ ብሎ በመትረየስ ፈጃቸው ።" በላይ ዘለቀ የቶክሱ እለት ሞቶ ተቀብሯል ተብሎ ለጥልያኖች ተነገራቸው። ሰው ሰደው መቃብሩን ቢያስመረምሩት ሴት ሆና ተገኘች ።
አንዱ አሳባቂ በላይ ዘለቀ ወደ እነብሰ አውራጃ ነው የሄደው ብሎ ለጥልያኖች ጠቆማቸው ። የጥልያን ጦር ወደ እነብሴ ዘመተ። የእነብሴና የጎንቻ ህዝብ ገጠመውና ጨረሰው ። አንድ ጥልያን ብቻ አመለጠ ።

በላይ ዘለቀና አገሬው
እስከ ነሀሴ 1929 ድረስ የበላይ ዘለቀ ተከታዮች ከ30 እስከ 50 የሚደርሱ ወንድሞቹ ብቻ ነበሩ ።
"ነሀሴ ጂወርጂስ በላይ ዘለቀ በረንታ ላይ አዋጅ አስነገረ። እኛን ምሰሉ ፡ እርዱን ። አለዚያ ግን ይህ የጦር ሜዳ ነውና እንዳትጎዱ ሂዱ ልቀቁ።"
"እናርጅ እናውጋ (የደብረወርቅ ወረዳ ) በረንታና ሸበል፡ ጉበያ (ደጀን አጠገብ ) እነማይ (ቢቸና አውራጃ ) ...ይሄ ሁሉ አመነ ፡ ተባበረን።
"ከህዳር ማርያም (1930) እስከ መጋቢት ውድማትን ፡ አዋባልን ፡ ቅምብዋትን ፡ ሊበንን ፡ ባስን ፡ አነድድን ደጀንን ...እነዚህን ያዝን ።"
"በየካቲት ትሊንቲ ከጫቀታ ዘመተብን አባይ ደረሰ ። አገድነው ። ብዙ ውጊያ ተደረገ ። 80 ብረት (ከነሰው ) ማረክን ። መለስነው ። ወደ ደጀን ተመለስን ።"
"ከሸዋ ሲዘምትብን አባይ ላይ አገድነው። ወር ካስራምስት ቀን ተዋጋነው። 3 መኪናዎች ሰበርን ። ውስጣቸው የነበሩ ጥልያኖች ሞቱ ።

"ጥልያን ሀይሉን አጠናክሮ በደጀን በኩል ከሸዋ መጣብን ። 12 በጦለኔ በጀኔራል ማሊን አዝማችነት መጣ ።
"መጋቢት 19 ቀን (1930) ውጊያው ማለዳ የጀመረ በአስራ አንድ ተኩል አበቃ ። መትረየስና መድፍ ከታች ፈረሰኛ በሻምላ (በጎራዴ ) " ተጨምሮበት ከላይ አሮብላ። ወንድሞቻችን አለቁ ። የጦር አዝማች የነበረው የበላይ ዘለቀ ወንድም ደጃዝማች ታደለ ላወቅ ወደቀ ። ተሰማ ላቀው ቆስሎ አመለጠ ። 300 ያህል አለቅን ። የተቀረውን ጨለማ ገላገለን ።
"ጠላት ፆን ማርቆስ ገባ ::እኛ ወደ በረሀችን ገባን ::"
"ሚያዝያ 4 (1930) እበረሀችን አፋፍ ላይ እንደ ሰፈርን ጠላት ባራት ረድፍ ቢቸና ገባ። ሚያዝያ 6 ጦሩን ባራት ማእዘን አቀነባብሮ በረሀችንን በሙሉ ከበበው ። በመካከሉ ደግሞ በግንባር እልፍ አእላፋት ጦር ይዞ ተሰለፈ ።"
"ባለው ሀይላችን ገጠምነው ።"
"ሊያፍነን ሞከረ በብዛቱ ።"
"የቆላ ጫካ ነው ....እሳት ለቀቅንበት "
"ይገርማል እኮ የቀን ነገር !ነፋሱ እሳቱን እያንቦገቦገ ወደነሱ ወሰደው ። ብዙዎቹን እሳት በላቸው ። ብዙዎቹ አመለጡ ። "የበላይ ዘለቀ ሚስት ወይዘሮ ሸክሚቱ አለማየሁ በመትረየስ ሞቱ (እንደ ወንድ ለብሰው ነበር ) ልጅ የሻሸወርቅ በላይ ተማረከች ። የናትየዋ እናትም ተማረከች ። "ከዚህ በሁዋላ አባይን ተሻግረን ጫቀታ ገባን ። ያጌ ከተማ ግዛው ሰብስቤ የተባለው የጥልያን እንደራሴ ገድለን አገሩን አቃጥለን የጎበዝ አለቃ ሾመን ... ፊታውራሪንና ቀኛዝማች እያሱ ልጅ በላይ ሾመው ...ተመልሰን ወደ ለምጨን በረሀ ገባን ።"
© አፈንዲ ሙተቂ

በላይ ዘለቀ
ከስብሐት ገብረ እግዚአብሔር
(የካቲት መጽሔት፣ 3ኛ ዓመት ቁጥር 7፣ ሀምሌ 1972)

—————————————-
ማስታወሻ፡- ከታች እንደምታነቡት ጋሽ ስብሐት በዚህ ጽሁፍ ውስጥ “በላይ ዘለቀ ፎቶ ተነስቶ አያውቅም” የሚል ነገር አስፍሮ ነበር። ይህም የሆነው ታሪኩን ለስብሐት የነገሩት ሰዎች በወቅቱ በላይ ፎቶ መነሳቱን መረጃው ስላልነበራቸው ነው። ይሁንና እዚህ የምትመለከቱት ፎቶ የበላይ ዘለቀ መሆኑ በብዙ ምንጮች ተረጋግጧል። ታዲያ ይህ ፎቶግራፍ በጽሑፉ ውስጥ ስለበላይ ዘለቀ ቁመና ከተነገረው ገለጻ ጋር አንድ ዓይነት መሆኑ በጣም አስደንቆኛል (ጽሑፉ በታተመበት ወቅት የበላይ ቁመና በስዕል ነበር የተገለጸው)።
እኔ ይህንን ጽሁፍ ለመጀመሪያ ጊዜ ያነበብኩት በነሐሴ ወር 1982 ነው። ጸሑፉ የበላይ ዘለቀ እውነተኛ ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ ይፋ የወጣበት በመሆኑ ለረጅም ጊዜ ስፈልገው ነበር። በቅርቡ በኢንተርኔት ላይ ተጭኖ ሳገኘው አስደሰተኝና ለናንተ ላካፍላችሁ ወሰንኩ። መልካም ንባብ!
አፈንዲ ሙተቂ
—————————————-
ፊታውራሪ ተሻለ አለሙ የ74 አመት አዛውንት ናቸው ::”እኔና በላይ ዘለቀ የወንድማማች ልጆች ነን “አሉኝ ::”በእድሜ 4 አመት እበልጠዋለሁ ::” እንግዲህ ደጃዝማች በላይ ዘለቀ ይኼን ጊዜ 70 አመታቸው ነበር ማለት ነው :: ፊታውራሪ ተሰማ ላቀው 67 አመታቸው ነው :: “የበላይ ዘለቀ ያባቱ ትንሽ ወንድም ነኝ” አሉኝ :: ፊታውራሪ ቀለመወርቅ መዝጊያ 62 አመታቸው ነው ::የደጃዝማች በላይ ዘለቀ ዋና ጸሀፊ ነበሩ ::የሚከተለውን ታሪክ የነገሩኝ እነዚህ 3 አዛውንቶች ናቸው ::

በላይ ዘለቀና ወንድሞቹ

ዘለቀ ላቀው (የበላይ ዘለቀ አባት ) የልጅ እያሱ አንጋች ነበሩ ። ልጅ እያሱ ሲገለበጡ ዘለቀ ላቀው ወደ ሚስታቸው አገር ወደ ጫቀታ ሄደው ልጆቻቸውን ይዘው ወደ አገራቸው ወደ ለምጨን (ቢቸና ወረዳ ) ተሻገሩ ። (ቢቸና ጎጃም ውስጥ ጫቀታ ወሎ ውስጥ ከአባይ ወንዝ ማዶ ለማዶ ናቸው ። ይገበያያሉ ፡ ይጋባሉም። )

በ1916 አ.ም. ማለት በላይ ዘለቀ የ14 አመት ልጅ ሳለ ፊታውራሪ እምቢ አለ የተባለ የራስ ሀይሉ ሌባ አዳኝ (ጸጥታ አስከባሪ) ዘለቀ ላቀውን ከበባቸው። ዘለቀ ላቀው እጄን አልሰጥም ስላሉ ተኩስ ተከፈተ። ዘለቀ ላቀውና አብረዋቸው የነበረ አለሙ መርሻ የተባሉ ወንድማቸው ከአስር ሰው በላይ ገድለው ብዙ ሰው አቆሰሉ።

«እኛ ልጆች ተኩስ ካባራ በኋላ ተየጫካው ስንመለስ ሁለቱም ሞተዋል። የዘለቀ ላቀው ሬሳ እቤቱ በራፍ ላይ ተሰቅሎዋል» አሉ ፊታውራሪ ተሻለ አለሙ ። እንግዲህ በላይ ዘለቀና ተሻለ አለሙ እኩል አባቶቻቸውን አጡ። አብረው የሀዘንን ጽዋ ቀመሱ ፡ እኩል በቀልን እያሰላሰሉ አደጉ ፡ በሁዋላም አብረው ጠላትን ተዋጉ ።
ዘለቀ ላቀው ሲሞቱ ልጆቻቸው ወደ እናታቸው አገር ወደ ጫቀታ ተመለሱ። በላይ ዘለቀ ያባቱን ደም ለመመለስ ተኩስ እየተማረ አደገ። አደገና ያባቱን «ናስ ማሰር» (ባለ ነሐስ ማሰርያ ) ውጅግራ ጠመንጃ ይዞ ወደ አባቱ አገር ወደ ለምጨን (ቢቸና) ተሻገረ ።

አባቶቻቸው የተገደሉባቸው ጎረምሶች ዳኝነት እንዳይሹ ዳኛው ራስ ሀይሉ ሆኑባቸው። የቀራቸው ምርጫ በቀል ነው ።
መሳርያ እየገዙ እየተዘጋጁ ለምጨን ቀንጦ ማርያም እያረሱ ፡ ቀን ይጠብቁ ጀመር።
እንዲህ ሲል ጥልያን መጣ …በሚያዝያ 28 ቀን (1928 አ.ም.) ለቀኛዝማች መሸሻ ጥልያን መሳርያ በአየር አወረደላቸው። (ለጥልያን ገቡ ) ካለው ሰበካ ያዙ። በረንታ ወረዳ (ቢቸና አውራጃ ) ደረሱ። የዱሀ ከተማ ሰፍረው ህዝቡን መሳርያ እየነጠቁ (ጥልያንን እንዳይወጋ ) ጥልያን ደግ መንግስት ነውና እንገዛለን እያሉ ይሰብካሉ (እንዲሾማቸው)።

«ልጅ በላይ ዘለቀ ግን እዋጋለሁ እንዋጋ እያለ እኛን ወንድሞቹን አነሳሳን» አሉ ፊታውራሪ ተሻለ አለሙ «ቀሰቀሰን ከሰላሳ እስከ ሀምሳ የምንደርስ ያንድ አያት ልጆች …የገልገል ቂልጡ ልጆች …ታጥቀን ተነሳን። ከቀኛዝማች በላይ መሸሻ ሰዎች መሳርያ እየነጠቅን በረሀ ገባን ።»

«ጦር ሲያሳድደን …ስንሸሽ …ቤት ሲያቃጥልብን … ከሁዋላው ወይም ከጎኑ በድንገት እየመታነው መሳርያ ነጥቀን ስናመልጥ …..እንዲህ ስንል አንድ ቀን የማናልፈው ጉዳይ መጣ። ግንባር መግጠም ግድ ሆነ ። ጠላት መሸሻ አሳጣና ።»
«የዛሬን ጦር ማን ይምራው ?» አለን ልጅ በላይ
«አንተን መርጠናል …እስከ መጨረሻው» አልነው።
“ሁላችሁም ወንድማማች ናችሁ ።” አልኳቸው ፊታውራሪ ተሻለን “በላይ ዘለቀን እርስዎ እንኩዋን በ4 አመት እበልጠዋለሁ ብለዋል ። እንግዲያው በምኑ ነው አለቃችሁ እንዲሆን የመረጣችሁት ?”
“እንዴ ! በደግነቱ ፡ በጀግንነቱ ! ጠባየ መልካም በመሆኑ ! እኔ ይቅርብኝ ብሎ ለሌላው ስለሚያዝን !” (ያን ጊዜ ፡ 1928 አ.ም. ልጅ በላይ 3 ወልደዋል ። ልጅ ተሻለ ግን ገና በታህሳስ ነው ያገቡት)።

ወይዘሮ ድንቅነሽ ሀይሉ (የራስ ሀይሉ ልጅ ) ጥልያን ሾመዋቸው የለምጨን ጉልተ ገዥ ሆነው ሄዱ። ህዝቡን መሳርያ አግባ ብለው አሰባሰቡ። በላይ ዘለቀና ወንድሞቹ በድንገት ገብተው መሳርያዎቹን ነጥቀው ሴትየዋን ሳይጎዱ ሳያጎሳቁሉ ወደ መጡበት መልሰው ላኩዋቸው ። የነጠቁዋቸውን መሳርያ 35 ያህል ጠመንጃ ዋሻ ደበቁት። ለራሳቸው በቂ መሳርያ ይዘዋላ።
ከዚህ በሁዋላ ደብረ ማርቆስን ጥልያን እየያዘ በላይ ዘለቀን ያሳድነው ጀመር ። ከ1928 አ.ም. ሚያዝያ እስከ ግንቦት 29 ቀን ድረስ ሁኔታው ተመሳሳይና ተደጋጋሚ ነበር። ጦር ይመጣል …ያስሳል …..እነ በላይ ዘለቀ ይሸሻሉ …በሁዋላ ቀስ ብለው መጥተው ጥቂቱን ገድለው መሳርያ ነጥቀው ….እልም ! መሳርያ በየዋሸው ያከማቻሉ።
እንደዚህ ብዙ አሰሳ ተሞከረ። ባንዱ አሰሳ የበላይ ዘለቀ ቤትና የለምጨን ቤቶች በሙሉ ተቃጠሉ። ከብቱም ተዘረፈ ። ጠላት ለምጨን 3 ጊዜ ነው ያቃጠለው።

“እስከ ታህሳስ 29 ቀን ድረስ አሰሳው የሚካሄደው በባንዳ ነበር ።” በታህሳስ 8 ቀን 1929 ግብጣን ደበቡ የተባለ ጥልያን ቢቸና ገባ ቢሉን ከዲማ ገስግሰን ቢቸና አደጋ ልንጥል ስንል ካህናት ጽላት ይዘው ስእል መስቀል ይዘው “አገሩንና ታቦቱን ያቃጥልብናልና አትውጉት ። እሱን እኛ ተመለስ እንለዋለን ።” ብለው መለሱን ። ግብጣን ደበቡም በላይ ዘለቀ መጣብህ ቢሉት ወደማርቆስ ተመለሰ ።”

በየካቲት 29 ጥልያን አገሩን አስነስቶ ወረረን ። ከያውራጃው ግብጣን ደበቡ አስከተተ ። ጦር ሲመጣባቸው እነ በላይ ዘለቀ ሸሹ ። አጥቷቸው ሲመለሱ እያደፈጠ በጎን አደጋ እየጣሉ ብዙ መሳርያ ነጠቁት ።
“የግንቦት እርገት ለት ..በ29 ነበር የዋለ ..ጥልያን ራሱ መጣ” የበላይ ዘለቀን ዘመዶች ከለምጨን እየደበደቡ ወደ አርበኞቹ እንዲመሩዋቸው አስገደዱዋቸው ። “ጦሩ ሲመጣ አሳለፍነው ። ከጎን አደጋ ጣልንበት ። በላይ ዘለቀ አንዱን ትሊንቲ ገደለው ኩረኔሉን አቆሰለው ። ብዙ ባንዳዎች ሞቱ ።”

ታስሮ እየተደበደበ ሲመራ የነበረው አዛዥ ቢያዝን ዱብዳ የተባለው የበላይ ዘለቀ ዘመድም ቆሰለ ።
በሰኔ 29 (1929) ጠላት በቅምቧት በደጀን በገበያ በሽበል በበረንታ የነበረውን “ደንበኛ ” በሙሉ አከተተው ። (ደንበኛ የሚባለው “የመንግስት ” የደንብ ብረት የያዘ ነፍጠኛ ነው ) ቀኛዝማች ስማ ነገዎ አዝማች ሆኖ ይህን ሁሉ አስከትቶ አባይ ወረደና አባራ ጂወርጂስ ሰፈረ ። ሀሳቡ እነ በላይ ዘለቀ ወደ ጫቀታ እንዳይሻገሩ በር በሩን ለመዝጋት ነበር ።
“እንውጋው ” አለ በላይ ዘለቀ

“ጦሩ በጣም ብዙ ነው አንችለውም ” አሉት ሌሎቹ። “ግድ የለም ።ጦሩ በየመንደሩ ይመራል ። አዝማቹ ላይ አደጋ እንጣልበት ።”
እነ በላይ ዘለቀ ፡ ቀኛዝማች ለማ ነገዎ ያደረበትን በለሊት ከበቡት ። ሲነጋ ለማ ነገኦን ከነወንድሞቹ ደመሰሱት ። ጦሩ በሙሉ እጁን ሰጠ ። መሳሪያውንና በቅሎውን ሁሉ አስረከበ ። ድል አድራጊዎቹ መሳርያውን ዋሻ ውስጥ ደበቁት ። በቅሎዎቹን ወደ ጫቀታ ልከው በጥይት ለወጡዋቸው ።” ይሄ የሆነው ሰኔ 10 ነበር። ሰኔ 12 በአውሮፕላን ይደበድቡን ጀመር ። በረንታ ጎይ ጂወርጂስ ላይ 12 ሰው ሞተብን ። እኛም ተመልሰን ወደ በረሀችን ሸሸን ።” ፊታውራሪ ለማ ሞገስ የጣልያን የጦር እንደራሴ ሆኖ ከማርቆስ ተልኮ ወጥቶ ዲማ አጠገብ ገድ ወንዝ ዋሻ ውስጥ እንዳለ ከበባቸው ። ወጥተው ገጠሙ ። ድል ነሱት ።
ብዙ ሰው ሞተበት ። እሱ ግን አመለጠ ።
በላይ ዘለቀ 60 ያህል ምንሽርና አልቤን ማረከ ። ምንሽርና አልቤን ሲያገኙ የመጀመርያ ጊዜያቸው ነበር ። እስካሁን ግን ሲዋጉ በናስማስር ፡ በውጅግራ ፡ በለበን ብቻ ነበር ።
“ድፍን ሀምሌን ተከበብን ። ለምጨን አንድ ዋሻ ገብተን ተደበቅን ። እኛን ሲያጣን ጊዜ የጎይ ጂወርጂስና ያካባቢውን ህዝብ ጎይ ላይ ሰብስቦ በላይ ዘለቀን ካላመጣችሁ ብሎ በመትረየስ ፈጃቸው ።” በላይ ዘለቀ የቶክሱ እለት ሞቶ ተቀብሯል ተብሎ ለጥልያኖች ተነገራቸው። ሰው ሰደው መቃብሩን ቢያስመረምሩት ሴት ሆና ተገኘች ።
አንዱ አሳባቂ በላይ ዘለቀ ወደ እነብሰ አውራጃ ነው የሄደው ብሎ ለጥልያኖች ጠቆማቸው ። የጥልያን ጦር ወደ እነብሴ ዘመተ። የእነብሴና የጎንቻ ህዝብ ገጠመውና ጨረሰው ። አንድ ጥልያን ብቻ አመለጠ ።

በላይ ዘለቀና አገሬው
እስከ ነሀሴ 1929 ድረስ የበላይ ዘለቀ ተከታዮች ከ30 እስከ 50 የሚደርሱ ወንድሞቹ ብቻ ነበሩ ።
“ነሀሴ ጂወርጂስ በላይ ዘለቀ በረንታ ላይ አዋጅ አስነገረ። እኛን ምሰሉ ፡ እርዱን ። አለዚያ ግን ይህ የጦር ሜዳ ነውና እንዳትጎዱ ሂዱ ልቀቁ።”
“እናርጅ እናውጋ (የደብረወርቅ ወረዳ ) በረንታና ሸበል፡ ጉበያ (ደጀን አጠገብ ) እነማይ (ቢቸና አውራጃ ) …ይሄ ሁሉ አመነ ፡ ተባበረን።
“ከህዳር ማርያም (1930) እስከ መጋቢት ውድማትን ፡ አዋባልን ፡ ቅምብዋትን ፡ ሊበንን ፡ ባስን ፡ አነድድን ደጀንን …እነዚህን ያዝን ።”
“በየካቲት ትሊንቲ ከጫቀታ ዘመተብን አባይ ደረሰ ። አገድነው ። ብዙ ውጊያ ተደረገ ። 80 ብረት (ከነሰው ) ማረክን ። መለስነው ። ወደ ደጀን ተመለስን ።”
“ከሸዋ ሲዘምትብን አባይ ላይ አገድነው። ወር ካስራምስት ቀን ተዋጋነው። 3 መኪናዎች ሰበርን ። ውስጣቸው የነበሩ ጥልያኖች ሞቱ ።

“ጥልያን ሀይሉን አጠናክሮ በደጀን በኩል ከሸዋ መጣብን ። 12 በጦለኔ በጀኔራል ማሊን አዝማችነት መጣ ።
“መጋቢት 19 ቀን (1930) ውጊያው ማለዳ የጀመረ በአስራ አንድ ተኩል አበቃ ። መትረየስና መድፍ ከታች ፈረሰኛ በሻምላ (በጎራዴ ) ” ተጨምሮበት ከላይ አሮብላ። ወንድሞቻችን አለቁ ። የጦር አዝማች የነበረው የበላይ ዘለቀ ወንድም ደጃዝማች ታደለ ላወቅ ወደቀ ። ተሰማ ላቀው ቆስሎ አመለጠ ። 300 ያህል አለቅን ። የተቀረውን ጨለማ ገላገለን ።
“ጠላት ፆን ማርቆስ ገባ ::እኛ ወደ በረሀችን ገባን ::”
“ሚያዝያ 4 (1930) እበረሀችን አፋፍ ላይ እንደ ሰፈርን ጠላት ባራት ረድፍ ቢቸና ገባ። ሚያዝያ 6 ጦሩን ባራት ማእዘን አቀነባብሮ በረሀችንን በሙሉ ከበበው ። በመካከሉ ደግሞ በግንባር እልፍ አእላፋት ጦር ይዞ ተሰለፈ ።”
“ባለው ሀይላችን ገጠምነው ።”
“ሊያፍነን ሞከረ በብዛቱ ።”
“የቆላ ጫካ ነው ….እሳት ለቀቅንበት ”
“ይገርማል እኮ የቀን ነገር !ነፋሱ እሳቱን እያንቦገቦገ ወደነሱ ወሰደው ። ብዙዎቹን እሳት በላቸው ። ብዙዎቹ አመለጡ ። “የበላይ ዘለቀ ሚስት ወይዘሮ ሸክሚቱ አለማየሁ በመትረየስ ሞቱ (እንደ ወንድ ለብሰው ነበር ) ልጅ የሻሸወርቅ በላይ ተማረከች ። የናትየዋ እናትም ተማረከች ። “ከዚህ በሁዋላ አባይን ተሻግረን ጫቀታ ገባን ። ያጌ ከተማ ግዛው ሰብስቤ የተባለው የጥልያን እንደራሴ ገድለን አገሩን አቃጥለን የጎበዝ አለቃ ሾመን … ፊታውራሪንና ቀኛዝማች እያሱ ልጅ በላይ ሾመው …ተመልሰን ወደ ለምጨን በረሀ ገባን ።”