አርማጭሆ መልስ፤ ወደ ወገራ ጉዞ ክፍል ፬

አርማጭሆ መልስ፤ ወደ ወገራ ጉዞ

ክፍል ፬

ከአርማጭሆ ጎንደር ስገባ ድርገት ነበር፡፡ በጣም መሽቷል፡፡ ቀበሌ 12 ቢራ ለመጠጣትና ወሬ ለመቃረም ገባሁ፡፡ የገባሁባት ቤት አንድ ጊዜ ከአንድ ወዳጄ ጋር አውቃታለሁ፡፡ የቀበሌ ቤት ናት፡፡ ቤቷ ከዐሥር ሰዎች በላይ በአንድ ጊዜ ማስተናገድ አትችልም፡፡ ስለዚህ ደንበኞች በአንድ ሰዓት ከገቡ ሌላ የውጭ ሰው መግባት አይችልም፡፡ ከዚህች ቤት የማይዳሰስ ፖለቲካ አሊያም አገራዊ ጉዳይ የለም ማለት ይችላል፡፡ ቤቷን በወሬ ማድመቅ የሚችል ሰው መቼም ቢሆን ቢራ ከፍሎ ላይጠጣ ይችላል፡፡ ሞቅ ያለው የሰሊጥ ነጋዴ ‹‹አባቴ ይሙት!›› እያለ የሁሉንም ሰው የሳምንት ሒሳብ ሊዘጋ ይችላል፡፡ የቻልከውን ያክል እየጠጣህ መጫወት ነው፡፡

ከዚህች ቤት ብዙ ነገር ለመረዳት ችያለሁ፡፡ የተሸከምነው አምባገነን ሥርዓት በዜጎች መካከል አለመተማመን ፈጥሯል፡፡ የዚች ቤት ደንበኞች ሕወሓት በዐማራው ሕዝብ ላይ የሚያደርሰው ግፍ ከመጠን የዘለለ መሆኑን ያምናሉ፡፡ ከመጠጥ ደንበኞች መካከል የሰሜን ጎንደር ፖሊስ መምሪያ በኃላፊነት ቦታ ላይ እንዳሉ የተረደዋቸው ሰዎች ሁሉ ነበሩበት፡፡ የጎንደር ዐማሮች ሕወሓትንና የትግራይ ሕዝብን አንድ አድርገው ይመለከታሉ፤ እርግጥ ነው ይህ በብዙ የአገራችን አካባቢዎች እንዳለ አውቃለሁ፡፡ ጎንደር ግን በግልጽ ያለ ምንም ፍርሐት እከሌ አለ የለም ሳይባል በግልጽ የሚወራ አሊያም የሚነገር ነው፡፡ ከዚችው መሸታ ቤት የሰማሁት እውነታ (ቀልድ ሊሆን ይችላል) አስተሳሰቡ ምን ያክል የሰረጸ እንደሆነ ሊሳይ ይችላል፡፡

አንድ ከሽሬ የመጣ ሰው ቸቸላ ሆስፒታሉ ጋር ለመሔድ መስቀል አደባባይ ላይ ባጃጅ ኮንትራት ይጠይቃል፡፡

‹‹ዋይ! አንተ ቸቸላ ሆስፒታል ስንት ትወስደኛለህ ኮንትራት?›› ይላል ከትግራይ የመጣው ሰው፡፡

የባጃጅ ሾፌሩ ‹‹መቶ ብር!›› በማለት ይመልሳል፡፡ ከመስቀል አደባባይ እስከ ቸቸላ ሆስፒታል የኹለት ብር ታክሲ ትራንስፖርት ነው፡፡ ኮንትራት የሚይዝ ሰው ከዐሥር ብር የበለጠ አይከፍልም፡፡ ሆኖም እንግዳው ሰው ባልጠበቀው የዋጋ መናር ተገርሞ ‹‹ዋይ አቡነ አረጋይ! አንተ ለዚህ ቸቸላ ሙቶ ብር ያልከኝ አገሬን ሽረ አድርሰኝ ብልህ ስንት ልትወስደኝ ነው?›› በማለት የባጃጅ ሾፌሩን ጠየቀው፡፡

‹‹ተመልሰህ ካልመጣህ በነጻ እወስድሃለሁ!›› በማለት መለሰለት፡፡

ይህ እዚች መሸታ ቤት ሲነገር የሰማሁት ነው፡፡ መሸተኞች የራሳቸው ጓደኛ እንደተናገረው አድርገው ነው ያወሩት፡፡ ቁም ነገሩ እውነት ወይም ቀልድ መሆኑ ላይ አይደለም፡፡ የትኛውም ቢሆን አገዛዙ የትግራይ ተወላጆች እንደ ባዕድ እንዲቆጠሩ አድርጓቸዋል፤ ትግሬዎች በየትኛውም የአማራ አካባቢ በጥርጣሬ ይታያሉ፡፡ ይህ ከኹለት ነገር ሊፈጠር ችሏል፡፡ አንደኛ አገዛዙ ወደ ተለያዩ አካባቢዎች የሚልካቸው ደኅንነቶች የትግራይ ተወላጆች መሆናቸው ትግሬ የተባለ ፍጥረት ሁሉ የአገዛዙ አጋዥ እንደሆኑ ተደርጎ ይወሰዳል፡፡ ሌላኛው ምክንያት ደግሞ አገዛዙ የትግሬዎችን መጠላት የሚፈልገው ይመስላል፡፡ ምክንያቱም ትግሬዎች በሌሎች ኢትዮጵያውያን እንደጠላት ሲቆጠሩ አንድነታቸውን አጠናክረው ሕወሓትን ሊደግፉ ይችላሉ ከሚል ያረጀ ያፈጀ የፖለቲካ ፍልስፍና የመጣ ሊሆን ይችላል፡፡

በጣም ረጅም የበረሀ መንገዶችን ሳቆራርጥ ሰንብቼ በምሽትም መሸታ ለመሸታ ቤት መንከራተቴ ያለኝን ጊዜ ለመቆጠብ መሆኑን አንባቢ ይረደዋል የሚል እምነት አለኝ፡፡ ካደርኩበት የ‹ኤል ሸፕ› ሆቴል ሰማዩ ገና የአህያ ሆድ ሳይመስል ነቃው፡፡ በድካም የሰነበተ ሰውነቴን በቀዝቃዛ ውኃ ነክሬ በጠዋት ወደ ደባርቅ አቅጣጫ ወጣሁ፡፡ ትናንት ወደ አርማጭሆ የሔድኩበትን አቅጣጫ ትቼ ወደ ኮሶዬ አመራሁ፡፡ የዛሬው መንገዴ ትናንት የሔድኩበትን በርሀ ወደ ታች እየተመለከትኩ ደጋ ደጋውን ነው፡፡ ከጎንደር ከተማ ርቄ አሁን ወገራ ወረዳ እገኛለሁ፡፡ በደጋማው የወጋራ አፋፍ ላይ ሆኘ የአርማጭሆና የኹመራ ጫካ ታዬኝ፡፡ ‹‹ኧረ ጥራኝ ጫካው›› አልኩኝ በውስጤ፡፡

የወገራ እረኛ በቅርርቶ፤

‹‹ኧረ ጥራኝ ጫካው ኧረ ጥራኝ ዱሩ

ላንተም ይሻልሃል ብቻን ከማደሩ፡፡

ተንኮለኛው ገደል በሬ ያሳልፋል፤ ዝንጀሮን ይጠልፋል

ጂል ያመጣው ነገር ለሁሉም ይተርፋል›› ኮሶዬ አፋፉ ላይ ሆኖ ዋሽንቱን ከድምጹ ጋር እያቀናጀ ይሸልላል፡፡

ምን ታደርገዋልህ! እኔ ከጫካ ጋር የማደር ልምድ የለኝም፡፡ ከራማዬ ከአርማጭሆና ከቋራ ጫካዎች ጋር ስላልሆነ ቻው ብያቸው መጥቻለሁ፡፡ እተራራው ላይ ሆኜ እንደገና ሳያቸው ለምን እንደ እናቴ ልጅ እንደናፈቁኝ አላውቅም፡፡ የምር ግን በጭጋግ የተሸፈነውን ከአድማስ ማዶ ዓይኔ እስኪታክተኝ የማየው የሆነ የሚናፍቅ፣ የሚስብ ነገር አለው፡፡ ‹‹አልበር እንዳሞራ›› ነው ነገሩ፡፡ ወይ እንደ አእዋፋት አሊያም እንደ መላእክት ሆኜ ክንፍ ቢኖረኝ ኖሮ ምንኛ በታደልኩ፡፡ በ‹‹ኖሮ›› አይኖርም፤ ወደ ከምናቤ ልወጣ ግድ ነው፡፡

የኮሶዬ ነፋሻማ ሜዳ ከጎንደር በግምት 15 ኪሎ ሜትሮች አካባቢ ይርቃል፡፡ ኮሶዬ ለዓይን የሚስብ ገደል ጫፍ ያለ ሜዳማ ቦታ ነው፡፡ ነፋሻማና ብርዳማ ነው፡፡ በጠዋት ስለደርስኩ የብርዱ ነገር አይጣል ነው፡፡ የኮሶዬ ሜዳ ገደሉ ጫፍ ላይ ሎጅ አለ፡፡ የሎጂው አልቤርጎዎች በእሳር ክዳን (ትኩል) የተሠሩና በነገሥታቱ የተሠየሙ ናቸው፡፡ ሎጂውን እየዞርኩ ስመለከት በአጼ ኃይለ ሥላሴና በንግሥት ኤልሳቤጥ የተሰየሙ የጎጆ አልቤርጎዎች (ትኩል) ሳይ ጊዜ ለምን እንደሆነ ሰዎችን ጠየቅኩ፡፡

ንግሥት ኤልሳቤጥ ኢትዮጵያን በ1956/7 ዓ.ም. ከንጉሠ ነገሥት አጼ ኃይለ ሥላሴ ጋር ስትጎበኝ ካየቻቸው ቦታዎች መካከል የጢስ አባይ ፏፏቴና የሰሜን ተራሮች ይገኙበታል፡፡ የሰሜን ተራሮችን ከንጉሠ ነገሥቱ ጋር ጎብኝታ ስተመለስ መስንግዶ የሚደረግበትን ቦታ መምረጥ ያስፈልግ ነበር፡፡ ከዚህ አካባቢ ከኮሶየ የተሻለ መስህብነት ያለው ቦታ ጠፋ፡፡ ከእከሌ ሆቴል አሊያም ሎጅ የሚሉት ነገር አልነበረም፡፡ ኮሶዬ መስኩ ላይ የአካባቢው ነዋሪዎች የሰባውን ሰንጋ አርደው በብላክ ሌቨል ፋንታ የወገራን ጠላ ዘልለው፤ በእንግሊዝ ኬክ ፋንታ የጎንደርን እንጀራ አዋጥተው የታላቋን ኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥትና የታላቋን ብሪታኒያ ንግሥተ ነገሥት ለመቀበል ዳስ ሠሩ፡፡ በዚህ ቦታ የሁለት ታላላቅ ርዕሳነ ብሔራት ተስተናግደዋል፡፡ ያኔ አሁን ከተራራው አናት ላይ ያለው ሎጂ አልነበረም፡፡ ያኔ ሎጅ ሳይሆን የቆርቆሮ ክዳን የነበረው ቤት አልነበረም፡፡ የሰው ልጅ ከሠራው ይልቅ ተፈጥሮ ያበጀችው እይታ ይማርክ ነበርና ነገሥታቱ ይህን ቦታ በድንኳንና በዳስ አረፉበት፡፡ እንኳን እኔ ሐበሻው ንግሥት ኤልሳቤጥም በዚህ ቦታ ውበት ለመማረኳ አልጠራጠርም፡፡

አሁን ካለው ዘመናዊ ሎጅ የሚያስተናግድ ልጅ ‹‹የታላቋን ብሪታኒያ ንግሥትና የታላቋን ኢትዮጵያ ንጉሥ በጊዜው ያስተናገዱ አዛውንት እዚያ ጋ አሉ፤ ማገኘት ትችላለህ›› አለኝ፡፡ በደስታ እየሮጥኩ ወደ አመላከተኝ ቤት ሔድኩ፡፡ የባህር ዛፍ መከላከያ ለበቅ ባልይዝ ኖሮ ቤት የነበረው ውሻ ይበላኝ ነበር፡፡ ሆኖም ውሻው ሲታገለኝ እደጅ የነበሩ የቤተሰቡ አባለት ደረሱልኝና በውሻ ከመነከስ ተረፍኩ፡፡ የታላላቅ አገሮቹን ንጉሥና ንግሥት ያስተናገዷቸው ሰው ማግኘት እንደምፈልግ ነገርኳቸው፡፡ መደብ ላይ የተቀመጡ አዛውንት አመላከቱኝ፡፡ ጠየቅኳቸው፡፡ እድልለኛ አልነበርኩም፡፡ እኔ ያገኘዋቸው የእድሜ ባለጸጋ ንጉሡና ንግሥቲቱ ሲስተናገዱ የተመለከቱ እንጅ እራሳቸው አስተናጋጅ አልነበሩም፡፡ የሆነው ሆኖ የእድሜ ባለጸጋው ከቤታቸው ወጣ ብለው ወደ ሜዳው በብትራቸው እያመለከቱ ‹‹ድንኳን የተጣለው እዚያ ላይ ነበር፤ አይ ምን የመሠለ ሠንጋ አርደን ነበር መሠለህ! ግን ያዘጋጀነውን ሁሉ በደንብ ሳይበሉ ትተውን ሔዱ›› አሉኝ፡፡ በጊዜው ርዕሳነ ብሔሮቹን ለማስተናገድ የተመረጠ ሰው አልነበረም ወይ? የሚል ጥያቄ አቀረብኩ፡፡ አሁንም በድጋሚ ከቤታቸው በላይ ወደ ተራራማው ጫፍ እያመላከቱ ‹‹ወደ አቀበቱ መውጣት የምትችል ከሆነ መንገድ የሚመራህ ሰው ልስጥህ›› አሉኝ፡፡

የምችል አይደለሁም፡፡ ሩጫዬ ከጊዜም ከገንዘብም ጋር ነው፡፡ አንድ ቀን የጉዞዬን ጊዜ ባራዘምኩ ቁጥር የጋዜጣው መውጣት አለመውጣት ያሳስበኛል፡፡ ደግሞም በመንገድ ላይ የያዝኩት ስንቅ ቢያልቅ መመለሻ እንኳ አይኖረኝም፡፡ ስለዚህ በያዝኩት የጊዜ ገደብ መሠረት መጓዝ አለብኝ፡፡ የኮሶዬ ተራራ አናት ላይ ሆኜ ወደ በርሀው ስመለከት የተራራ ሰንሰለቶችን በጭጋግ ተሸፍነው አየሁ፡፡ ትናንት የነበርኩበት የአርማጭሆና የጠገዴ በርሃ በርቀት ይታየኛል፡፡ በእጄ የምነካት የምትመሥለው የጩጌ ማርያም ገዳምም ከሥሬ ናት፡፡ የጩጌ ማርያም ገዳም በድንጋያማ የተራራ ሰንሰለት ላይ ያለችና በ17ኛው ክፍለ ዘመን የተገደመች ናት፡፡ ከአንድ ዓመት በፊት ሒጄ አይቻታለሁ፡፡ አካባቢውን ለማያውቁ አንባቢያን የጩጌ ማርያም ገዳምን በትንሹም ቢሆን መናገር ያለብኝ ይመስለኛል፡፡ ገዳሙን ለማየት ስሔድ የያዝኩትን ማስታዎሻ ሳገላብጥ የሚከተለውን አገኘሁ፡፡

የአገሬዉ ሰዉ ለሰዉ ብርታት የሚሰጥበትን ዘዴ ሳስብ ይገርመኛል፡፡ የወገራ ሰዉ ‹በአገጩ በዚህ በኩል በጣም ቅርብ ነዉ!› ካለህ ቢያንስ ለሰዓታት ትጓዛለህ፡፡ በትሩን በረጅሙ እያጠቆመ ‹በዚያ በኩል ቅርብ ነዉ!› ካለህ ቢያንስ ለግማሽ ቀን ትሔዳለህ፡፡ ኮሶዬ ያገኘሁት ሰው ወደ ጩጊ በየት በኩል እንደምሔድ እንዲያሳየኝ አቅጣጫውን ስጠይቀው ሊነካት ያሰባት ይመስል እያንጋጠጠ ‹‹እዚች ተራራ ገደሉ ላይ የሆነ ቤት የሚመስል ነገር ይታይሃል?›› ሲል ጠየቀኝ፡፡ ከአለንበት አፋፍ ገደል ሥር እየተመለከትኩ ጫካና አምባ ተራራ እንጅ ቤት አለመኖሩን ነገርኩት፡፡ ‹‹ያችን አምባ እያት እንጅ! ከአምባዋ ጎን ካለዉ ገደሉ ላይ ተመልከት ቤት ታያለህ!›› አለኝ፡፡ እንደምንም ከርቀት ከጭጋግ ጋር ለመለየት የሚያስቸግር ቤት አየሁ፡፡ ‹‹አየሁት አየሁት!›› ስል አጻፋ መለስኩ፡፡

‹‹ያች ብዙ ተዐምራት የተሰራባት ጩጊ ማርያም ገዳም ናት›› አለኝ፡፡ ‹‹በየት በኩል ነዉ መንገዱ?›› ተጨማሪ ጥያቄ አስከተልኩ፡፡

‹‹በዚህ ነዋ›› በግንጭሉ እየጠቆመ ገደሉን አሳዬኝ፡፡

‹‹እንዴ! ይህ እኮ እንኳን ለሰዉ ለዝንጀሮም አይመችም!›› አልኩት፡፡

ሳቀብኝና ‹‹ቅርብ ነች፡፡ በአንድ ሰዓት ውስጥ ደርሰህ መመለስ ትችላለህ!›› አለኝ፡፡ በወኔ መንገዱን ጀመርኩት፡፡

ይህን ገደል በሽርታቴ ተያያዝኩት፡፡ ገደሉ ያን ያክል እንዳየሁት የሚያስፈራ ሆኖ አላገኘሁትም፡፡ በቀላሉ በስበት ኃይል እየተምዘገዘግኩ ወረድኩት፡፡ በጫካ ውስጥ ፈንዛ ጅራት ካላቸዉን ጉሬዛዎች እና ዝንጀሮዎች ጋር እየተላጋሁ ከራሴ ጋር እያወራሁ ሸመጠጥኩ፡፡ ዝንጀሮዎች እየጮሁ ገደል ለገደል ሲሮጡ መርግ ቢልኩብኝ እያልኩ በፍርሃት አስጨንቀውኝ ነበር፡፡ ደግነቱ በዛፎቹ ጥላ ሥር ስለምጓዝ ትንሽ ያስፈራል እንጅ ሙቀቱ አይታወቅም፡፡ በርቀት ገዳሙን እያየሁ የደረስኩ እየመሰለኝ እኔም በአገጬ ለመንካት እየሞከርኩ ለአንድ ሰዓት ያክል ለመጓዝ ተገደድኩ፡፡

ገዳሙ መግቢያ አካባቢ አፈሩ አንሸራቶ ጉድ ሰርቶኝ ነበር፡፡ ከዚያ ቦታ ላይ ብወድቅ ማንም ሳያየኝ መዳረሻዬ ተጨማሪ ኹለት ሰዓት የሚያስኬድ ገደልን እጨርስ ነበር፡፡ ሸርተት ካሉ መዳረሻው የማይታወቅ አገርና ዓለም ነው፡፡

ገዳሙ ያለበት እጅግ ገደል የበዛበት ሰንሰለታማ የድንጋይ አምባ ነዉ፡፡ መነኮሳቱና አርድዕቱ በገደሉ ላይ እንደዚያ ሲሮጡ በዝንጅሮቹ የገደል ላይ ጉዞ መደነቄ አናደደኝ፡፡ በዚያ ገደል ‹ሰዉ ዓለምን ንቆ በባዕት ለእድሜ ልካቸዉ የሚኖሩ መነኮሳት› እንዳሉ ማየት እጅግ ይገርማል፡፡ እኔ ላንድ ቀን እንቅልፍ ወስዶኝ የምተኛ አይመስለኝም፡፡

ይህ ገዳም የተገደመው በአባ ምዕመነ ድንግል በአስራ ሰባተኛዉ ክ/ዘመን ነዉ፡፡ በአጼ ሱስንዮስ ዘመነ መንግሥት (ከ1600- 1624 ዓ.ም.) አባ ምዕመነ ድንግል ብዙ መከራንና እንግልትን እንደተቀበሉ ገድላቸው ይመሰክራል፡፡ ገዳሙ ካለበት የቋጥኝ ተራራ ወገብ ላይ ዋሻ አለ፡፡ ዋሻዉ ውስጥ ደግሞ በክረምትም በበጋም የማይሞላ የማይጎድል ‹ማዬ ዮርዳኖስ› ወይም ‹የዮርዳኖስ ዉኃ› የሚሉት አለ፡፡ ጸበሉ በርካታ ምዕመናን ይጠመቁበታል፡፡ ግን አይጎድልም፡፡ የሚጠመቅ ሰዉ ከሌለም ሞልቶ አይፈስም፡፡ አፈር በሆነበት ቦታ ምንጮች እየደረቁ ባለበት ጊዜ ግጥም ካለ ቋጥኝ ተራራ ላይ ይህ መሆኑ ለእንደኔ ዓይነቱ ተጠራጣሪ አጃኢብ ያስብላል፡፡ ጸበሉን ጠጣሁት- አይሰለችም፡፡ እንዲያዉም እዉነት ለመናገር ከመጣሁ በኋላ ናፍቆኛል፡፡ መልኩ ሀጫ በረዶ ይመስላል፡፡ በመቆሙ ብዛት አረንጓዴ (አልጌ) አልጣለበትም፡፡ ይህን ጸበል ጠጣሁትም፤ ሲያጠምቁ ያገኘዋቸው አባም አጠመቁኝ፡፡

ብቻ ግሩም ነዉ እላችኋለሁ፡፡ ጸበሉን የሚጠጡ ፍጥረታት ገላቸው (አካላቸዉ) አይፈርስም፡፡ ጸበሉን የጠጡ 16 ፍየሎች ከነ ሙሉ አካላቸዉ ለ400 ዓመታት ለገባሬ ታእምር እስካሁን አሉ፡፡ ወልደዉ ለመሳም ያልታደሉ ሰዎች ከዚህ ቦታ መጥተዉ ተጠምቀዉ ጸበሉን ቢጠጡ የልጅ ጉጉታቸዉን እዉን ለማድረግ ዘጠኝ ወራት ብቻ እንደሚያስፈልጋቸው ከገዳሙ ያገኘዋቸው አርድእት ነግረውኛል፡፡

ቦታዉ የዋልድባዉ ሰቋር ኪዳነ ምህረት ዓይነት ነዳላ አምባ አለዉ፡፡ ወደ ነዳላዉ አምባ ለመሄድ ጸበሉን የጠመቁኝ አባት በዚህ በኩል ሒድ አሉኝ ወደ ምዕራብ አቅጣጫ እያመለከቱ፡፡ በተቀደሰዉ ቦታ ጫማህን አዉልቅ በሚለዉ መጽሐፍ ቅዱሳዊ መርህ መሠረት ጫማ መልበስ ክልክል ነዉ፡፡ ጫማ የለመደ እግር በሚያቃጥል አለትና በሚቆረቁር አሸዋ ላይ መሔድ ይጠበቃል፡፡ በዚያ ድንጋያማ ተራራ እንደ ገበሎ አስተኔ በልብ አሊያም በአራት እግር መጓዝ ይጠይቃል፡፡ ከዋሻዉ ማዶ ‹ሰማያዊ ኬንዳ› የመሰለ ነገር ማዶ ካለዉ ገደል ላይ ተንጣሎ ይታያል፡፡ ያ ኬንዳ ምንድን ነዉ? ስል ጠየቅኩ፡፡ በተቀደደዉ የቋጥኝ ተራራ አልፎ የሚታየዉ ሰማይ ነዉ አሉን አባ፡፡ ከጸበሉ የነበረች አንዲት እናት ጋር አብረን እንድንሔድ አባ ነገሩን፡፡ ጉዞ ወደ ነዳላዉ አምባ፡፡ አብራኝ የምትጓዘዉ እናት እጅግ የበረታች ናት፡፡ እርሷ በዚያ ገደል ላይ ከዝንጀሮ እኩል ትፈጥናለች፡፡ ተከተልኳት፡፡ ድንጋይ በድንጋይ ላይ እየወጣን ወደ ነዳላዉ አምባ ተቃረብን፡፡ ወደ ገደሉ ስንወጣ በእጃችን እየቧጠጥን ነው፤ በእጃችን አጥብቀን ከመያዛችን በፊት ያገኘነውን ጎቶ ጥንካሬ መለካት ያሻል፤ አሊያ ዲካው ወደ ማይታወቀው ገደል መጓዝ ይመጣል፡፡ ከቦታዉ ስንደርስ አንድ ሽማግሌ አባት ከንቃቃት ድንጋይ ሥር እንደቤት አደርገዉ ሲጸልዩ ደረስን፡፡ አባ ከባዕታቸዉ ፈጽመዉ አይወጡም፡፡ የምጽዋት ገንዘብም ፈጽመዉ አይቀበሉም፡፡ ፎቶ ግራፍና ምስል እንድወስድ ብጠይቃቸዉ ‹‹ልጄ አወግዝሃለሁ›› አሉኝ ተቆጥተዉ፡፡ ይቅርታ ጠይቄ አቡነ ዘበሰማያት ደግመዉልኝ በበረከት ተለየዋቸዉ፡፡

በመጨረሻ እኔን ጠየቅኩት? ‹አባቶች ለነፍሳቸዉ እና ለአገር ደኅንነት ከዱር አራዊት፣ በልባቸዉ ከሚሳቡ ነፍሳት ጋር ሁሉ እንዲህ ይታገላሉ፡፡ እኔ ግን ከዚህ ድረስ መጥቼ በረከት እንኳ መውሰድ እንዴት ተሳነኝ?› እማሆይ ማዕድ አቀረቡልን፡፡ በላን፡፡

በልቤ የአባቶቼን ጽናት እያሰብኩ ወደ መጣሁበት ዓለም ለመመለስ ተነሳሁ፡፡ ከፊቴ አምዘግዝጎ ያረወደኝን ገደልና ጫካ ለመዉጣት፡፡ ዝንጀሮዎቹን ቢያዝሉኝ ስል ተመኘሁ፡፡ ዛፍ ለዛፍ የሚሯሯጡት ዝጉርጉር ጉሬዛዎች አስቀኑኝ፡፡ በ180 ዲግሪ ቀጥ ያለው የወገራ አቀበት ፊቴ ላይ ተደቀነ፡፡

……….

ወደ አያሌው ብሩ አገር ዳባት መንገድ ጀምርኩ፡፡ አምባ ጊዎርጊስ፣ ገደብዬ፣ ዳባት፣ ወቅን፣ ደባርቅ…፡፡ ዳባት ላይ የአያሌው ብሩ ቤተ መንግሥት አለ፡፡ አያሌው ብሩ የወገራ ገዥ የነበሩ ሲሆን በአጼ ኃይለ ሥላሴ ሀትሪክ ተሠርተዋል አሉ፡፡ አጼ ኃይለ ሥላሴ ወደ አዲስ አበባ እንዲሔዱ ጥሪ ሲልኩባቸው የወገራ ሰው እንዳይሔዱ መክሯቸው ነበር፡፡ ነገር ግን የወገራን ሰው ምክር ባለመሥማታቸው የአጼው ተንኮል ሰለባ ሆነዋል፡፡ በዚህም ምክንያት ድፍን በጌምደሬ ሲዘፍን ‹‹አያሌው ሞኙ ሰው አማኙ ሰው አማኙ፤ ኧረ አያሌው ተው በለው ተው በለው›› የሚለው የእርሳቸውን ሞኝነት ለማመለከት እንደሆነ ይናገራሉ፡፡ ቀሪውን ማጣራት የባህል ተመራማሪዎች ፋንታ ይሆናል፡፡

አምባ ጊወርጊስ ላይ ሆኖ ወደ ደባርቅ ሲመለከቱ አንዲት ኮረብታ በርቀት ትታያለች፡፡ ዳባት ላይ ሆኖም ይህችው ተራራ ከትክተት አትሰወርም፡፡ ዳባትን አልፈን ደባርቅ ሆነንም እናያታለን፡፡ የሰሜን ተራሮች አናት ላይ ብንወጣም ይህችን ተራራ ማንም አይጋርደንም፡፡ ይህች ተራራ ‹‹ወቅን›› ከተባለች አነስተኛ ከተማ ራስጌ ላይ የምትገኝ ስትራቴጂክ አምባ ናት፡፡ ስያሜዋም ‹‹ዞሮ ዞሮ ወቅን›› ትሰኛለች፡፡ ዞሮ ዞሮ ወቅን ከወገራ እስከ ኹመራ፣ ከአርማጭሆ እስከ ጃናሞራ፣ ከአዲአረቃይ እስከ ሽሬ ድረስ ቁልጭ ብላ በጉልህ ትታያለች፤ ዞሮ ዞሮ ወቅን፡፡

ከጎንደር እስከ አርማጭሆ፤ የቅማንት ጉዳይ፣ የግጨው ግጭትና የኢትዮ ሱዳን ድንበር ክፍል ፫

By Muluken Tesfaw

ከጎንደር እስከ አርማጭሆ፤ የቅማንት ጉዳይ፣ የግጨው ግጭትና የኢትዮ ሱዳን ድንበር

ክፍል ፫

ወደ አርማጭሆ መንገድ ጀምረናል፡፡ የተሳፈርኩባት ሚኒ ባስ የገነት ተራራንና ወለቃን በሌሊት አልፋ ወደ ትክል ድንጋይ እየተንደረደረች ነው፡፡ በነገራችን ላይ የገነት ተራራ ‹‹ትግሬ መጯኺያ›› በመባል ይታወቅ ነበር፡፡ በታሪክ ምሁራን ለዘመነ መሣፍንት መምጣትና ለጎንደር ነገሥታት ፍጻሜ ምክንያት ነው ተብሎ የሚታወቅ ራስ ሚካኤል ስሑል የሚባል ሰው ነበር፡፡ ራስ ሚካኤል ስሁል የትግራይ ተወላጅ ሲሆን ‹ንጉሥ ሠሪ› ወይም ደግሞ ‹አንጋሽ አፍላሽ› በመባል ይታወቃል፡፡ ይህም የሆነው እንዳይነግሥ የንግሥና ዘር የለውም፤ ስለዚህ የይስሙላ ንጉሥ ዙፋን ላይ አስቀምጦ ቤተ መንግሥቱን በቁጥጥር ሥር አደረገ፡፡ በዚህ ዘመን ነገሥታቱ ከጎንደር ራቅ ባሉ አካባቢዎች በግዛታቸው ሥር ያሉትን ሁሉ ማስተዳደርም ሕግን ማስፈንም ተሳናቸው፡፡ በዚህ የተነሳ ከርቀት ቦታዎች እየመጣ ፍትሕ የሚለምነው ሰው ቁጥር በረከተ፡፡

የተከዜ ወንዝንና በርሃን ተሻግረው ለቀናት ተጉዘው ጎንደር የሚደርሱት ትግሬዎች ጎንደር ከተማ ከደረሱ በኋላም ‹ብልኮ› እተባለው ሰፈር ላይ ኬላ ተጥሎ እንዳይገቡ ይከለከሉ ነበር፡፡ ይህም የነ ራስ ሚካኤል ፍትሕ ለማግኘት የትግሬ መጯኺያ የተባለው ተራራ ላይ በመውጣት የጎንደር ቤተ መንግሥትን ወደ ታች እየተመለከቱ ‹‹በሕግ አምላክ!›› እያሉ ይጮኹ ነበር፡፡ በዚህም ያ ተራራ ‹‹ትግሬ መጯኺያ›› እንደተባለ እንዲጠራ ምክንያት ሆነ፡፡ ዞሮ ዞሮ ተራራው አሁን ገነት ተራራ ተብሎ ስሙ ተቀይሯል፡፡ ጎሃ ሆቴል የሚባል መዝናኛም በደርግ መንግሥት ተሠርቶበት ትግሬ ይዝናናበታል እንጅ አሁን ላይ አይጮኽበትም፡፡

ወለቃ ከጎንደር ከተማ ወደ ደባርቅና ወደ ኹመራ መስመር ላይ ያለች ትንሽ መንደር ነች፡፡ ወለቃ የምትታወቀው ቤተ እስራኤሎች (ፈላሻዎች) መንደር በመሆኗ ነው፡፡ እስራኤል በዘመቻ ሰሎሞን የጀመረችውን ፈላሾችን ወደ አገሯ የመውስድ ሥራ በቅርቡ አጠናቃ ጎንደር ያለውን ቆንሲል ከመዝጋቷ በፊት የፈላሾች መንደር ወለቃ ነበረች፡፡ በወለቃ አሁን ላይ የዳዊት ኮከብ በሰማያዊ ቀለምና በነጭ መደብ የተሳለባት አንዲት የጀበና ቡና ቤት ውጭ አንድም አይሁድ ወይም የአይሁዳዊነት ምልክት አይታይም፡፡ የአይሁዳውያን መንደር ነበረች በሚል ብቻ ትታወሳለች፡፡

ላይ አርማጭሆ ትክል ድንጋይ እየደረስን ነው፡፡ ትክል ድንጋይ ከቅማንት ማንነት ጋር ችግር ከተፈጠረባቸው ቦታዎች አንዷ ናት፡፡ በነገራችን ላይ ከቅማንት የማንነት ጥያቄ ጋር በተያያዘ በዚህ አካባቢም እንደ ጭልጋው ሁሉ የከፋ ነገር ተከስቷል፡፡ ከ2006 ጀምሮ እስከ 2008 ዓ.ም. ግማሽ ዓመት ድረስ በሰሜን ጎንደር ብዙ ፍርድ ቤቶች የሚመጡ ክሶች የፍች ጥያቄዎች ያዘሉ ነበሩ፡፡ በጥብቅና እና በዳኝነት ሥራ ላይ የተሰማሩ አንዳንድ ግለሰቦች እንዳረጋገጡልኝ በርካታ ጥንዶች ‹ሰይጣን› በመካከላቸው ገብቶ ትዳራቸውን ንዶታል፡፡ በአማርኛ እያወሩ በግእዝ የሚያስቀድሱ በሥርዓተ ተክሊል ጸሎት ተጋብተው ‹አይ ትዳር እንደነሱ ነውጅ!› እየተባሉ ሲነገርላቸው የነበሩ ጥንዶች ቤት በድንገት የሚፈርሰው ‹ሉሲፈር› በመካከላቸው ካልተገኘ በስተቀር እንዴት ሊሆን ይችላል? አባ የንስሀ ልጆቻቸውን እሁድ እሁድ ሰብስበው ‹ስለ ፍቅረ ቢጽ› ሲያስተምሩ ‹ትዳርና ፍቅር እንደ እነ እንትና ነው!› እያሉ በአርኣያነት ሲጠቅሷቸው የነበሩ ጥንዶች ቤት በሰዓታት ውስጥ የቤታቸው ዋልታና ማገር ፈርሷል፡፡ ሕጻናት ትምህርት ቤት ደርሰው ሲመለሱ የወላጆቻቸውን ፍቅርና እንክብካቤ ሲናፍቁ እንዳልነበር ከአባት ወይም ከእናት ጋር ማን እንደሚቀር የልጆች ክፍፍል ተመልሶ ለልጆች ሰቀቀን ሆነ፡፡ ቤተሰብ ይሉት ተቋም ተናደ፤ ፈረሰ፡፡ ልጆችም ተበተኑ፡፡ የሃይማኖት አባቶች ትዳር ሲፈርስ እያዩ ምንም ማድረግ የማይችሉት ነገር ገጠማቸው፡፡ የአርባ አራቱ ታቦታት ጠበል ይህን የገባ ሰይጣን ፈውስ መስጠት ተሳነው፡፡ በቃ! ቅማንትና አማራ በሚል ሰበብ የስንት ሰው ሕይወት አደጋ ላይ ወደቀ? የቤተሰብ ፍቅር እንዲህ እንዳልነበር ሲሆን ማየት በጣም የሚያም ነገር ነው፡፡

ትዳር እንዴት ይፈርስ እንደነበር ለማስረጃ ይሆን ዘንድ የአንድ ሰው ታሪክ ከዚህ ላይ መናገር ፈለግኩ፡፡ ግለሰቡ ታሪኩን ያጫወተኝ በዚህ መልክ ነበር፡፡ ‹‹አስራ ሰባት ዓመታት ከሚስቴ ጋር አብረን ስንኖር ስለ እርሷ ማንነት የማዉቀው ነገር አልነበረኝም፡፡ ሰዉነቷ ብቻ በቂዬ ነበር፡፡ እዉነቴን ነዉ የምልህ የጎንደር ልጅ ከመሆኗ ዉጭ የማዉቀው አልነበረኝም፡፡ በጋብቻችን ለአቻዎቻችን አርኣያ የምንሆን ሰዎች ነበርን፡፡ በትዳራችን 3 ልጆችን አፍርተናል፡፡ የመጀመሪያዋ ልጄ 16 ዓመቷ ነዉ፡፡ ባለፈዉ ዓመት የጥቅምት መድኃኒዓለም ሊደርስ አንድ ሳምንት ሲቀረው እናቷ ደወሉልኝና ‹ለመድኃኒዓልም ዝክር ዝግጅት ታግዘኝ ላካት› አሉኝ (አማትን አንቱ በማለት ነው የሚጠራው)፡፡ እኔም እናቷን እንድታግዝ መሔዷን በደስታ ተቀበልኩ፡፡ የጥቅምት መድኃኒዓለም አልፎ ግን ከነገ ዛሬ ትመጣለች እያልኩ ከልጆቼ ጋር ብናያት የዉሃ ሽታ ሆነች፡፡ ስልክ ስንደዉል ስልኳን ዘግታለች፡፡ መጨረሻ ቤተሰቦቿ ካሉበት ቦታ ትክል ድንጋይ ሰዉ ተላከ፡፡ የተላኩት ሰዎች ‹ልጃችን ‹አማራ› አግብታ አትኖርም!› የሚል መልስ ተነገራቸው፡፡ አንድ ዓመት ያልሞላዉን ሕጻን ልጅ እና ሌሎቹንም ልጆቿን ትታ ለመቅረት እንደወሰነች ሰማሁ፡፡ በቄስ በሽማግሌ አስጠየቅኳት፡፡ ፈቃደኛ ልትሆን አልቻለችም፡፡ የሚገርምህ ልጆቼ ሲያድጉ ሠራተኛ አያውቁም፡፡ ሠራተኛ በዘመድ አፈላልጌ ቢያንስ ምግብ እንድታዘጋጅልን አደረግኩ፡፡ ልጆቼ ግን ሌላ ሰው የሠራውን ተመግበው ስለማያውቁ አስቸገሩኝ፡፡ ስለዚህ ምጣድ ሁሉ ሳይቀር እየጋገርኩ ልጆቼን ለማሳደግ ሞከርኩ፡፡ በዚያ ላይ ሕጻኑ ልጅ ሌሊት ላይ እማዬ እያለ ጡት ለመጥባት ፈልጎ ሲያጣት ያለቅስብኛል፡፡ ቤታችን ሁሉ ነገር ምሉእ ነበር፡፡ ግን በዚህ ምክንያት የምወዳትን ሚስቴን አጣሁ፤ ቤተሰቤም ፈረሰ›› አለኝ፡፡ ይህ ግለሰብ የነገረኝ ብዙ የሚያም ነገር አለው፡፡ ቢሆንም የጠቀስኩት ለግንዛቤ በቂ ነው፡፡

ይህ የአንድ ሰው ታሪክ ብቻ አይደለም፡፡ ሳይጠፋፉ በሰላም የተለያዩማ እድለኞች ነበሩ፡፡ በዚህ መካከል የሚያድጉ ሕጻናት በሕሊና ሊጎዱ የሚችሉትን ሳስብ አዝናለሁ፡፡ ሆኖም የደማውን ሕሊናየን የሚያክም ነገርም አገኘሁ፡፡ አሁን ላይ ‹በሁለቱም ወገን› ጎራ ከፍለው ሲናከሱ የነበሩ ሁሉ ትምህርት ወስደዋል፡፡ የችግሩ ምንጭ እነርሱ አለመሆናቸውን አምነዋል፡፡ ዛሬ ላይ የአድባር ዛፍ ሥር የተቀመጡ ነጭ ሸማ የለበሱ ሰዎችን ካያችሁ የፈረሰው ትዳር እንደገና ሲጠገን ነው፡፡ እንዳልነበር የሆነው ቤተሰብ ፍቅር በዛፉ አድባር ሲመለስ ነው፡፡ የገባው ሰይጣንም በአርባ አራቱ ታቦት ጸበል ተረጭቶ ሲወጣ ነው፡፡ አሁን ላይ ጎረቤታሞች ቡና እተጠራሩ ነው፡፡ ይህ ለእኔ ትልቅ እፎይታን ሰጥቶኛል፡፡ ከላይ የገለጽኩት ግለሰብም ከባለቤቱ ጋር ለመታረቅ ሙከራ ላይ እንዳለ ነግሮኛል፡፡ ትንሽ ቀናት ሰንብቼ ቢሆን ኖሮ የቤተሰቡን ፍቅር ሲታደስ አይቼ እንደምመጣ እርግጠኛ ነበርኩ፡፡

ከትክል ድንጋይ ወደ ታች አርማጭሆ ሳንጃ ጉዞ ቀጥያለሁ፡፡ በዚች ከተማ የማይረሳ ታሪክ አለኝ፡፡ ሳንጃ ከሁለት ዓመት በፊት አውቃታለሁ፡፡ አሁንም የተለወጠ ነገር የለም፡፡ ከሁለት ዓመት በፊት ያየኋት ሳንጃ ምንም የተቀየረችው ነገር የለም፡፡ ሙቀቷ ብቻ ትንሽ ሳያይል አልቀረም፡፡ በአካባቢው የነበረው ደንም የተመናመነ መሠለኝ፡፡ ከሁለት ዓመት በፊት ለተመሳሳይ ሥራ አሽሬ፣ ዳንሻና ሶሮቃ ደርሰን ከአንድ ወዳጄ ጋር ስንመለስ ሳንጃ ላይ መሸብን፡፡ ሳንጃ ቤርጎ ለመከራየት ስንዘዋወር አብሮኝ የነበረው ጓዴ ዩንቨርሲቲ አብሮት የተማረ የአርማጭሆ ጓደኛውን አገኘነው፡፡ ይህ የጓዴ ጓደኛ ‹‹እኛ ቤት ካልሔዳችሁ!›› ብሎ ገለገለን፡፡ ተከትለነው ሔድን፡፡ በእንግድነት ቤት እግራችን ታጥበን የሚበላውና የሚጠጣው በገፍ ቀረበልን፡፡ አልጋ ተለቆልን እንድንተኛ ቢነገረንም እንቅልፍ የማያስተኛ ነገር ገጠመን፡፡

በአርማጭሆ ደም የሚባል መጥፎ ነገር አለ፡፡ በእንግድነት የገባንበት ቤትም ደም የተቃቡ ሰዎች ነበሩ፡፡ እኛ ቤት ከመድረሳችን አንድ ሳምንት ያክል ቀደም ብሎ የጓደኛችን አያት (የአባቱን እናት) ሰው ገደላት፡፡ እንደነገሩን ከሆን በአርማጭሆ ሴት መግደል ነውር ነው፡፡ ሆኖም ግን አልፎ አልፎ እንዲህ ዓይነት ነገር መከሰቱ አይቀርም፡፡ በአርማጭሆ ሰው የተገደለበት ወገን የገዳዩን ተመሳሳይ ወገን ካልገደለ አስከሬኑ አይቀበርም፡፡ ስለዚህ በሰው የተገደለ ሰው ካለ ሌላም እንደሚጨመር መገመቱ ቀላል ነው፡፡ የገዳይ ዘመዶች በተቻላቸው መጠን ከአካባቢው ርቀው ቢሸሹም ከመገደል አይድኑም፡፡ ደም ያልመለሰ ሰው ሁልጊዜም መሰደቢያ ይሆናል፡፡ ደም መመላለስን በተመለከተ ብዙ ገራሚ ነገሮች አሉ፡፡ ሚስቱን አስረግዞ የተገደለ አባት የተወለደው ልጅ አድጎ የአባቱን ደም የመለሰበት አጋጠሚም አለ፡፡ ወንድ ልጅ ቢጠፋ በአርማጭሆ ሴት ደሟን ትመልሳለች፡፡ የአባቱን ወይም የወንድሙን አሊያም የጓደኛውን ደም የመለሰ ሰው ደመላሽ ይሰኛል፡፡ ኮረዳዎች ይገጥሙለታል፤ የዘፍን ቅኔን ይቀኙለታል፡፡ አሊያ ግን በድፍን አርማጭሆ አንገቱን ደፍቶ መኖሩ ነው፡፡ ወደ ቀደመው ነገር ስመለስ የጓደኛችን አባት የገደለበትን ሰው እናት ሳንጃ ከተማ መግቢያው አካባቢ ወንዝ ውኃ ስትቀዳ አገኛትና እዚያው ከእነተሸከመችው እንስራ አሰናበታት፡፡ ሁለቱም እናቶች ተቀበሩ፡፡ ነገር ግን ደም አይደርቅምና ቀጣዩን ሟች ከየትኛው ወገን እንደሚሆን ስለማይታወቅ ከሁለቱም ወገን መፈላለግ ጀመሩ፡፡ እኛ በእንግድነት ባህል እግራችን ታጥበን በልተንና ጠጥተን የሚመች አልጋ ላይ ተኝተን አባትና ልጅ በየተራ መሣሪያ በር ላይ ደቅነው ይጠብቁ ጀመር፡፡ መሣሪያ የያዘ ሰው ከበር ላይ ተቀምጦ እኛ እንዴት እንቅልፍ ይውሰደን? የመከራ ሌሊት ረጅም ነው እንዲሉ እኛም እንቅልፍ በዓይናችን ሳይዞር አድረን አርማጭሆን ለቀን ወጥተናል፡፡

አሁንም ድጋሚ ሳንጃ ተከስቻለሁ፡፡ ከሁለት ዓመት በፊት ያስተናገደንን የጓደኛየን ጓደኛ ሳንጃ ላይ አገኘሁት፡፡ ይህ መልካም ወዳጄ የቅማንት ቤተሰብ ልጅ መሆኑን በዚህ ዓመት ነገረኝ፡፡ በፊት ስለነበረው የደም መቀባባት ጉዳይ ሳነሳለት እያዘነ ‹‹ባለፉት ጊዜያት ደም ስትቃባ ጠብህ ከግለሰቦች ጋር ብቻ ነበር፤ አሁን ግን አንድ ሰው ከተገደለ ‹የገደለው እኮ እሱ አማራ ወይም ቅማንት ስለሆነ ነው› እየተባለ ወደ ቡድን ጠብ ይቀየራል፡፡ ብዙዎቹ ዘመዶቼ ወደ ትክል ድንጋይ ናቸው፡፡ ላይ አርማጭሆ የተያዘው ነገር እንዲህ ያለ ነው፡፡ ምን እንደሚሻል አላውቅም›› አለኝ፡፡ ወዳጄ በተፈጠረው ነገር ካዘኑ ሰዎች መካከል ነው፡፡ እርግጥ ነው ያላዘነ ሰው የለም፡፡ ነገሮች አሁንም በዚህ መልኩ መቀጠል አለመቀጠላቸውን ላነሳሁለት ጥያቄ ‹‹እርግጥ ነው አሁን መሻሻሎች አሉ፤ ብዙ ዘመዶቼ ላይ አርማጭሆ ስለሆኑ እሔዳለሁ፡፡ በጉዳዩ ላይ እንወያያለን፡፡ ይህ በሕወሓት የተፈጠረ ሴራ መድረቅ እንዳለበት ዘመዶቼ ሁሉ ያምናሉ›› የሚል መልስ ሰጠኝ፡፡

ይህ ወዳጄ በአካባቢው ያደረግኩትን ጥናት ቀና እንዲሆን ብዙ አግዞኛል፡፡ አንዳንዶቹ ነገሮች በአንድ ኢትዮጵያ በምንላት አገር እየኖርን መሆን አለመሆኑን እንድንጠይቅ ሊያደርጉን ይችላሉ፡፡ ባለፈው ዓመት በምዕራብ አርማጭሆ ግጨው በተባለው አካባቢ የቀለጠ ጦርነት ነበር፡፡ ምክንያቱ ደግሞ የሚከተለው ነው፡፡

ችግሩ ከተጠነሰሰ ስድት ዓመታት አልፈዋል፡፡ የሕወሓትን የተስፋፊነት እቅድ በአርማጭሆና ጠገዴ ከሚኖረው ሕዝብ የበለጠ የሚያውቀው የለም፡፡ ይህን የተገነዘቡ የጠገዴና የአርማጭሆ ባላባቶች በአርማጭሆ የተለያዩ አካባቢዎች የዛሬ ስድት አመት ገደማ ቀለም ይዘዉ ዛፎቹን እያቀለሙ ደንበር አበጁ፡፡ ክረምት አልፎ ክረምት ሲተካ ዛፎቹ ላይ የተቀባው ቀለምም እየጠፋ ድንበሩም እየፈረሰ ሔደ፡፡ የተወሰኑ የሕወሓት አራሾች በየዓመቱ ትንሽ ትንሽ እያለፉ ማረስ ጀመሩ፡፡ ለምን? ብለዉ የሚጠይቁ ሰዎች ሲበርክቱ የሁለቱ ክልል መንግሥታት ጣልቃ ገብተዉ ካርታ ሠሩ፡፡ በዚህ ካርታ መሠረት ግጨው በሰሜን ጎንደር ሥር አረፈ፡፡ ከዳንሻ ጀምሮ እስከ ግጨው የተዘረጋ ትልቅ የወያኔ እርሻ አለ፡፡ የትግራይ ልማት ማኅበር እርጎየ ላይ ትምህርት ቤት ሠራ፡፡ የልማት ማኅበሩ የሠራው ትምህርት ቤት ለምን እንደሆነ የተገዘበ ሰው አልነበረም፡፡ በአርማጭሆነና በጠገዴ ያሉ የብአዴን አመራር ካቢኔዎች ሆን ተብሎ ይሁን አሊያም ባጋጣሚ በእናታቸው ወይም ባባታቸው አሊያም ሙሉ በሙሉ የትግራይ ተወላጅ የሆኑ ይበዛሉ፡፡

በሰኔ 2006 ዓ.ም. የክረምት መግቢያ ላይ የሕወሓት የጦር ተመላሽ የሰሊጥ አምራቾች ግጨዉ ከተባለዉ ተራራ አልፈዉ መመንጠር ጀመሩ፡፡ የአርማጭሆና የጠገዴ ሕዝብ አይሆንም ብለዉ በኃይል አባረሯቸዉ፡፡ ከጠገዴ ወረዳ ፖሊስ ሊያጣራ አንድ ኮንስታብል ማዕረግ ያለው ሰው ተላከ፡፡ ለእርሻ የመጡትን ሰዎች የእነርሱ ቦታ አለመሆኑን ነገሮ የአካባቢውን ገበሬዎችም አረጋግቶ ተመለሰ፡፡ ወደዚህ ቦታ የተላከዉ ፖሊስ ግዳጁን ፈጽሞ ከተመለሰ በኋላ በምን እና ማን እንደገደለዉ ሳይታወቅ በአገር አማን በጥይት ተገድሎ ተገኘ፡፡

ሰሊጥ አምራቾቹ እንደገና ተመልሰዉ መጥተዉ ሰሊጥ ለመዝራት ሞከሩ፡፡ ገበሬዎችም እንደገና ለመዝራት ከመጡት ሰዎች ጋር ተጣሉ፡፡ ችገሩ እየተባባሰ በመጣበት ወቅት የወረዳው ፖሊስ አዛዥ ለዞንም ሆነ ለክልል እርዳታ ሳይጠይቅ አፍኖ ያዘው፡፡ የፖሊስ አዛዡ ችግር ወደተፈጠረበት የሚሔዱ ጓዶቹን በግጭቱ መካከል ገብተው እነርሱ ላይ ለሚደርስ ጉዳት ሁሉ ኃላፊነት እንደማይወስድ አስጠንቅቆ ላካቸው፤ በርቀት ቆመዉ እንዲታዘቡ እንጅ ገብተዉ እንዲገላግሉ የፈለገ አይመስልም፡፡

ችገሩ እየጠነከረ ሲሔድ የሚገደሉ ሰዎችም ቁጥር ጨመረ፡፡ የፖሊስ አዛዡ ለአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን በስልክ አሳወቀ፡፡ ግን ይፋ ጦርነቱ ተጀመሮ ነበር፡፡ የትግራይና የአማራ ተወላጆች በየጎራቸዉ ተሰለፉ፡፡ የሰሜን ጎንደር ዞን የአማራ አድማ በታኝ ፖሊስ ላከ፡፡ የትግራይ ክልል ልዩ ኃይልና አድማ በታኝ ፖሊሶች የሲቪል ልብስ ለብሰው ግን ደግሞ እስከ አፍንጫቸዉ ታጥቀው ወደ ጦርነት ገቡ፡፡ በሲቪል ሰዎች መካከል የተደረገ ግጭት ለማስመሰል የታቀደ መሆኑ ነው፡፡ ግጨዉ ተራራ በአንድ ቀን ዉስጥ ወደ ጦር ሜዳነት ተቀየረች፡፡ ከሳንጃና ትክል ድንጋይ ብዙ ወጣቶች ወደ ግጭው ሲሔዱ መንገዱ ተዘጋ፡፡ ለቀናት ከጎንደር ኹመራ የመኪና መንገድ አገልግሎት መስጠት አቋረጠ፡፡ ምርኮ ሁሉ ነበረ፡፡ ይህ ሁሉ ነገር ከተፈጸመ በኋላ በሽምግልና ግጭቱ በረደ፡፡ ሕወሓት በወልቃይና በጠገዴ የተነሳውን እንቅስቃሴ ለማፈን እንዲያውም ግዛቴ ከዚህም የሰፋ ነው የሚል አስተሳሰብ ለመፍጠር ያደረገው ይመስላል፡፡

የፌደራል መንግሥት የሚያሠራው ከኹመራ ተነስቶ በማይካድራና አብደራፊ አልፎ መተማ የሚገባ መንገድ አለ፡፡ መንገዱን የያዘው ሱር የተባለ ኮንስትራክሽን ነው፡፡ በአቶ አባይ ወልዱ ትእዛዝ ከማይካድራ ቀጥታ ወደ ሱዳን ታጥፎ እንዲሠራ ይደረጋል፡፡ አቻቸው አቶ ገዱ ደግሞ የአቶ አባይን ትእዛዝ ጥሰው ወደ መተማ እንዲሠራ አደረጉት፡፡ አቶ ገዱ በምዕራብ አርማጭሆ የሚመረተውን ሰሊጥ ወደ ትግራይ ክልል እንዳይሔድ አብራጂራ ላይ ኬላ ተክለው የኢትዮጵያ የእህል ንግድ ድርጅትም እዚያው ቅርንጫፍ ጽ/ቤት እንዲከፍቱ በማስደረጋቸው በአካባቢው ስማቸውን ለመገንባት ጥረዋል፡፡ ብአዴን ለአማራው ሕዝብ የአህያ ባል እንደሆነ ማንም እያወቀ አካባቢው በአቶ ገዱ ላይ የጣለው እምነት ጉድ እንዳይሠራቸው እሰጋለሁ፡፡

ድንበር ጠባቂው ባሻ ጥጋቡ

በምዕራብ አርማጭሆ እጅግ ሰፊ የሆነና ለም መሬት በሱዳን መንግሥት ቁጥጥር ሥር መሆኑን በተለያየ የአርማጭሆ አካባቢዎች የሚኖሩ ብዙ ሰዎች ነግረውኛል፡፡ በዚህ አካባቢ የነበሩ ቦታዎች ሁሉ አረብኛ ትርጓሜም እየተሰጣቸው ነው፡፡ በእርግጥ ቀደም ባሉት ጊዜያትም ቢሆን ብዙ ቦታዎች የአረብኛ ትርጓሜ ያላቸው አሉ፡፡ ለምሳሌ አብደራፈፊ የሚባለው ከተማ ስያሜ ‹አብደላ ፊ› ከሚል ከአረብኛ ቃል የተገኘ ሲሆን ትርጓሜውም ‹አብደላ አለ› የሚል ነው፡፡ ያ ማለት ግን አካባቢው የሱዳን ነው ወይም ነበረ ማለት አይደለም፡፡ ሕዝቡ አረብኛን አቀላጥፎ ይናገራል፡፡ የሆነው ሆኖ በርካታ ኪሎ ሜትሮችን የሚሸፍን ከ2000 ዓ.ም. በፊት በእኛ ገበሬዎች እጅ የነበረ መሬት አሁን እዚህ የለም፡፡ ሕዝቡም በሥጋት ሌሎች የተረፉ ድንበር ላይ ያሉ አረብኛ ሥያሜ የነበራቸውን ቦታዎች ሁሉ ወደ አማርኛ እየቀየራቸው ነው፡፡ ለምሳሌ ያክል ቀድሞ ‹ኮር ኹመር› ትባል የነበረችው ትንሽ መንደር አሁን ‹ጠፈረ ወርቅ› ተብላለች፡፡

አሁን የባሻ ጥጋቡን ጉዳይ እናንሳ፡፡ ባሻ ጥጋቡ በሱዳን የገዳሪፍ ግዛት ስሙ የናኘ ነበር፡፡ ባሻ ጥጋቡ ለተበደለ ሰው የሚቆምና በኃይለኛነቱ የሚፈራ የራሱ ሚሊሻዎች የነበሩት አንድ ግለሰብ ነው፡፡ እንዲያውም ሱዳኖች ‹ባሻ ጥጋቡ ይቅር እንጅ መለስስ ይመጣ› ይሉ እንደነበር ይወራል፡፡ ድፍን አርማጭሆ ፍትሕ ሲጎድልበት የሚያመለክተው ለምዕራብ አርማጭሆ ፖሊስ አሊያም አስተዳደር ጽ/ቤት አልነበረም፤ ለባሻ ጥጋቡ እንጅ፡፡ ባሻ ጥጋቡ በደል ያደረሰውን ሰው ወዲያውኑ እንዲያስተካከል የፍትሕ ርትእትን ያስጠብቃል፡፡ የሱዳን መንግሥት ለም የሆነውን የአርማጭሆ መሬት በወሰደ ጊዜ የባሻ ጥጋቡን መሬት ማንም ሊደፍረው አልቻለም፡፡ እንደሚባለው የባሻን መሬት አልፈው ሱዳኖች ወደ መሐል ሲገቡ መካከል ላይ የባሻ መሬት ይገኛል፡፡ ሆኖም ሰው ሆኖ ከሞት የሚያመልጥ የለምና ይህ ጀግና በ2005 ዓ.ም. ታሞ ከዚህ ዓለም ተለየ (እርግጥ ነው ለሕክምና አዲስ አበባ በሔደበት ወቅት ሆን ተብሎ ተገድሏል የሚባል ሐሜትም አለ)፡፡

የባሻ ጥጋቡ ተዝካር እለት አንድም የአርማጭሆ ሰው አልተጠራም፤ ነገር ግን አንድም የአርማጭሆ ሰው የቀረ የለም፡፡ ሕዝቡ አዘነ፤ ተዝካሩን ተረባርቦ አወጣ፡፡ የባሻ ጥጋቡን መሞት የሰሙ ሱዳናውያን የባሻን የእርሻ መሬት ለመቀማት ካምፑን ወረሩት፡፡ በዚህ ጊዜ የሚገርም ነገር ተከሰተ፡፡ አንዲት መነኩሴ ቆቧን ጥላ ክለሽ አንግባ ‹‹ገና ለገና ባሻ ሞቷል ተብሎ ርስቱ ሊደፈር ነው?›› በማለት ለጦርነት ሔደች፡፡

አብራጂራ የነበረውን የመለስ ቢል ቦርድ የአርማጭሆ ሰው አውርዶ በምትኩ ‹‹ባሻ ጥጋቡ ሆይ ራዕይህን እናስቀጥላለን!› የሚል ጥቅስ ጽፎ ሰቀለበት፡፡ ይህ ተረት ተረት ሳይሆን ትናንት የተፈጸመ እውነታ ነው፡፡

ከአርማጭሆ ወደ ጎንደር እየተመለስኩ ነው፡፡

የሚቀጥል…

የኢትዮ ሱዳን ድንበርን ለማጣራት ያደረግኩት ድካምና ውጤት

By Muluken Tesfaw

የኢትዮ ሱዳን ድንበርን ለማጣራት ያደረግኩት ድካምና ውጤት

ክፍል ፩

የካቲት 24 ቀን 2008 ዓ.ም. ጎንደር ከተማ አደርኩ፡፡ እራት ላይ ‹ትእቢት› የሚባል ምግብ በልቼ ተሰቃይቻለሁ፡፡ ነገሩ እንዲህ ነው፡፡ ናይል ሆቴል ከአንድ የቀዬ ወዳጄ ጋር ሒደን ራት ስናዝዝ ‹የቤቱ ምርጥ ዛሬ ምንድን ነው?›› አልናት አስተናጋጇን፡፡ ‹‹ትእቢት ይምጣላችሁ›› አለችን፡፡ በስሙ እየተገረምን ምግቡ ምን ዓይነት ይሆን ይሆን? እያለን የሚጠጣ አዘዝን፡፡ ‹ምኒልክ› በጎንደር የድራፍት መጠጫ ሆኖ አገኘሁት፡፡ የምኒልክ ብርጭቆ ስለተመቸን ነው መሠል ደጋግመን ተጎነጨን፡፡ የምር በምኒልክ ጃምቦ መጠጣት ደስ ይላል፡፡ ምግቡ መጣ፡፡ መመገብ ጀመርን፡፡ በአጭሩ ምግቡ የሚጣፍጥ ነገር ግን የሚያሰቃይ ነው፡፡ የተፈጨው ሥጋ በበርበሬ ተለውሶ ከዚያ ላይ ቃሪያ (ቄጦ) ታክሎበት የሚጣፍጥ ሆኖ ነው የቀረበ፡፡ እንዳንበላ ያቃጥላል፤ እንዳንተወው ይጣፍጣል፡፡ ደጋግሜ በጎርስኩ ቁጥር በፊቴ ላይ ላቨት መንቆርቆር ጀመረ፡፡ ምግቡ እልክ ያስይዛል፡፡ በላይ በላዩ በምሊክ ድራፍቱን ባንቆረቁርበትም ሊበርድ የሚችል አልሆነም፡፡ እንዳሉትም ትእቢት ያራግፋል፡፡ የሆነው ሆኖ እንዲህ ያለውን ምግብ የጤና ጥበቃ ቢከለክለው የሚል ሐሳብ አለኝ፡፡ የሆቴሉ ባለንብረቶች አንድ ቀን አንድ አቅመ ደካማ ሰው እንዳያሸልብባቸው እሰጋለሁ፡፡

የካቲት 25 ቀን 2008 ዓ.ም. ወደ መተማ ማልጄ ወጣሁ፡፡ እግረ መንገዴን ባለፉት ወራት ከቅማንት የማንነት ጥያቄ ጋር በተያያዘ የደረሰውን ጉዳት ለማጣራት አሰብኩና እያቆራረጥኩ መጓዝን መረጥኩ፡፡ ከጎንደር ጭልጋ፣ ሰራባ፣ ነጋዴ ባህር፣ ገንዳ ውኃና መተማ በየተራ እያረፍኩ ጉዞ ጀመርኩ፡፡ በየቦታው የተወሰኑ ሰዎችን ለማነጋገር ሞክሬያለሁ፡፡ ሁሉም ግን የሚሰጡኝ መረጃ የተቀራረበ ነው፡፡ ከቅማንት የማንነት ደጋፊዎች ጋር ባደረግኩት ሁሉ አብዛኛዎቹ ብአዴን ሆን ብሎ ቅማንቶችን በወታደር አስጨፍጭፏል የሚል ቅሬታ ይቀርባል፡፡ የሚነግሩኝን ከመስማት ውጭ ምን ያክል እውነት እንደሆነ ማረጋገጥ አልቻልኩም፡፡

ከመተማና ጭልጋ ወረዳዎች ያሉ አንዳንድ ሲቪል ሠራተኞች የነገሩኝ በጣም አስደንቆኛል፡፡ ከባድ ሆኖ ያገኘሁት ነገር ቢኖር ከሰው ጋር በቀላሉ ግንኙነት መመስረት ነው፡፡ ማንም ሰው ማንንም አያምንም፡፡ መንግሥትን ብታማም ብታሞግስም የወያኔ ሰላይ ነው ተብሎ ይታሰባል፡፡ እንዲሁ ማኅበራዊ ነገሮችን ለማውራት ደግሞ ቶሎ ወደ ወቅታዊ ጉዳዮች ሊገባ የሚችል ሰው የለም፡፡ በዚህ ምክንያት ጥናቴን አስቸጋሪ አድርጎብኝ ነበር፡፡ ከተጓዦች አሊያም ምግብና ካፌ ላይ ከሚጠቀሙ ሰዎች ጋር ግንኙነት ለመመስረት አስቸጋሪ መሆኑን መግለጽ በቂ ነው፡፡

ባለፈው የቅማንት የማንነት ጥያቄን ምክንያት በማድረግ የብዙ ሰዎች ሕይወት አልፏል፡፡ የሚያሳዝነው ጎረቤት ከጎረቤት ተገዳድለዋል፡፡ ባልና ሚስት በተኙበት በጩቤ ተወጋግተዋል፡፡ እያንዳንዱ የሆነው ነገር ሁሉ እጅግ የሚያሳዝንም የሚያስተክዝም ነገር ነው፡፡ አንድ ቋንቋ እያወሩ፣ አንድ እምነት እየተከተሉ አብረው አድገው፣ ተዋልደውና ከብደው እርስ በእርስ ለመተራረድ ከመፈላለግ በላይ አሳዛኝ ነገር የለም፡፡ ብዙ ቤቶችና በአውድማ ላይ ያለ ምርት በቃጠሎ ወድሟል፡፡ ለሺህ ዓመታት አብሮ የኖረ ሕዝብ እንዴት እንዲህ ሊሆን እንደቻለ እንቆቅልሽ ነው፡፡ ማንም እንግዳ ሰው ከዚያ አካባቢ ቢሔድ ያለውን ልዩነት ማሳዬት እንደማይችል በእርግጠኛነት መናገር ይቻላል፡፡ ታዲያ ለምን ይህ ሆነ? ብለን ስንጠይቅ ነዋሪውም ሆነ አመራሩ ተጠያቂ የሚያደርገው ሕወሓትን ነው፡፡ ሕወሓት በወልቃይትና ጠገዴ የተነሳውን ተቃውሞ ለማፈን የፈጠረው ብሎም የቅማንት ሕዝብ የአርማጭሆን፣ የቋራን፣ የደንቢያንና የወገራን በከፊልና ሙሉ አካባቢዎችን በመያዝ አዲስ ማንነት ከፈጠረ በወልቃይት የተጀመረው የመስፋት (ታላቅ የመሆን) ምኞት ለማስፈጸም እንደሆነ ሁሉም ሰው ይናገራል፡፡ ባለፉት ዓመታት የታችና ምዕራብ አርማጭሆን አካባቢዎች ወደ ትግራይ ለመጠቅለል ሰሊጥ ለማምረት የመጡት የሕወሓት ሰዎች የፊርማ ማሰባሰብ ሥራ ጀምረው እንደነበር ያስታውሳሉ፡፡ ጎንደር ላይ ትምህርት በትግርኛ እንዲሰጥ ጥያቄ ቀርቦ እንደነበር ሁሉ ከሕጻን እስከ አዋቂ የሚያውቀው ነው፡፡

ባለፉት ወራት በነበረው የእርስ በእርስ ግጭት የተፈጠረው እጅግ የሚያሳዝን ነው፡፡ ከላይ የገለጽኩት አዲስ ያልኩት መረጃ የሚከተለው ነው፡፡ ከብዙ የማኅበረሰቡ ክፍሎች ብሎም ከአመራሮች ለማረጋገጥ ሞክሬያለሁ፡፡ የተባለውን እውነት ነው ለማለት ግን እኔ አላየሁትም፤ የተነገረኝ ግን ይህ ነው፡፡ ግጭቱ ሊፈጠር ጥቂት ቀናት ሲቀሩት ከትግራይ ክልል በሽተኛን በሚያመላልስ አምቡላንስ መትረጊስ ተጭኖ ወደ ጭልጋ ገባ፡፡ መትረጊሱ በአምቡላንስ የመጣበት ምክንያትም አምቡላንስ ስለማይፈተሸ ነው፡፡ አንዲት የጀበና ቡና በማፍላት የምትተዳደር ሴት እጅግ በርካታ መጠን ያለው ገንዘብ በጉንፏ (በልብሷ ደብቃ) ይዛ መግባቷን ሁሉ በድፍን ጎንደር ይወራል፡፡ የመጣው መትረጊስ በርካታ ዜጎችን መቅጠፉ ያሳዝናል፡፡ በተለይ ደግሞ የተጨራረሰው በአንድ ሕዝብ መካከል ልዩነት ለመፍጠር መሆኑን ማወቅ ለአእምሮ ሰላም አይሰጥም፡፡ ይህ ሁሉ እንግዲህ የተደረገው ጎንደሬን እርስ በእርሱ ለማጫረስ በሕወሓት የተሸረበ ሴራ መሆኑ ነው፡፡ ይህን መረጃ አንድ ሕጻን ልጅም፣ አዛውንትም፣ ተራ ተቀጣሪ ሠራተኛም፣ ካቢነውም የሚያወሩት ነው፡፡ አሁን ላይ ሕዝቡ ወደ ቀደመው አንድነቱ የተመለሰ ይመስላል፡፡ በሁለቱም ወገን ማን እያፋጃቸው እንደሆነ ግንዛቤ እንደወሰዱ ያወራሉ፡፡ ብስለት የሚመጣው ዘግይቶ ሆነና የሞቱት ሰዎችን ሕይወትና የጠፋውን ንብረት ማስመለስ አልተቻለም፡፡ ለወደፊትም ይህ እንዳይደገም ስምምነት መኖሩ የሚያስደስት ነው፡፡

ከጎንደር እስከ መተማ ድረስ በየቦታው የወዳደቁ መኪናዎች ይበዛሉ፡፡ ይደንቃል፤ በመኪና አደጋ የሚረግፈውን የአገሬ ዜጋ ሳስብ አዘንኩ፡፡ በአማካይ በየዐሥር ኪሎ ሜትር የተጋጩ መኪናዎችን ወይም መስመር ወጥቶ የተከሰከሰ ተሸከርካሪን ማዬት ይገርማል፡፡ ከጎን የተቀመጡትን ስጠይቅ ‹ይህ ትናንት ነው፤ ዐሥራ አምስት ወታደሮችን የጫነች ኦራል መኪና ከሚኒ ባስ ጋር ተጋጭታ ስትገለበጥ ሁሉም ወታደሮች አመድ ሆኑ፤ የሚኒባሱ ጋቢና ያሉት አልተረፉም፡፡ ይህ ደግሞ ከሱዳን መኪና ጋር ተላትሞ ነው፡፡ ሲኖማ ሲሔድ ጭኖ ሲመለስ ተጭኖ› የሚሉ ነገሮችን ትሰማላችሁ፡፡ ብዙ አደጋ የደረሰባቸውን ተሸከርካሪዎች ባየው ቁጥር ከጎኔ ያሉ ሰዎችን መጠየቅ ሰው ያሰለቻል ብየ ስለማስብ አንዳንዴ እኔም እየሰለቸኝ ዝም ብዬ እጓዛለሁ፡፡ የእኛ ሕይወትም ከእነዚህ እንደ አንዱ እንዳይሆን አሰጋለሁ፡፡

አካባቢው ሙቀቱ ከፍተኛ ነው፡፡ መንገዱ ዳርና ዳር በበርሃ ግራሮች የተሸፈነ ነው፡፡ በርቀት ግራሮቹን ሲያዩያቸው ነጫጭ ወፎች ያረፉባቸው ነው የሚመስሉት፡፡ ምንድን ነው? ብዬ ስጠይቅ ጥጥ የጫኑ መኪናዎች ሲመጡ ጥጡን ዛፎቹ ስለሚያስቀሩት ግራሮቹ በሙሉ ጥጥ አባዛች (ደዋሪ) ሆነዋል፡፡ መተማ ከተማ ወረድኩና ምሳ በላሁ፡፡ ወደ ጋላቫት እስከ ዐሥራ አንድ ሠዓት ድረስ መግባት ይቻላል፡፡ ጋላቫት ማለት ብዙ ኢትዮጵያውያን የሚነግዱባት የሱዳን ከተማ ነች፡፡ መተማ ማለት ደግሞ ብዙ ሱዳናዉያን የሚሰክሩባት የኢትዮጵያ ከተማ ነች፡፡ ጋላቫት ብዙ የአገራችን ሴቶች በረንዳ ላይ ቡና እያፈሉ ገላቸውንም ጭምር የሚሸጡ አሉ፡፡ ሕገ ወጥ የሰዎች ዝውውር በአካባቢው የበዛ በመሆኑ ብዙ ዓይነት ቋንቋ ተናጋሪ ሴተኛ አዳሪዎች አሉ፡፡ አዘዋዋሪ ደላላዎቹ ካርቱም አሊያም ሊቪያ እናደርሳችኋለን ወደ ኢጣሊያም በቀላሉ ትገባላችሁ እያሉ ገንዘባቸውን ከወሰዱባቸው በኋላ እንጣጥ ፍርጥ እያሉ ከአንዱም ሳይሆኑ ሴተኛ አዳሪ ብቻ ሆነው ይቀራሉ፡፡ የሱዳን ሲም ካርድ ይገዙና ቤተሰቦቻቸውን በሱዳን ሞቫይል በመደወል መተማ ተቀምጠው ካርቱም ነው ያለሁት እያሉ የሚደልሉ ሞኞችም ሞልተዋል፡፡
እንደሰማሁት ከሆነ በሕገ ወጥ የሰዎች ዝውውሩ አንዳንድ ቱባ የመንግስት ባለሥልናትና የፌደራል ፓሊስ አባላት አሉበት፡፡ ደላላዎቹ ወደ ሱዳን ለመሻገር የመጣን ሰው በቀላሉ የሚለዩበት ክሕሎት የሚገርም ነው፡፡ የድንበር ከተማ ከመሆኑ አንጻር ብዙ አዳዲስ ሰዎች ማየት የሚደንቅ አይደለም፡፡ ነገር ግን አዲስ መተማ ከሚደርሱ ሰዎች መካከል የትኛው ወደ ሱዳን እንደሚሰደድ አሊያም ለኮንትሮቫንድ ንግድ እንደመጣ ማወቅ ለደላላዎቹ ምንም ያክል አይከብድም፡፡ በደላላ እጅ የገባች ተሰዳጅ ደላላው በፈለገው ነገር ያሳምናታል፡፡ ለደላላዎች የእራሳቸውን ሽያጭ ዋጋ ከከፈሉ በኋላ ያሰቡበት ቦታ ሳይደርሱ ከኮሚሽን ተካፋይ ባልሆነ ወይም ቅሬታ በገባው የጸጥታ አካል ተይዘው መተማ ፖሊስ ጣቢያ ይታሰራሉ፡፡ እነዚህ እህቶች አንዳችም ነገር ሳያስቀሩ ለደላላው ሰጥተዋል፡፡ ደላላው ደግሞ ከዚህ በኋላ አይገኝም፡፡ ያላቸው ብቸኛው ተስፋ ራሳቸውን መሸጥ ብቻ ይሆናል ማለት ነው፡፡ በዚህ ምክንያት ሴተኛ አዳሪ ሆነው የቀሩ እህቶች ቁጥር የትየለሌ ነው፡፡ የበርሃ ሰው የመጠጥና የሴት ነገር አይሆንለትም፡፡ የፍየል ግንባር በምታክል ከተማ ያን ያክል ሰው በዚህ መተዳደሩ ለዚህ ነው፡፡ በአናቱም ሱዳናዉያን ወደ መተማ የሚሻገሩት አንድም ቢራችንን አሊያም እህቶቻችንን ለመሸመት ነው፡፡ መጀመሪያ በገንዛ ብራቸው (ገንዘባቸው) ራሳቸውን ለደላላ የሸጡ ሴቶች ገላቸውን ቸርችረው አጠራቅመው ነገም ካርቱም አሊያም ጣሊያን ለመድረስ ተስፋን ይሰንቃሉ፡፡ የሰው ልጅ ምን ያክል ተስፈኛ መሆኑን ተገንዝቤያለሁ፡፡ ወላጆቻቸውን በውሸት ካርቱም ተቀጥሬ እየሰራሁ ነው ያለች አንዲት የጂማ ልጅ መተማ መቀመጧን ማንም እንደማያየት እርግጠኛ ስለሆነች ነው፡፡ በዚያ ላይ የሱዳን ሲም ከኢትዮ ቴሌኮም በተሻለ ኔትወርክ መሥራቱ ላይክስ አይበድል ነው፡፡ ገላቸውን ቸርችረው ትንሽ ገንዘብ ማጠራቀም የቻሉ ሴቶችም ወደ ኢትዮጵያ የሚመጣ ሰው አግኝቻለሁና ከጎንደር በባንክ ይልክላችኋል ብለው ለቤተሰቦቻቸው በመንገር በሌላ ሰው ስም መተማ ባሉ ባንኮች የሚልኩ አሉ፡፡

ሳስበው አገራችንን ጥለን ለመሔድ ራሳችንን ክደን ክብራችንን አውልቀን የጣልንበት ጉድጓድ ጥልቀት ይገርመኛል፡፡ በአገራችን ሰርተን መለወጥ እንዳንችል ያደረገን ነገር ምንድን ነው? ኢትዮጵያዊነታችን አውልቀን ለመጣል ያስገደደን ምክንያቱ ከቶ ምን ይሆን? እነዚህ ጥያቄዎች ሁልጊዜም አብረውኝ የሚጓዙ ናቸው፡፡ ገንዘብ እንዳንል አንዲት እህት ከተወለደችበት ተነስታ ጣሊያን ወይም የመን ለመድረስ በአማካይ ከ20 እስከ 30 ሺህ ብር ያስፈልጋታል፡፡ ይህንን ብርም ወላጅና አሳዳጊ ከየትም ከየትም ሰብስቦ ተሰድዳ ነገ ለምታሳልፍለት ልጁ ይሰጣል፡፡ ሴትነት በራሱ ፈተና ነው፡፡ በየመንገዱ እየተደፈሩ ከጋላቫት ገዳሪፍ ካርቱም ለመግባት ብቻ ቀናትን በበርሃ መጓዝ ይጠበቅባቸዋል፡፡ ከዚያ በኋላ እንደገና የሱዳን ደላሎች የመንግሥት ጥበቃ ልል በሆነባቸው የግብጽና የቻድ በርሃዎችን አቆራርጠው ወደ ሊቪያ ይገባሉ፡፡ በበርሃ አካላቶቻቸው እየተበለቱም የሚሸጡባቸው ሰዎች አሉ፡፡ ኩላሊትን የመሠለ አካል አንደኛው መገኛ ቦታው የግብጽ፣ የቻድና የሊቪያ በርሃ ነው፡፡ ከሊቪያ እንደገና ወደ ደቡባዊ ጣሊያን ለመሻገር የሜዲትራኒያን ባህርን ከሻርክ ጋር ታግለው ማለፍ ይጠበቅባቸዋል፤ ሌላም ሌላም፡፡

ታዲያ የአገሬ ዜጎች በዚህ መልኩ ከሞት ጋር ግብግብ እየገጠሙ ስለምን ይሰደዳሉ? ያልን እንደሆነ መልሱ ነጻነትን ፍለጋ ነው፡፡ ነጻነትን ያጣው ፖለቲከኛ አሊያም ጋዜጠኛ ብቻ አይመስለኝም፡፡ ይህ ቢሆንማ ኖሮ ሁላችንም ጋዜጠኛነቱን አሊያም ፖለቲከኛነቱን ትተን ነጻነታችን ባወጀን ነበር፡፡ በእኛ ምድር ሰው በነጻነት መኖር፣ መስራት አይችልም፡፡ ይህም ብዙዎቻችንን ከሞት ጋር እንድንጋፈጥ አድርጎናል፡፡ መልኣከ ሞት ፊታችን ቆሞ እያየን ኢትዮጵያ ያለው ጭቆናና ባርነት ከፊታችን ከቆመው መልኣከ ሞት የበለጠ ስለሚሆንብን አገራችን ትተን እንሰደዳለን፡፡ ከንአንን የመሰለች አገር እያለችን በባዕዳን መሸጥን መምረጥ በእውነት መረገም ነው፡፡ እርገመቱስ መቼ ይሆን የሚለቀን?

ጋላቫት ከአበሻ ሴቶች ጋር ቡና በዐሥር ብር ገዛሁ፡፡ ከላይ የገለጥኩትን የስደተኞች ጉዳይ በዝርዝር ያጫወቱኝ እነዚሁ አንስቶች ናቸው፡፡ ቡና ለመጠጣት ቁጭ ባልኩበት ሰዓት እንኳ ከዳሚዋን ልጅ ስንት ሱዳን መጥቶ እንደወደቀባት ያየሁት ምስክር ነኝ፡፡ አንደኛው ሲያልፍ ይቆነጥጣታል፤ ሌላኛው ሲመጣ ጡቷ አካባቢ ሆን ብሎ ይነካታል፤ ሌላኛው መቀመጫዋ ላይ፡፡ እርሷ ለሁሉም ትስቃለች፡፡ ለሁሉም የፈላጊነት ስሜት ታሳያለች፡፡ የእኛ እህቶች ኑሮ ይህ ነው በመተማና በጋላቫት፡፡ ወደ ቋራ መሔድ ስለነበረብኝ ሒሳብ ከፍየ ተነሳሁ፡፡ ደረቴ ላይ በጣም የሚያቃጥል ስሜት ተሰማኝ፡፡ ለካስ አንገቴ ላይ ያለው ሐብል ግሎ በእሳት የተጠበሰ ብረት ሆኗል፡፡ በእጄ አነሳሁት አቃጠለኝ፡፡ የሚገርም ነው፡፡ በአካባቢው ጸሀይ ከአናት አንድ ሜትር ከፍታ ያላት ነው የሚመስለው፡፡ ብዙ ሰዎች ራቁታቸውን መሆን ይወዳሉ፡፡ ሽፍን ጫማና ጥቁር ቲሸርት በመልበሴ እንግዳ እንደሆንኩ በቀላሉ እለያለሁ፡፡ ፀሀይ ገና በማለዳ ይህን ያክል ኃይል ካለት ከተሲያት ምን እንደምትሆን ማሰብ ይቻላል፡፡

መተማ ዮሐንስ ገባሁ፡፡ ይህ ቦታ አጼ ዮሐንስ ከድርቡሾች ጋር ሲዋጉ ሕይወታቸው ያለፈበት ነው፡፡ በኒም (በብዛት ያለ ዛፍ) ዛፎች የተሸፈነውን የመተማ ዮሐንስ ቤተ ክርስቲያን ተሳልሜ ከዛፎቹ ሥር ትንሽ ተቀመጥኩ፡፡ ከሁለት ሳምንት በፊት ፕሮፌሰር መስፍንን በድንበር ጉዳይ ስጠይቃቸው ‹ስለምን አንድ ቁርጠኛ ሰው ጂፒኤስ ይዞ በመሔድ ትክክለኛ ካርታው የት ላይ እንደሚያርፍ አያረጋግጠም?› የሚል መልስ ሰጥተውኝ ነበር፡፡ የእሳቸው መልስ ይህን እንድወስን ሳያደርገኝ አልቀረም፡፡ ጎግል ማፔን ከፍቼ የት ላይ እንዳለሁ ለማረጋገጥ ሙከራ አደረግኩ፡፡ ምንም እንኳ ያለኝ የካርታ እውቀት ውስን ቢሆንም ጎግል ያለሁበት ቦታ (ከረንት ሎኬሽን) ከሱዳን ድንበር ትንሽ ሜትሮችን ራቅ ብዬ እንደሆነ ነገረኝ፡፡ እርግጥ ነው ይህ ቦታ አሁንም ድሮም የአገራችን ነው፡፡ ይህ ትክክል ከሆነ የት ቦታ ላይ ሊሆን ይችላል ወደ ሱዳን የተካለለ? የሚለውን ጥያቄ መመለስ ግድ ይለኝ ነበር፡፡ የጀበና ቡና እና ጫት ደባልቀው ወደሚጠቀሙ ወጣቶች ተደባልቄ ወሬ ጀመርኩ፡፡ ጥርጣሬ በማይፈጥር መልኩ የድንበርን ጉዳይ ለማንሳት ሞከርኩ፡፡ በአጭሩ በዚያ ማኅበር የተነሳው ሐሳብ የሚያስረዳው እንደመተማ ያሉ ታዋቂ ከተሞች ወደፊትም እንደማይነኩ ነገር ግን ሰው ያልሰፈረባቸው ጥቅጥ ጫካዎች በተለያየ ጊዜ ወደ ሱዳን እየተካለሉ እንደሆነ ፍንጭ ሰጡኝ፡፡ ስለዚህ ተወደድም ተጠላም ከመተማ ወደ ሰሜንና ደቡብ የቋራና የአርማጭሆ ጫካዎች መፈተሸ ይኖርባቸዋል ማለት ነው፡፡

ቋራ ለመሔድ ወደ ሸኽዲ ከተማ ተመለስኩ፡፡ ሸኽዲ ከተማ ከመተማ 30 ኪሎ ሜትሮችን ያክል ወደ ጎንደር መስመር ትገባለች፡፡ ከተማዋ መሐል አስፓልት ላይ ቆመው የሚያድሩ ወይም የሚውሉ መኪናዎች ብዙዎቹ ነዳጅ ጫኝ ናቸው፡፡ አንድ መኪና ላይ የእሳት አደጋ ቢከሰት ያ ሁሉ ነዳጅ የተሸከመ መኪና ብቻ ሳይሆን ከተማዋም እንዳለ ልትጠፋ ትችላለች፡፡ በነገራችን ላይ ይህ የእኔ ብቻ ሳይሆን የከተማዋ ነዋሪም ስጋት እንደሆነ ለማረጋገጥ ሞክሬያለሁ፡፡ የገንዳ ውሃን እንደተሻገርን አንድ ቦቲ ተቃጥሎ የመንደሯን አብዛኛዎቹን ቤቶች እሳቱ ላፍ አድርጓቸዋል፡፡ መኪና መንገዱም በመዘጋቱ በቅያሬ ነው የሔድነው፡፡ እዚህ ላይ ሌላ የገረመኝ ነገር የኮንትሮ ባንድ ነጋዴዎች ጉዳይ ነው፡፡ ከጋላቫት በርካታ ነገሮች በእርካሽ ዋጋ ይገዛሉ፡፡ የልብስ ማጠቢያ ሳሙና (ኦሞ) በኪሎ ግራም፣ ጫማ፣ የመኝታ ልብሶች፣ ጥይትና ሌሎችም የደራ ገበያ አላቸው፡፡ መተማ ጉምሩክ ዘመድ ያላቸው ሰዎች በቀላሉ ያልፋሉ፡፡ ዘመድ የሌላቸው ደግሞ አንድም የመተማ ጉምሩክ ኬላን አሊያም የመተማ በርሃን አታለው ማለፍ ይጠበቅባቸዋል፡፡ ሁለቱም ቀላል አይደሉምና ዋጋ ያስከፍላሉ፡፡ አስቀድመው በስልክ የሚሰጡትን ኮሚሽን (?) ተደራድረው ያለምንም ፍተሻ የሚያልፉት ብዙ ናቸው፡፡ ያም ሆኖ ግን ሸኽዲ ከሚገኘው የመተማ ጉምሩክ ኬላ ላይ ንብረታቸውን ተቀምተው የሚያለቅሱ ሰዎች አይታጡም፡፡ ጉምሩክ ሠራተኞቹ አንዳንድ ጊዜ ከኮንትሮ ባንድ ነጋዴዎች ላይ ግማሹን ወስደው መካዝን ሳያስገቡ ያስቀምጡታል፡፡ ያ የግላቸው መሆኑ ነው፡፡ ወደ መካዘን ለምን አይገባምና ደረሰኝ አልትሰጠኝም ብሎ የሚከራከር ንብረቱ የተወሰደበት ግለሰብ ሙሉን ሊቀማ ይችላል፡፡ የሚፈትሸው ሰው እንደሚወስደው እያወቁ ሁሉንም ከማስዘረፍ ብለው ብዙዎች ይተዋሉ፡፡ አንዳንዶች ብልጥ ነጋዴዎች ደግሞ መኪና ውስጥ ላለው ሰው ያከፋፍሉና የእኔ ነው በሉ ይላሉ፡፡ ይህም አንድ ሰው አንድ ዓይነት እቃ በቁጥር ይዞ መንቀሳቀስ ስለሚችል ከመዘረፍ ይድናሉ፡፡

ጥይት ወደ ጎንደር የሚገባበት መንገድ አስገርሞኛል፡፡ የጠርሙሱ ስፕራይት ለስላሳ (ሱዳኖች እስቲም ይሉታል) ቀለሙ አረንጓዴ ነው፡፡ ስቲሙን የተወሰነ በመጠጣት አሊያም በመድፋት ካጎደሉት በኋላ ብዙ ጥይት ወደ ላስቲኩ ይጨመራል፡፡ ከዚያም ጥይት የሚነግደው ግለሰብ እስቲሙን የሚጠጣ በመምሰል ወደ አፉ እያስጠጋ ጥይቶቹን ከጉምሩክ በቀላሉ ያሳልፋል፡፡ እርግጥ ይህ ዘዴ አሁን ተነቅቶበታል፡፡ በዚህ ሁሉ ዘዴ ማሳለፍ የማይችል ከሆነ ግን ከ30 ኪሎ ሜትር በላይ በጫካ ከበርሃና ከአራዊት ጋር ታግሎ ሸኸዲን ማለፍ ይጠበቅበታል፡፡ ሌላም አማራጭ አለ፡፡ ከሸኽዲ መሀል ከተማ ላይ ወደ ቋራ በመታጠፍ ቢሻው በቆላ ድባ አሊያም በአቸፈር አድርጎ ማምለጥ ይችላል፡፡ በቋራ በኩል ፍተሻው ጥብቅ አይደለም፡፡ ሸኽዲ ከተማ መካከል ላይ መውረድ ቢኖርብኝም ረስቼ የጉምሩክ ኬላ ላይ ስደርስ ከተማውን ማለፌን አረጋገጥኩ፡፡ በዚህ ከመጠን በላይ በሚሞቅ ጸሀይ እንደገና እየተቃጠልኩ ወደ ኋላ ተመለስኩ፡፡ የሚገርመው ከፍተኛ ንፋስ አለ፤ ነገር ግን ንፋሱ በራሱ ፊት ይጠብሳል፡፡ ንፋስ ብርድ ሲሆን እንጅ ሲያቃጥል ያየሁት መተማ ነው፡፡ ሙቀቱ ገና በረፋድ እንዲህ ከሆነ እኩለ ቀን ላይ ምን እንደሚሆን መገመት ይቻላል፡፡

ከሸኽዲ ወደ ገለጎ ቋራ ለመሔድ መኪና ማፈላለግ ያዝኩ፡፡ የቋራና የሽንፋ ሰው በጭነት አይሱዚ እላይ ተጭኖ መሔድን ይመርጣል፡፡ ለምን እንደሆነ ስጠይቅ የመኪናው ውስጥ ሙቀት ከመጠን ያለፈ ስለሆነ ከጭነቱ እላይ መሆን የተሻለ እንደሆነ ለእኔ ለእንግዳው ነገሩኝ፡፡ እድለኛ ነኝ መሰል ወደ ቋራ ሒዳ እንደገና የምትመለስ ፒካ አገኘሁና በእርሷ ወደ ቋራ መንገድ ጀመርኩ፡፡ ሽንፋ ደርስን፡፡ ሽንፋ ከአንድ ወር በፊት ወደ አምስት ሺህ የሚጠጉ በእርስ በእርስ ግጭት የተጎዱ ተፈናቃዮች ሰፍረውበት ነበር፡፡ እዚህ አካባቢ ያለው ሙቀት መተማ ካለውም ያይላል፡፡ ንፋሱም አይንቀሳቀስም፡፡ በነገራችን ላይ መተማና ሽንፋ አካባቢ አንዳንድ ጊዜ ሰዎች በተኙበት ሊያሸልቡ ስለሚችሉ ሌሊት ላይ የአየር ሁኔታውን አይተው የፖሊስ አምቡላንስ መኪና ከእንቅልፍ ይቀሰቅሳሉ ብለውኛል፡፡ አሁን የምሔድበት አካባቢ ጫካ ብቻ ነው፡፡ የቋራ ወረዳ ኹለት ሦስተኛው የአልጣሽ ብሔራዊ ፓርክ ሲሆን ጥቅጥቅ ጫካ ብቻ ነው፡፡ ፓርኩ እኛ ከምንሔድበት መንገድ ወደ ቀኝ ገባ ብሎ ነው፡፡ ከሰሞኑ የዓለማችን ሳይንቲስቶች ከኹለት መቶ በላይ አናብስቶችን በሳትላይት አይተናል ያሉት ከዚህ ነው፡፡ ፓርኩ በሱዳን ድንበር የተዋሰነ ነው፡፡

ገለጎ (ቋራ) ስንደርስ ዘጠኝ ሰዓት አልፎ ነበር፡፡ እንደማንኛውም የሙቀት አካባቢ ከተሞች ሰዎች ሁሉ በረንዳ ላይ ከገመድ በተሰራ ወንበር ወይም አልጋ ላይ ተቀምጠው ይመገባሉ፤ ይጠጣሉ፡፡ ምንም እንኳ የወረዳው ከተማ ብገኝም የሱዳን ድንበር ካለሁበት በጣም የሚርቅ ብቻም ሳይሆን መንገዱ የራሱን መኪና ላልያዘ ሰው የሚመች አይደለም፡፡ ስለሆነም ድንበሩን በተመከተ የማቀርበው ያየሁትን ሳይሆን በቅርብ የሰማሁትን ብሎም የተቻለኝን ያክል ለማረጋገጥ የሞከርኩትን ያክል እንደሆነ አንባቢ እንዲረዳ እሻለሁ፡፡ ቋራ ላይ የሰማሁት በኋላም ሸኽዲ ያሉ የመንግሥት ሠራተኞች ያረጋገጡልኝ ነገር ቢኖር የሱዳን ወታደር ሽንፋ ወንዝ ተሻግሮ የኢትዮጵያ ድንበር ውስጥ መስፈሩን ነው (ሽንፋ ወንዝ የመተማና የቋራ ወረዳዎችን እያካለለ ከሔደ በኋላ እንደገና ለሱዳንና ለኢትዮጵያ ድንበር ይሆናል፡፡ የኢትዮጵያ ድንበር ሆኖ የአላጣሽ ፓርክን እየከለለ በመጨረሻም በበርሃ ሰርጎ ይቀራል እንጅ ከአባይ አይጨመርም አሊያም ሌላ ገባር የለውም፡፡ መተማና ቋራ ድንበር ያለችው ከተማ በወንዙ ስም ሽንፋ ትባላለች)፡፡ የሰፈሩበት አካባቢ ‹ሰልፈረዲ› ቀበሌ ቁጥር 3 በተባለ በርሃ ቦታ ነው፡፡ ቀድም ባሉት ጊዜያት የሱዳን ወታደሮች ቁጥር አምስት በተባለው ‹አንቶቭ ኮረብታ› ካምፕ ነበራቸው፡፡ ይህ ቦታ በአማርኛ ቁጥር 5 ተብሎ እየተጠራ የሱዳን ግዛት እንደሆነ ብዙም ግልጽ አይደለም፡፡ በዚህ አካባቢ ያሉ የሠፈራ ጣቢያዎች በቁጥር ይጠራሉ፡፡ አስቀድሞም የሱዳን ግዛት ከሆነ ቁጥር 5 ተብሎ መጠራት ላያስፈልገው ይችል ነበር፡፡ ከባዱ ነገር ከዚህ አካባቢ ሁሉም በኃይል እንጅ በሕግ የሚተዳደር ስለሌለ ቁጥር 5 ብቻም ሳይሆን የኢትዮጵያ እንደሆነች የምትታወቀው ቁጥር 3 በበርካታ ግጭቶችና የቋያ ቃጠሎ ምክንያት ሰው አልባ ናት፡፡ በዚህ ከብት የሚያረቡ ዘላኖች ብቻ ይኖራሉ፡፡ ሆኖም ግን በቅርብ ጊዜ ወዲህ ነው የሱዳን ወታደር ወደዚህች ቀበሌ የመጣው፡፡ በነገራችን ላይ የሰልፈረዲ ቀበሌ ስፋቱ ራሱን የቻለ አንድ ወረዳ ቢያንስ እንኳ ንዑስ ወረዳ ይሆናል፡፡ መተማ ወረዳን የተወካዮች ምክር ቤት ቋሚ ኮሚቴ ለጉብኝት በሔደ ጊዜ የመተማና የቋራ ሕዝብ ተወካዮች ‹‹እነዚህ የሱዳን ወታደሮች ስለምን እኛ ድንበር ውስጥ ካምፕ ሠርተው መኖር ተፈቀደላቸው?›› የሚል ጥያቄ አንስተው ነበር፡፡ የተወካዮች ምክር ቤት የመጡት ኮሚቴዎች በትክክል መልስ አልሰጡም፡፡ በገደምዳሜ ‹‹በአካባቢው ያሉ ጸረ ሰላም ኃይሎችን በጋራ ለመከላከል በእኛ ጥሪ ነው የመጡት ሆኖም የክልሉ መንግሥት እንዲወጡ እየተነጋገረ ነው›› በማለት መልሰዋል፡፡ በአካባቢው ያለን ጸረ ሰላም ኃይል ለመከላከል በሚል እኛ ድንበር ላይ የሱዳን ወታደሮች በቋራ መስፈራቸው የአካባቢው ማኅበረሰብ ላይ ቅሬታ ፈጥሯል፡፡ የሚገርመው ነገር አንድ መንግሥት ስለ አገሩ ዳር ድንበር ዴንታ በሌለበት በዚህ ጊዜ እነዚህ ነዋሪዎች ግን የሱዳን ወታደር ተሻግሮ መጥቶ ቢራ ጠጥቶ ከመሔድ በዘለለ ካምፕ መሥራታቸው የእግር እሳት ሆኖባቸዋል፡፡ ማኅበረሰቡ የሽንፋ ወንዝ እስኪሞላ ድረስ በተጠንቀቅ እየጠበቁ ነው፡፡ እንደሰማሁት ከሆነ የሱዳን ወታደር የእኛ አገር ገበሬዎች በተኩስ ከገጠሙት እየዘለለ ወደ ውኃ በመግባት በወንዝ የመወሰድ እድል ብቻ ይኖረዋል፡፡ ቆሞ እንኳ ገበሬዎችን ለመከላከል አቅም እንደሌለው ነው ያወሩኝ፡፡ ነገሩን ጠቅለል ስናደርገው በዚህ አካባቢ የሱዳን ወታደሮች እኛ ክልል ውስጥ ሰፍረዋል፡፡ የሰፈሩበት ቦታ የተሰጣቸው ይሁን አሊያም እንደተባለው ለጊዜያዊነት ብቻ ማንም አያውቅም፡፡ ነገር ግን ቁጥር 5 የተባለው አካባቢ በትክክል በሱዳን የሚተዳደር ቦታ ነው፡፡ ቀድሞ የማን ቦታ ነበር ለሚለው ጥያቄ እኔ መልስ መስጠት አልችልም፡፡

የሚቀጥል…

Hiber Radio Interview with Chairman of Ethiopia Border Committee

የኢትዮጵያ ድንበር ለሱዳን ተላልፎ ሊሰጥ ጫፍ ላይ የደረሰ ይመስላል። የአገዛዙ <<ጠቅላይ>> ሚኒስትር አቶ ሀይለማርያም ደሳለኝ ባለፈው ወር ይሄንኑ ተግባራዊ የሚያደርግ ስምምነት ካርቱም ላይ ተገኝተው ፈርመዋል። ሕወሃት በትጥቅ ትግል ወቅት ወደ ስልጣን ለመውጣትና ከወጣም በሁዋላ በዛ በኩል ለስልጣኑ የሚያሰጉት እንዳይመጡ በአገር ጥቅም እስከመደራደር፣ አሳልፎ እስከመስጠት እየሄደ ነው የሚል ጠንካራ ስሞታ ይቀርባል። አቶ ሀይለማሪያም ሰሞኑን በኢትዮጵያውያን በኩል ይሄን ሩጫቸውን በመቃወም የአገራችንን ድንበር አትስጡ የሚል ወቀሳ ለማጣጣል ከመሞከር አልፈው <<ተቆርሶ የሚሰጥ መሬት የለም>> ከማለት አልፈው ለሱዳን ጥብቅና ቆመዋል። በዚህ ጉዳይ ላይ ኢትዮጵያውያንን በማስተባበር ድንበሩ ተቆርሶ እንዳይሰጥ ላለፉት ዓመታት ድምጹን በየመድረኩ የሚያሰማው የኢትዮጵያ የድንበር ጉዳይ ኮሚቴ ምላሽ አለው ። ከአቶ አለሙ ያይኔ የኮሚቴው ሊቀመንበር ጋር ቆይታ አድርገናል።

https://youtu.be/3w-81nXaqCw

ለሱዳን ሊሰጥ ነው ስለተባለው መሬት : ጆሮ ያለው ይስማ ልብ የአለው ልብ ይበል!

By historian   Fikre Tolossa

ለሱዳን ሊሰጥ ነው ስለተባለው መሬት
—————————————————-

eprdf berber

አሁን በጎንደር አና በቤንሻንጉል አካባቢ የሜገኙት የእነ ኦሜድላና ጋምቤላ መሬቶች በአውነት የማን ናቸው? ያለጥርጥር የኢትዮጵያ ናቸው። ለምን እንደዚህ እንዳልኩ ዝቅ ብዬ አስረዳለሁ። መሬቶቹ በታሪክ የሱዳን ነበሩና ለሱዳን ይሰጡ የሚሉት የኢትዮጵያ ባለስልጣናት መሬቶቹን ለሱዳን ለመስጠት የሚያቀርቡት ምክንያት “በ በሱዳን የእንግሊዝ ቅኝ ግዛት ጊዜ የእንግሊዝ መንግሥት ተወካይ የሆነ አንድ ሻለቃ የወሰን ምልክቱን የተከለው እዛ አካባቢ ነው፤ቀድሞ አፄ ምንይልክ በዚህ ተስማምተው፥ በሁዋላ ደግሞ አፄ ኅይለሥላሴ እና ደርግም ይህን አፅድቀውታል፤” የሚል ነው። በሌላ አነጋገር፥ በታሪካዊ ምክንያት ነው። እዚህ ላይ አንድ አስቂኝ ታሪክ ታወሰኝ። አንድ እንግሊዛዊ ከሱዳን የኢትዮጵያን ድንበር ተሻግሮ የዱር እንስሳና አውሬ ለማደን በሚል ፈሊጥ ሲዘዋወር ለስለላ ነው ብለው በጠረጠሩት የሃገሬው ተወላጆች ተገሎ እዛው ተቀበረ። ታዲያ ይህን ሰበብ አድርጎ አንድ እንግሊዛዊ መኮንን (ምናልባትም እላይ የተጠቀስው እብድ ሻለቃ) ያ አካባቢ በሞላ ለእንግሊዝ መንግሥት ሊሰጥ ይገባል፤አለ። በምን ሂሳብ ተብሎ በአባ መላ (ፊታውራሪሃብተጊዮርጊስ ዲነግዴ) ተጠየቀ። አንድ የእንግሊዝ ዜጋ ሞቶ እዚህ ስለተቀበረ፤ሲል መለሰ። አባ መላም ከትከት ብለው ስቀው፥እሺ ደግ ነው፤አንድ የእንግሊዝ ዜጋ ሞቶ እዚህ ስለተቀበረ ይሄን ሁሉ መሬት ለናንተ እንሰጣችሁአለን። የአፄ ቴዎድሮስ ልጅ ልዑል ዓለማየሁ ለንደን ውስጥ ሞቶ እዛው ለንደን (ዌስትሚኒስትር አቢ) ስለተቀበረ እኛ ደግሞ ለንደንን እንረከባችሁአለን። በዚህ ከተስማማህ ውል መፈራረም እንችላለን፤ብለው አሾፉበት። ከዛ ቦታ በቅፅበት ዳብዛው ጠፋ። ስለታሪክ ካወሳን ዘንድ፥ ይሄ ዛሬ ሱዳን የተባለው ምድር ሁሉ ቢያንስ ለ 4000 ዓመታት ያህል የኢትዮጵያ ግዛት ነበር።ጥንት የሚታወቀው ኑብያ ተብሎ ነበር። ኖባ በተሰኘው የኩሽ ዘር ስም።መናገሻውም መርዌ ነበር። የዛሬ 2900 ዓመት ግን ሱዳን ይባል ጀመር። ይህ ስም የወረደው ከአፄ አክሱማይት እናት ከንግሥት ሳዶንያ ነው። እሱ በህፃንነቱ የግብፅ ፈርኦን ሆኖ እስከሚያድግ ድረስ እስዋ በ 350,000 የአማራ ሰራዊት ታጅባ ዙፋኑን እየጠበቀች በሱ ስም ግብፅን፥ ሊብያን እና የዛሬውን ሱዳን ታስተዳድር ነበር። በዚህ ምክንያት፥ ከሳሃራ በርሃ በታች የአለው ምድር በሞላ ሳዶንያ ተባለ። ቀስ በቀስ ደግሞ ሱዳን። እንዳውም ኑብያ ውስጥ የነበረው መርዌ ለዛ አካባቢ እንደ ዋና ከተማ ሆኖ ያገለግል ነበር። ቢያንስ 14 የኢትዮጵያ ሴቶች ህንደኬ በሚል ማእረግ በንግሥትነት በተከታታይ ዛሬ ሱዳን፤ ግብፅና ሊብያ የሚባሉትን ሃገሮች ለ 1000 ዐመት ያህል ገዝተዋል። ለመጨረሻ ጊዜ የኑብያ ንጉሥ የነበሩት በ 16ኛው ክፍለ ዘመን የኖሩት አፄ ፋሲል ነበሩ። ከኑብያ ብቻ ሳይሆን ከስናር (ከካርቱምብዙያልራቀ ስፍራ) ድረስ የወርቅ ግብር ይመጣላቸው ስለነበር አዝማሪ አንዲህ ሲል የሱዳን ገዥነታቸውን አረጋግጦላቸው ነበር፤-

ጎንደር ቢያጉረመርም ፋሲል ፈረስህ ኑብያና ስናር ወርቁን ጫኑልህ፥ሳሩን ተጠየፈ የፋሲል ፈረሱ፥ ክምር የሱዳን ወርቅ ገፈራው ነው ለሱ።

“ገፈራ” ማለት የፈረስ ምግብ ነው። ዛሬ ፉርሽካ የምንለው ዐይነት። እንግዲህ ይህ ግጥም፥ ሱዳን አስከ የዛሬ 500 ዐመት የኢትዮጵያ ግዛት አንደነበረች ይመሰክራል። በሁዋላ በዘመነ መሳፍንት አና ከዛ ትንሽ ቀደም ብሎ ኢትዮጵያ አየተዳከመች ስትሄድ ቱርኮች ያዝዋት። ቱርኮች ተዳክመው ለእንግሊዝ ለቀቁላት። እንግዲህ ከእጅ የወጣ ሃገር በታሪክ ሰነድ ወይም ማረጋገጫ የሚመለስ ቢሆን ኖሮ፥ መላው ሱዳን ለኢትዮጵያ በተመለሰ ነበረ። ከላይ አንደ ተረዳነው ሱዳን የኢትዮጵያ እንጂ ኢትዮጵያ የሱዳን ሆና አታውቅም። ታዲያ በምን ምክንያት ነው አሁን የኢትዮጵያን መሬት የጠየቀችው? እስዋ አፍዋን ምን ቁርጥ አርጉዋት ጠየቀችና? እስዋ በራስዋ ተነሳስታ ደፍራ መሬት አለኝ አላለችም።

አሁን በአመራር ላይ የአሉት የኢትዮጵያ ባለስልጣናት ደርግን በሚዋጉበት ሰዐት ሱዳን ለዋለችላቸው ውለታ ወሮታውን ሊመልሱላትና አሁንም ተቀዋሚዎቻቸውን እንዳታስተናግድ የሚከፍሉዋት ዋጋ መሆኑ ነው። ወዲህም መሬቱ ያለው በአማራ፥በቤንሻንጉል፥ በጋምቤላና በአሮሞ ክልሎች ስለሆነ የእኛን ምድር ስለማይመለከት ችግር የለውም ዐይነት ነው። ብሄራዊ ስሜት የሚባል ነገር ስለሌለ። መሬት በነፃ እንካ ከተባለ ማን ይጠላል? ስለዚህ ሱዳኖቹ እየፈነጠዙ ሊወስዱ አኮብኩበዋል።አሁን ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው መንግሥት 1600 ኪሎሜትር ለም መሬት ለሱዳን ይገባታል ብሎ ጠበቃ የቆመላት እላይ የተጠቀሰው ቅኝ-ገዢ መኮንን በቸከለው ድንበራዊ ችካል ክሆነና በእንግሊዝ ቅኝ ገዥነት አገር ቅርጫ አንዲሆን ከተፈቀደ፥ እንዲሁም እንግሊዝ ያቀናው መሬት ሁሉ ለሱዳን ይቸር ዘንድ ከተፈረደ፥ የቀድሞው የአንግሊዝ ቅኝ ግዛቶች የነበሩት እነ ዩጋንዳና ሱዳን፥ ካስፈለገም እነ ናይጀሪያ ሁሉ ለሱዳን መሰጠት ይገባቸዋል ማለት ነዋ!!! የሆነ ሆኖ፥ ያ ሆፈፌ ቅዥተኛ እንግሊዝ ምኞታዊ ህልም አልሞ የፈለገውን ያህል የወሰን ድንጋይ ቢተክልና አፄ ምኒልክም አልተስማሙም እንጂ ቢስማሙለትና መሬት ቆርሰው ቢሸልሙትም አንኩዋን ያ ውል የሞተ ነው። ለምን ቢባል፥ ሱዳንን ዐለምና የተባበሩት መንግሥታትም ያወቃትና በታሪኩዋ ለመጀመሪያ ጊዜ ራስዋን ችላ የራስዋን ባንዲራ ያውለበለብችበት ዳር ድንበር አሁን የአለው ነውና። እኤአ በ 1953 ዐመተ ምህረት እንግሊዝ ግዛቴ ይሄ ብቻ ነውና ያንቺም ግዛትሽ ይሄው ነው ብሎ በዐስር ጣቱ ፈርሞ የተወላት መሬት ነው። እሱውም ከመከፈልዋ በፊት የነበረው የቆዳ ስፋቱ 2,505,813 ስኩዌር ኪሎሜትር የሆነው ነው። ከመከፈልዋ በፊት ሱዳን በቆዳ ስፋት ከአፍሪካ አንደኛ ነበረች። አሁን ሶስተኛ ነች። አሁንም ከኢትዮጵያ ትልቃለች ማለት ነው። የያዘችው ይበቃት ነበር። የኢትዮጵያን መሬት ለግሰናት በደቡብ ሱዳን የተወሰደባትን መሬት እንተካላት ካልተባለ በቀር። ሰጭና ነሽው አንግሊዝ ከተደረገና የእንግሊዝ መንግሥት ለክቶ፥ “አበጥሮ”፤ “አንጥሮ” ሁሉን አጣርቶ ራሱ በመጨረሻ ያረጋገጠው የሱዳን ምድር እላይ የተጠቀሰው ስፋት ከሆነ በምን ሂሳብ ነው አንግሊዝም ሆነ የተባበሩት መንግሥታት የማያውቁትን የኢትዮጵያን መሬት በ ህቡዕ ለሱዳን የሚለገሳት? አይገባትም አንጂ በእርግጥ ሱዳን ይገባኛል የምትለው መሬት ከአላት ወደ ተባበሩት መንግሥታት ሄዳ ነው አንጂ አቤቱታዋን የምታቀርበው በስርቆሽ በር ነው እንዴ መሬት ቆርሳ የምትሮጠው? ወይንስ መሬቱን ከቦጨቀች በሁዋላ ወደ ተባበሩት መንግሥታት ቀርባ መርቁልኝ ልትል ይሆን? እስዋ ግን ወደ እዛ እስካሁን ያልሄደችው እኤአ በ 1953 እንግሊዝ ካስረከባት በቀር ሌላ መሬት ስለማይገባት “ወይጅ ወዲያ አትቀልጅ!” ይሉኛል፤ ብላ ፈርታ ነው። አለዛ ሱዳን ነፃ ከወጣች ጀምሮ መሪዎችዋ ከ ኢብራሂም አቡድ ጀምሮ እስከነ ኑሜሪ አና አሁን ያለውም አል በሺር የይገባኛሉን ጥያቄ ገና ድሮ ባቀረቡ ነበር። ሰብብ ፈጥረን ስለቀድሞ ውለታዋ እና ተቀዋሚዎቻችንን ስለምትገታልን እንዲሁ በነፃ እንቸራት ካልተባለ በቀር እንደ እውነቱ ከሆነስ ሱዳን፥ “ኢትዮጵያ ያዘችብኝ፥ ይገባኛል፤” የምትለው አንዲት ስንዝር መሬት የላትም። ከቅኝ ግዛት ነፃ ከወጡ በሁዋላ የአፍሪካ ሀገራት በሞላ የያዙት ድንበርና ወሰን የቅኝ ገዥዎችቸው አነዚህ ናቸው፤ ብለው ያረጋገጡላቸውን ብቻ ናቸው። ስለዚህ ሱዳን ከሌሎቹ የአፍሪካ ሃገራት በምንም አትለይም። በመሆኑም ከኢትዮጵያ ልቀበል ይገባኛል ልትል የሚያስችላት ኢትዮጵያ ውስጥ አንድ ጥሪኝ አፈር የላትም። ስለ ኦሜድላ ብቻ እንኩዋን ብንዘክር፥ አፄ ኅይለሥላሴ በሱዳን በኩል ከስደታቸው ሲመለሱ ከ 5 ዐመታት በሁዋላ ለመጀመሪይ ጊዜ የኢትዮጵያን ሰንደቅአላማ ሰቅለው የአውለበለቡት ኦሜድላ ላይ ነበር። ይህን በሚያደርጉበት ጊዜም የ እንግሊዝ የቅኝ ገዢ ትልቅ ባለስልጣናት ለ ሰንደቅአላማዋ አክብሮት በተጠንቀቅ ቆመው መሬቱ የኢትዮጵያ መሆኑን ተቀብለው ይመለከት ነበር እንጂ “የሱዳን መሬት ላይ እንዴት ባንዲራ ያውለበልባሉ!” ሲል በንጉሱ ላይ ቅዋሜ አላሰሙም።

ኦሜድላ የኢትዮጵያ ለመሆንዋ ከዚህ በላይ ምን ማረጋገጫ አለ? ታዲያ በምን ምክንያት ነው አሁን ይቺ ታሪካዊ ስፍራ ለሱዳን የምትሸለመው? ቀዳማዊ ኅይለሥላሤ ኦሜድላ ላይ የኢትዮጵያን ሰንደቅአላማ ሲያውለበልቡ ጦሩን እንዲያቀነባብር በእንግሊዝ መንግሥት ተሹሞ አብሮአቸው በሱዳን በኩል የገባው ሜጄር ዊንጌትም ታዛቢ ሆኖ እጎናቸው ነበረ። ንጉሡን ተሽቀዳድሞ አዲስ አበባ የገባው ሎርድ ካኒንግሃምም እሳቸው ኦሜድላ ላይ የኢትዮጵያን ሰንደቅአላማ እንዳውለበልቡ አሳምሮ ያውቅ ነበር። እነዚህም ሁለት ታላላቅ የእንግሊዝ መንግሥት ተወካዮች ኦሜድላ የኛ ናት አላሉም። የሆነ ሆኖ እውነት እንግሊዝ ከ አፄ ምንይልክ ጋር ተዋውሎ ከነበር እሱው እንግሊዝ የመሬት ይገባኛል ጥያቄውን ያቅርብልን እንጂ ያልተዋዋልናት ሱዳን ምን አገባት? ከሱዳን ሳንዋዋል እንዴት ሱዳን የተዋዋልነው ይከበርልኝ፥ ልትል ትደፍራለች? ይህን ጥያቄ ሊያነሳ የሚችል አንግሊዝ ብቻ ነው። ነበርም። ግን እንግሊዞች አላነሱም። ምክንያቱም ቀላል ነው። የዚህ ዐይነት ውል ከአፄ ምንይልክ ጋር ስላተፈራረሙ። ተፈራርመው ቢሆን ኖሮ መጠየቅ ብቻ አይደለም፥የተፈራረሙበት ቀለም ሳይደርቅ መሬቱን እጃቸው ያስገቡ ነበር። ስላልተፈራረሙ ይህን አላደረጉም። የሱዳንን ነፃነት እንግሊዞች ሲፈቅዱም የተባለውን መሬት የኔ ነበር ብለው ወደ ሱዳን አላዘዋወሩም። አሁን ያለውን መሬት ብቻ ነው ትተውላቸው የሄዱት።አሱም ለሁለት ተከፍሎባቸዋል። ከአንግሊዝ የተረከቡትን መሬት እንኩውዋን በቅጡ መያዝ አቅቶአቸው “የቆጡን አወርድ ብላ የብብትዋን ጣለች፤” የተባለው ተረት በነሱ ላይ ተፈፅሞባቸዋል። የራሳችውን አጥብቀው መያዝ ሳይችሉ የኛን መሬት መከጀላቸው ማስቆጣት ብቻ ሳይሆን ያስደንቃል። እንግዲህ እንግሊዝ ከአፄ ምንይልክ ጋራ መሬትን አስመልክቶ ላለመዋዋሉ ሶስት ማስረጃዎች አሉ ማለት ነው። አንደኛ፥ የተባሉትን መሬቶች ቀደም ሲል እጁ ባለመክተቱ፤ ሁለተኛ፥ ንጎሱ ኦሜድላ ላይ ሰንደቅአላማችንን ሲሰቅሉ አለመቃወሙ፥ ሶስተኛ፥ ሱዳንን ለቆ ሲሄድ ለሱዳን ከተወላት የተባበሩት መንግሥታይ ባፀደቀላት ዳር ድንበር ውስጥ እነዚህን ሁሉ የኢትዮጵያ መሬቶች በካርታም ሆነ በፅሁፍ ባለማካተቱ። በነዚህ ሶስት ማስረጃውች ምክንያት እሩቅ ሳንሄድ፥ ሰነድ ለማግኘት አፈር ሳንቆፍር እና ድንጋይ ሳንፈነቅል ምንይልክ እና እንግሊዝ አንዳችም የመሬት ውል እንዳልተፈራረሙ እናረጋግጣለን። ተፈራርመዋል የሚል እስቲ ሰነዱን ያቅርብልን!!! ደግሞም ቢፈራረሙም እንኩዋን ውሉ የቅኝ ገዥዎች ሰለሆነና ምንይልክም ሆነ ማንኛውም መሪ የአትዮጵያ መሬት የግል ንበረቱ ስላልሆነ መሬት ለባእዳን ሰጥቻለሁ ቢል አይፀናም።አፄ ምንይልክ ተስማምተውበት፥ አፄ ኅይለሥላሴ እና ደርግ ያፀደቀውን ነው እኛ በ ተግባር የምናውለው፤ ሲል ኢህአዲግ ደጋግሞ ተናግሮአል።

ይህን መሰረት በማድረግ እኔ ብዙ ምርምር አካሂጄ ሁለቱ አፄዎችና የደርግ ሊቀመንበር የነበሩት ኮረኔል መንግሥቱ ኅይለማርያም ለሱዳን መሬት ለመስጠት የተዋዋሉበት አንድም ሰነድ አላገኘሁም።ምክንያቱም ስላልነበረ። ስለ ሌለም። አሁን በህይወት የአሉት ኮሎኔል መንግሥቱም አንድም የዚህ ዐይነት ውል ከሱዳን ጋር እንዳልተፈራረሙ አበከረው መስክረዋል። ይልቁንም አኔ ያገኘሁት መረጃ፥ አውሮፓውያን መንግሥታት ለብቻቸው ተሰብስበው አፍሪካን ለመቀራመት ያደረጉትን ውል ለአፄ ምንይልክ ነግረው የኢትዮጵያን ነፃነት ግን አንደሚያስጠብቁ ቢገልፁላቸው፥ “እኔ በሌለሁበት እናንተ ተሰብስባችሁ ያደረጋችሁትን ውል በፍፁም አልቀበልም፤ የኢትዮጵያን ነፃነት አናስጠብቃለን ሰለአላችሁት ግን አመሰግናለሁ፤” በማለት ተንኮላቸውን ውድቅ ማድረጋቸውን የሚያሳይ ነው። በነገራችን ላይ፤ አፄ ምንይልክ እንኩዋን ለሱዳን መሬት ሊሰጡና በሰላም ኢትዮጵያ ውስጥ ይኖሩ የነበሩት የውጭ ሀገር ሰዎች መሬት አንዲገዙ አይፈቅዱላቸውም ነበር። አላደረጉትም እንጂ ሶስቱም መሪዎች አድርገውትም እንኩዋን ቢሆን፤የኢትዮጵያን ህዝብ መሬት አንስተው ለባእዳን ለመቸር ምንም መብት አልነበራቸው። ኢትዮጵያ፥ እንዲያስተዳድሩዋት አደራ የተሰጠቻቸው ምድር እንጂ እንዳሻቸው ለፈለጋቸው አገር ገፅበረከት አድርገው የሚለግስዋት የግል ንብረታችው አልነበረችምና። አሁን ያለውም መንግሥት አንዲሁ የኢትዮጵያን መሬት ገምሶ ለባእዳን ለመቸር ከቶም አንድም ህገመንግሥስታዊ ነፃነት ወይም ስልጣን የለውም። በጉልበቱ ካልሆነ በቀር። ረጅሙን ታሪካችንን ወደ ሁዋላ መለስ ብለን ብናስተውል፥ ባለፉት 5300 ዐመታት ኢትዮጵያን የመሩት መንግሥታት ድንበር ከማስፋት በቀር መሬታቸውን እንደ አንጀራ ቆርሰው ለባእዳን ሲቸሩ በፍፁም ተስተውሎ አያውቅም። አሁን ከአለው መንግሥት በስተቀር።እዚህ ላይ ባድመ ይታወሰናል። ባድመ ባድማው ደረቁ መሬት ከአትዮጵያና ኤርትራ በኩል ወደ 150000 ገደማ ወይም ከዛ በላይ ምስኪን ሰዎች በከንቱ አስጨረሰ። ከዚያ አልጀርስ ላይ ለኤርትራ ይገባታል ይሰጣት፤ ተብሎ ተፈረደላት።ባድመ እስካሁን በ ኤርትራ እጅ ውስጥ አልገባችም። ለምን? የትግራይ መሬት ውስጥ ስለሆነች የማትነካ፥ የማትገሰስና የተቀደስች ሆና ወይስ በሌላ ምክንያት? ሰፊ መሬት አለኝ ብሎ ከማውራት በቀር ለማንም የማይጠቅመውን ጠፍ መሬት አንሰጥም ብሎ ይዞ፥ ለመሬት ብላ ከኛ ላልተዋጋችው ሱዳን ለምለም ምድር ገምጦ ለመቸር መቸኮል ምን ይባላል? ይህ ለሰሚው ግራ ነው። ባድመም በኤርትራ ላትወስድ የቻለችው፥ “ትግራይ ሀገርህ ተወራለችና የኢትዮጵያ ህዝብ ሆይ! ተነሳ!” ተብሎ በተጠራው የሀገር ማዳን ጥሪ መሰረት፥ “ጉዳዩ እኔን አይመለከተኝም ይህ የትገራይ መሬት ነው፤” ሳይል በብሄራዊ ስሜት የነደደው ቆራጡ የኢትዮጵያ ህዝብ አጥንቱን ከስከሶ፤ ደሙን አፍሶ፤ንብረቱን አጉድሎ ባደረገው ተጋድሎ ነው። ትግራይ ስትወረር የኢትዮጵያ ህዝብ ፥ “ወይኔ ሃገሬ!” ብሎ ደሙን ሲያፈስ ባድመ የመጨረሻው እንጂ የመጀመሪያው አይደለም። ከዛ በፊት ጣልያን ከማንም አስቀድሞ ትግራይን በወረራት ጊዜ በመቀሌ፥ በአምባላጌ፥በአድዋ እና በማይጨው በ 40 ዐመታት ልዩነት ውስጥ ሁለቴ ከፍተኛ መስዋእትነት ከፍሎአል። ለዚህ ሁሉ ውለታው አፃፋው ይሄ ነውን? እባካችሁ ሰከን ብላችሁ ነገሩን አስቡበት። ይህ ድርጊት በትውልድ ያስወቅሳችሁአል። ጠንቁ ለልጆቻችሁና ለልጅ ልጆቻችሁ፤ እንዲሁም ለዘራችሁ ይተርፋል። ለስልጣን ያበቃችሁ የትግራይ ህዝብ ሳያቀር በአደራጎታችሁ ያፍርባችሁአል። የኢትዮጵያ ህዝብ ዛሬ አቅም ባይኖረው ነገ ሊጠነክር ይችላል። ሳይወድና ሳይፈቅድ መሬቱን ሱዳን አሁን ብትወስድበት እንኩዋን ነገ ሲጠነክር ተዋግቶ ያስመልሰዋል። በዚህ ሳቢያ አሁን ልትጠቅምዋት ያሰባችሁአት ሱዳንም ሰላም አታገኝም። የ እናንተም ስም በክፉ ተነስቶ አፅማችሁም ሲወቀስ ይኖራል። ስለዚህ ሱዳንን በሌላ በሌላ ነገር ካስዋት እንጂ የስንት ሰማአታት ወገኖቻችን ደም እና ላብ የአለማውን መሬታችንን አሳልፋችሁ በብላሽ አትስጡ። ለሱዳን ካሳ፥ አፍንጫዋ ስር የተገነባላት የአባይ ግድብ መች አነሳት? በዚህ የኢትዮጵያ ህዝብ ገንዘቡን በከሰከሰበት ግድብ ከማንም በላይ ተጠቃሚዋ ሱዳን አይደለችንምን? ግድቡ ይበቃታል፤ መሬቱ ይቅርባት። ብቻችሁን ይህን መወሰን ካስቸገራችሁ ደግሞ ፓርላማችሁና የኢትዮጵያ ህዝብ ይምከርበት። ለይስሙላስ ቢሆን ፓርላማ አለ አይደል? እንዲህ ዐይነቱ ትልቅ የሀገር ሉአላዊነት ጉዳይ ሀገር ሳይመክርበትና ህዝብ ሳይወስንበት አንዴት በዝግ ጉዋዳ ይካሄዳል? ባድመ አንዳትወሰድ የተረባረባችሁትን ያህል አና ለኤርትራ አንዳይሰጥ የምትተጉትን ያህል፥ እባካችሁ አሁን ሱዳንን የሚያዋስናትን ሁሉ የኢትዮጵያ ዳር ድንበር ለሱዳን ከመቸር ታቀቡ። በውኑ ከዚህ ከታቀባችሁ፥እናንተም፤ ልጆቻችሁም፥ ዘራችሁም፥ አንዲሁም በመቃብር ውስጥ የሚኖረው አፅማችሁም ከመወቀስና ከመረገም ይተርፋል። ጆሮ ያለው ይስማ። ልብ የአለው ልብ ይበል።l

Petition Letter to UN Secretary General: Ethiopia and Sudan border demarcation

Click here to Sign ለመፈረም ይህን ይጫኑ

(This petition do not recommend donation! Your donation will help keep iPetitions running. This is not a donation to the person or organization whose petition you just signed.)

Petition Letter to UN Secretary General: Ethiopia and Sudan illegal border demarcation

December 19, 2015

H.E. Mr. Ban Ki-Moon
United Nations Secretary General
1st Avenue, 46th Street
New York, NY 10017

Your Excellency:

We the undersigned Ethiopian political parties and civic organizations have the honor to bring to your attention certain developments which do not augur well for the maintenance of peace and security between Ethiopia and the Sudan. Given that sovereignty lies with the Ethiopian people (and state) rather than with a regime, we feel compelled to put all responsible states and international organizations on notice that the long-term interests of the peoples of Ethiopia and the Sudan are being compromised to advance the interests of the elites who have forcibly usurped the power of the state.

Your Excellency will recall that, almost two years ago, several political parties and civic society organizations had the honor to register with your office a strong protest against a secret border deal that the dictatorial governments of both countries had concluded. Although the exact details of the deal are still shrouded in secrecy, the media in both countries have recently reported that the Ethiopian Prime Minister and the Sudanese President have made public their intention to demarcate the common boundary between the two countries on the basis of that deal.

We wish to recall that the respective territorial limits of both countries were defined by treaty at the turn of the 20th century. The 1902 Treaty provided that the line delimited therein must be demarcated by officers of the two governments. If and when the decisions and recommendations of the Joint Commission were accepted by the two governments, each side was then to undertake to explain the boundary line to their respective citizens.

This, however, did not occur. Instead, Major Gwynn alone, representing Great Britain as the colonial power then administering the Sudan, travelled the whole frontier ( about 950 miles) in the space of just a few months in 1903 and purported to demarcate the boundary. In this demarcation, the line Gwynn actually marked out departed from that marked on the map attached to the Treaty in several places for reasons which he alone deemed adequate. In the event, the reasons for the departure were all self-serving and unsurprisingly ended up favoring the Sudan to Ethiopia’s detriment.

It would be carrying coal to Newcastle to point out to Your Excellency that an arbitrary and unilateral demarcation line carried out by a colonial officer a century ago cannot bind the Ethiopian government. It is precisely for this reason that more than four successive Ethiopian governments prior to the current one have rightly and consistently rejected initially British and subsequently Sudanese entreaties to give the boundary line official legitimacy. As early as 1924, Emperor Haile Selassie, when he was still Regent of Ethiopia, declined to accept Gwynn’s unilateral acts, calling on the British government instead to demarcate the frontier by a joint Anglo-Ethiopian commission on the basis of the 1902 Treaty. In calling for such a commission, he minced no words in pointing out to the British Prime Minister of the time, Mr. Ramsey MacDonald, the fact that the frontier had not been demarcated in accordance with the 1902 Treaty. Successive Ethiopian administrations have uniformly maintained this position.

Recently, however, Sudan’s fortunes have improved dramatically with the apparent decision of the quisling government ruling Ethiopia today to accept Gwynn’s line as the basis for a fresh marking of the boundary on the ground. The decision to give legitimacy to the Gwynn line is widely interpreted by the Ethiopian public as a backroom deal intended as a quid pro quo for the Sudan to deny support for the opponents of the current Ethiopian regime. For the Sudan, the Gwynn line offers a vast expanse of territory that historically and under the 1902 Treaty legally belongs to Ethiopia. In return for acquiring Ethiopian territory, the Sudan has pledged that its territory shall not be used by Ethiopian political movements seeking to bring about democratic change in their country.

The rub, however, is that the decision to demarcate the boundary on the basis of a one-sided, outdated, unilateral and illegal arrangement is sure to be a continuing and prolific source of friction and conflict between the sisterly peoples of the two countries and their governments. An arrangement contrived by the extremely narrowly-based, illegitimate, and hated government of Ethiopia and the equally discredited government of the Sudan, led by a war criminal according to the International Criminal Court, will not and cannot stand the test of time.

We have it on good authority that the impending demarcation will deviate from boundary line as defined by the Treaty. Such a boundary will never be accepted by the vast majority of the Ethiopian people. That this is the position of the Ethiopian people has been made manifest by the numerous public demonstrations and press releases, at home and abroad, put out by virtually all political parties, civic organizations, and prominent intellectuals and elders. More importantly, the Ethiopian communities in the border areas who stand to lose their ancestral lands have already put up a stiff resistance in defense of Ethiopian territory and in rightful defiance of the current government’s actions.

As such, it defies common sense to believe that the demarcation line concocted by the two governments will stand the test of time as a final boundary. Quite to the contrary. The effort should be considered as laying a land mine with great potential to destroy relations between the two countries when the shelf life of the current rulers expires. And expire it will, sooner than the leaders are able to realize for they have been blindsided by greed and power.

Your Excellency knows the Horn of Africa is a region already plagued by extreme insecurity and instability, owing among other reasons, to its location astride the Red Sea, its proximity to the conflict- ridden Middle East, and the rivalries of great and aspiring powers alike arising from their desire to control the Nile basin and to exploit the natural resources of the region. Sadly, the Al-Bashir government has become the gateway and proxy for some of these powers and is intent on leveraging its friendly relations with Ethiopia’s historic enemies to obtain undue territorial concessions. The territories it seeks to acquire happen to be extremely fertile and close to Ethiopia’s major river systems, which it will then dole out to rich investors from the Middle East.

Recent developments along the Ethio-Sudanese border are harbingers of what we fear will come to define relations between the peoples of the two countries. Just a few months ago, thirty-three Ethiopians were taken prisoner by the Sudanese forces and a further eight Ethiopians were abducted from the border region by Sudanese militia and cruelly slaughtered like sheep near the Sudanese town of Gallabat. Following this massacre, the border has witnessed a rash of clashes between Ethiopian citizens and Sudanese militia as well as citizens. The Sudanese Ministry of the Interior has claimed that sixteen Sudanese civilian were killed and seven abducted in October by armed Ethiopian groups in reprisal raids. Needless to say, this cycle is likely to escalate with the implementation of the demarcation plan.

The feckless and illegitimate government of Ethiopia has chosen to sweep news of these clashes under the rug. Sudanese media, however, have carried several candid and strident interviews including, for example, with the Sudanese Ambassador to Ethiopia revealing the seriousness of the deteriorating situation on the border. The ambassador’s interview confirms our worst fears. Many innocent citizens of both countries have lost their lives and properties as a result of the rising tension on the border. Incredibly, however, the Ambassador seeks to blame the tension squarely on the shoulders of what he refers to as “the neighboring region’s government” – a thinly- veiled reference to the so-called Amhara Regional State- which he accuses of opposition to the demarcation on the basis of the Gwynn line. Yet, the planned demarcation is not confined to just the territory of the Amhara Regional State but extends to the entire frontier between Ethiopia and the Sudan. Therefore, since the boundary question concerns an issue of Ethiopian- not regional – territorial sovereignty, it is bound to involve the entire nation. Ethiopia’s history is replete with examples of its citizens coming together whenever the country’s territorial sovereignty is threatened.

We recognize that our legal standing to lodge complaints of this nature to Your Excellency is somewhat hampered by current international norms. Yet, in as much as festering border problems so often lead to conflicts between states and/or their citizens and since one of the principal purposes of the United Nations is to maintain international peace and security, we believe that it is entirely appropriate for the Secretariat of the United Nations to apprise itself of the current situation on the Ethio-Sudan border.

The border situation has all the elements and hallmarks of a brewing conflict which calls for Your Excellency’s attention. Some may indulge the hope that as long as the current governments of Ethiopia and Sudan are in agreement as to the basis on which the border is to be demarcated there would be little or no threat to the peace and security of the region. That view is in error. Because the current government is wholly unrepresentative of the views and interests of the Ethiopian people and is bereft of any semblance of legitimacy, its commitments and agreements do not carry weight with the people.

The Ethiopian people view the government’s decision to demarcate the boundary on Sudan’s terms as nothing less than a sellout. If the demarcation goes as planned, thousands of people all along the frontier will be uprooted from their homes, farms and investments, a result they will not take lying down. Ethiopians demand that the proposed demarcation of the boundary line be effectuated in compliance with the provisions of the 1902 Treaty. Anything short of that which is concocted as a political expedient for the ruling clique to prolong its power by ceding Ethiopian territory will never be honored by the Ethiopian people and is bound to provoke serious backlash.

In any case, we wish to go on record to affirm Ethiopia’s right to territorial sovereignty as defined by the 1902 Treaty – and not any other agreement that is reached behind the back of the Ethiopian people. We wish the UN Secretariat to know that the Ethio-Sudan border is pregnant with a situation calling for Your Excellency’s attention. We would appreciate registration of our petition with the UN offices and its circulation among member states.

Please accept the assurances of our highest consideration.

Sincerely,

1. Ethiopian Democratic Hibrehizb Unity Movement
2. Ethiopian Peoples Revolutionary Party
3. Ethiopian Borders Forum
4. Ethiopiawinnet: Council for the Defense of Citizen Rights
5. Gasha LeEthiopia
6. Gonder Hebret
7. International Women’s Organization

cc. Dr Nkosazuma-Dlamini Zuma
Chairperson of the Africa Commission
P.O.Box 3243
Addis Abeba, Ethiopia

The Government of the Republic of Sudan
C/O The Embassy of the Republic of Sudan
2210 Massachussetts Avenue
Washington, DC, 20008

The Federal Democratic Republic of Ethiopia
C/O The Embassy of Ethiopia
3506 International Drive, N.W.
Washington, DC, 20008

ለሆዳሙ አማራ የተላለፈ ጥሪ

By Achamyeleh Tamiru

ለሆዳሙ አማራ የተላለፈ ጥሪ

ወያኔ የጎንደርን መሬት ለሱዳን አሳልፎ በመስጠት አማራውን የማጥፋት ፕሮጀክቱን አጠናክሮ ቀጥሏል! ሆዳሙ አማራ ግን ይህንን እያጠፋው ያለውን የግፍ አገዛዝ 35ኛ ዓመት ውልደትና የአማራውን የእልቂት አመታት ድል ባለ ድግስ ሲያከብር «አይ አማራ፤ ያን ሁሉ አማራ የጨረሰን ስርዓት፣ ሊያጠፋው የታገለውንና መንግስት ከሆነም በኋላ እያጠፋው ያለውን ቡድን ልደት እንዲህ ድል አድርጎ ይደግስና ያክብር» እየተባለ ልክልኩን ሲነገረው ሰንብቷል። ይህም ሲያንሰው ነው! ሆዳም የሆነ የጉድ ህዝብ!

የጦጣ ግንባር የምታህል የትግራይ መሬት የሆነችውን ባድሜን «ኤርትራ ልትወስድብን ነው» ብሎ ወያኔ ጦርነት ውስጥ ገብቶ 80 ሺህ የሚሆኑ የድሀ ልጆችን ካስጨረሰ በኋላ አለማቀፍ የድንበር ኮሚሺን ተቋቁሞ ባድመን ለኤርትራ ቢወስንም ወያኔ ግን የትግራይ መሬት የሆነውን ባድመን ለኤርትራ ላለመስጠት አሻፈረኝ በማለት እስካሁን ተቀምጦ ጅቡቲን የሚያህል የአማራውን መሬት ግን በድብቅ ለሱዳን መስጠቱ የማይቆጨው ሆዳሙ የአማራ ህዝብ ከገዳዩ ኋላ ሲጎተት ይኖራል! ዓሰብም ወሎ ስለነበረች ነው ተላልፋ የተሰጠች። አሰብ ትግራይ ቢሆን ኖሮ ከባድመ በላይ ደም ይፈሳል እንጂ ተላልፋ አትሰጥም ነበር። የሰሜን ወሎ መሬት ወደ «ትግራይ ሪፑብሊክ» የተካተተው፤ መተከል ከጎጃም ተቆርሶ ወደ ቤንሻንጉል ጉሙዝ የገባው፤ ወልቃይትና ሁመራ ከጎንደር ተቆርሶ ወደ «ትግራይ ሪፑብሊክ» የተጠቃለለው ሆዳሙ አማራ ሳያውቅ አይደለም። ይህንንና ሌላውን በአማራ ላይ የደረሰ በደል እየገጣጠመ ምስል የማይፈጥር ደንቆሮና ሆዳም ብቻ ነው።

እኔ ካሁን በኋላ ወያኔን ማውገዝ ልተው ነው። ወያኔ ዛሬ እያደረገው ካለው ውስጥ አንድም ያልታገለለት ነገር የለም። የታገለለትን ለምን አሳካህ ብሎ መውቀሱ ተገቢ አይደለም። ወያኔ ጫካ ሀ ብሎ ሲገባ ለሚመሰርተው የትግራይ ሪፑብሊክ መንግስት ጠላቱ አማራ እንደሆነና አማራ ካልጠፋ የትግራይ ሪፑብሊክ መንግስት እውን እንደማይሆን በጥቁርና ነጭ ብራና ፍቆ ቀለም በጥብጦ ማኒፌስቶ በመጻፍ ነው የበረሀ ትግሉን የጀመረው። በአስራ ሰባት አመታት የትግል ቆይታውም የትግራይን ወጣት የቀሰቀሰው፤ ቄስ መነኩሴውን ከጎኑ ያሰለፈው «አማራ ሰይጣን ነው፤ ሰይጣን ስለሆነ ይህን ሰይጣን ተረባርበን ማጥፋት አለብን» ብሎ ያነሳሳው ሰይጣኑን አማራ ለማጥፋት ነው። ታዲያ ዛሬ ወያኔ ያንን የታገለለትን አማራውን የማጥፋት ግቡን እየደረሰበት ቢመጣ ጥፋቱ ምኑ ላይ ነው? ስንት ሺ የትግራይ ወጣቶችን መስዕዋት ያደረገበት የትግል ውጤቱ አይደለም እንዴ?

ከፍብዬ እንዳልሁት ለአማራው መጥፋት ተጠያቂው ራሱ ሆዳሙ አማራ ብቻ ነው። ከጅምሩ ጀምሮ ወያኔዎች ሲታገሉ [የአማርኛ ትርጉሙ የግርጌ ማስታወሻው ላይ ይገኛል]፤

*« አማራ አድጊ፣ አማራ አሻ፣ አማራ ጉሀፍ » እያሉ እየፎከሩበት»፤

*«ገረብ ገረብ ትግራይ፣
መቃብር አምሃራይ!» በማለት ታጋዮቻቸውን ያጀገኑበት፤

*«ጎበዝ ተኻወት ተጋዳላይ ትግራይ፤
አርኪብካ በሎ ንዚ-ሃሻ አምሃራይ!
ጅግና ተጋዳላይ ስማ’እሞ ህዝባዊ ሰራዊት ስማ’እሞ………………..» በማለት እየተቀኙበት ሊያጠፉት ታፍለው ሳለ የጎንደርና የጎጃም፤ የወሎና የሸዋ ህዝብ ግን መንገድ እያሳዬ፣ «የጠላቴ ጠላት ወዳጄ ነው» ብሎ አብሯቸው እየተዋደቀ፤ ቋንጣና ቆሎ እያዘጋጀ አዲስ አበባ ሚንልክ ቤተ መንግስት ድረስ አጅቦ የሚጠፋበትን በትረ ስልጣን ያስረከበው ራሱ ሆዳሙ አማራ ነው።

ወያኔዎች ስልጣን ከያዙ በኋላም «ሆድ ሲያውቅ ዶሮ ማታ» እያለ ሊታደጉት የተነሱትን ፕሮፌሰር አስራትንና መሰል የህዝብ ልጆችን ቁጭ ብሎ እያየ በወያኔ ያስገደለው እሱ ራሱ አማራው ነው። ከዚያም አልፎ አማሮች እንደ አውሬ ባገራቸው እየታደኑ ሲገደሉ «ወያኔ ከሰራው የአማራ ክልል ውጭ ያሉ አማሮችን አላውቅም» ሲል የወያኔው ሹመኛ፣ ሆዳሙ አማራ ግን በተለመደው የሰነፍ ፍልስፍናው አይቶ እንዳላዬ፣ ሰምቶ እንዳልሰማ የሆነው ራሱ ሆዳሙ አማራ ነው።

ይህ ሆዳም ዝህብ ሊታደጉት ካብራኩ የወጡ ልጆቹን ሁሉ አሳልፎ ለወያኔ በመስጠት አስበልቶ ሲያበቃ የት እንደወደቁ እንኳ ሳይጠይቅ ገዳዩ የመለስ ዜናዊ ሲሞት ግን፣ ኩታውን አዘቅዝቆ፣ ፊቱን ፈጅቶ፣ ደረቱን እየደቃ ከእለት እስካርባ ሀዘን ተቀምጦ የጨካኙን ተስካር ድል አድርጎ ደገሰ። ዛሬ የሚጮህለት ያጣውም ጠላቶቹን አልቅሶ ሲቀብር ለተቆርቋሪዎቹ አንድ ዘለላ እንባ እንኳ በመንፈጉ ነው። ስለዚህ አማራው እያለቀ ያለው ሆዳሙ አማራ በሰራው ስህተቱ ነው። በዚህም የተነሳ ዛሬ ለራሱም ለኢትዮጵያም ሸክምና Helpless Creature ሆኗል። በየእስር ቤቱ አማሮችን ሱሪያቸውን እያስፈቱ «አማራው ሱሪውን መፍታቱን እንድታውቅ ነው» እያሉ ሲሳለቁባቸው፤ ዘሩን እንዳይተካ የአማራ ወንድ በየማጎሪያው ሲኮላሽ፤ እናቶች የሚያመክን መርፌ ሲወጉ ሆዳሙ አማራ ግን ምንም እንዳልደረሰበት አይቶ እንዳላየ የዝምታ ግርማ ውስጥ ተዘፍቆ ይኖራል።

አውቃለሁ ይህንን በመናገሬ «አድጊ፣ አሻ፣ ጓሀፍ» እያሉ በፎከሩበት፤ «ገረብ ገረብ ትግራይ መቃብር አምሃራይ» በማለት ታጋዮቻቸውን ያጀገኑትን፤ «ጎበዝ ተዓወት ተጋዳላይ ትግራይ፣ አርኪብካ በሎ ንዚ ዓሻ አምሃራይ፤ ጅግና ተጋዳላይ ስማ’እሞ ህዝባዊ ሰራዊት ስማ’እሞ………………..» በማለት ያጠፉትን ወያኔችን አንድም ያልተነፈሰ ሆዳም አማራ ሁሉ በእኔ ላይ እንደሚነሳ ይገባኛል። የአማራው ጠላት ሆዳሙ አማራ እንደሆነ ስለማቅ ግን ማንም ሆዳም እየተነሳ በበላበት ቢጮህ አይገደኝም።

ሰው የሌለው የጎንደር መሬት ግን እንዲህ እያለ ይጮሃል…..

መተማ ሁመራ ቋራም ሆድ ሲብሰው፣
ሱዳን ተሰደደ መሬቱም እንደሰው፤

የፕሮፌሰር አስራት ልጅ የሆነው የጎንደር ገበሬም ብቻውን ያለሰው ያለዘር ቢጮህ ምን ያደርጋል ብሎ እንዲህ ይላል….

በሮቼን አምጡልኝ አርጀ ልብላቸው፣
ደግሞ እንደመሬቱ ሳይቆረጥማቸው፤
መሬቱን ሲያርሱብኝ እያየሁ ዝምብዬ፣
ዘር ሳይዙ ማረስ ምን ያደርጋል ብዬ፤
እንዲህ ያለ ዘመን የተገላቢጦሽ፣
አህያ ወደ ቤት ውሻ ወደ ግጦሽ።
===================================================

የግርጌ ማስታወሻ
*«ገረብ ገረብ ትግራይ፣
መቃብር አምሃራይ!»
ትርጉም በግርድፉ:- የትግራይ ተራሮች የአማራ መቃብር ይሆናሉ

*«ጎበዝ ተኻወት ተጋዳላይ ትግራይ፤
አርኪብካ በሎ ንዚ-ሃሻ አምሃራይ!
ጅግና ተጋዳላይ ስማ’እሞ ህዝባዊ ሰራዊት ስማ’እሞ………………..» እያሉ

ትርጉም:- ጎበዝ ድል አድርግ የትግራይ ተጋዳላይ፤ ተከትለህ በለው ይህን ጅል አማራይ

* « አማራ አድጊ፣ አማራ አሻ፣ አማራ ጉሀፍ »
ትርጉም :- አማራ አህያ፣ አማራ ጅል፣ አማራ ቆሻሻ
===================================================

ለሆዳሙ አማራ የተላለፈ ጥሪ እነሆ! ይህን ዝግጅት የግድ መደመጥ ያለበት ነው። ኢሳት ምስጋና ይገባዋል! ወንድማገኝ ተባረክ!

http://ethsat.com/…/esat-tikuret-wondimagegne-discussed-wi…/

2015 Border demarcation between Sudan and Ethiopia to resume next December

(KHARTOUM) – Ethiopia’s Prime Minister Hailemariam Desalegn said that redrawing the borders between Sudan and Ethiopia will begin next month according to a previous agreement with Sudan’s President Omer al-Bashir. Sudanese president Omer Al- Bashir and Ethiopian prime minister Hailemariam Desalegn sign a series of joint cooperation agreements in Khartoum 4 December 2013 (Photo SUNA)

The post 2015
Border demarcation between Sudan and Ethiopia to resume next December
appeared first on 6KILO.com.

Clashes Erupted again on Ethiopia – Sudan border

(KHARTOUM) Sudan Tribune – Around 16 Sudanese people have been killed in an attack by Ethiopian armed groups on the joint border, a Sudanese official said on Wednesday. Repeated clashes have been erupted on the Sudanese-Ethiopian border between the ’’Shifta’’ Ethiopian armed groups and the local Sudanese farmers during the recent weeks. Sudan and Ethiopia

The post Clashes Erupted again on Ethiopia – Sudan border appeared first on 6KILO.com.

Sudan’s Defense Force Killed 8 Ethiopian Farmers

(KHARTOUM) Sudan Tribune – Sources have disclosed ongoing clashes between Sudanese troops and Ethiopian gangs known as Shifta on the border between the two countries since Sunday saying that military reinforcement has been sent to the area. A road leading to Ethiopia-Sudan border (Photo Jamminglobal.com) No official statement has been issued from both governments. The

The post Sudan’s Defense Force Killed 8 Ethiopian Farmers appeared first on 6KILO.com.