የማለዳ ወግ . . . የ”ጃሃዳዊ ሐረካት” ዘጋቢ ፊልም መዘዝ !

ለማየት የጓጓነው ዘጋቢ ፊልም . . .
ነቢዩ ሲራክ -ከሳውዲ አረቢያ
“ጀሃዳዊ ሐረካት ” ዘጋቢ ፊልም ” በኢትዮጵያ እስላማዊ መንግስት ለመመስረት
ከሃሳብ ያለፈ እቅድ አላቸው” የተባሉት ተጠርጣሪ አሸባሪዎችን ገመና አንጠርጥሮ
ሊያሳየን መሆኑን ሞቀ ደመቅ ደመቅመቅ ያለው የኢቲቪ ማስታወቂያ ልባችን
አንጠልጥሎት ከርሟል ። ሳምንት በደመጽና በምስል በለፈፉትና በናኙት
ማስታወቂያ የሙሰሊማን የመፍትሄ አፈላላጊ ኰሚቴ አባላት “አሸባሪ” አካሄድ
በተጨባጭ መረጃ እንደሚያሳዩን የነገሩን የመንግሰት መገናኛ ብዙሃንን የተለመደ
ስራ የማውቀው ሳይቀር ነፈሴ በአንገቴ እሰክትወጣ ጉጉት አሳድሮብኛል። ይህ
መሰሉ ስሜት ለጊዜው ምንጩ ከየት እንደሆነ ባውቀውም ስሜቴን ተቆጣጥሬ
በሰአቱ ደረስኩ፡፡ ተመሳሳይ ስሜት አድሮባቸው እንደሁ በሚል እዚህ ሳውዲ
የሚኖሩ ኢትዮጵያውንን እየደወልኩ ስሜታቸውን መጠየቅ ያዝኩ ! እውነት ነው
! ኢቲቪ ሞቅ አድርጎ ማስታወቂያ መልቀቅ ከጀመረ ወዲህ የመንግስት ደጋፊም ሆነ “መንግስት በጣልቃ ገብነት ህገ መንግስታዊ
መብታችን ነካ!” ብለው የተቃወሙ በርካቶች ማክሰኞን እንደኔ በከፍተኛ ጉጉት በመጠባበቅ ላይ መሆናቸውን ተረድቻለሁ ።
ከሁሉም በላይ ጉጉቴን የናጠው ደግሞ “የሃይማኖት ጣልቃ ገብነት ያቁም !” ባዮች አቀንቃኝ የሆነው የፌስ ቡክ ቡድን
“የድመጻችን ይሰማ “ተከታታይ መረጃ ነበር፡፡ ይህ ቡድን ባቀረበው መረጃ ኮሚቴዎች በደረሰባቸው ከፈተኛ ድበደባና ስቃይ
በሚቀርበው “ጀሃዳዊ ሐረካት ” ዘጋቢ ፊልም ላይ ተገደው “በሉ” የተባሉትን ሁሉ ማለታቸውን በትረካ ሳየቀር አቀናብረወት
መስማቴ ነበርና ይህም ህመም ሆኖኛል፡፡ ሙስሊማን “መንፈሰ ጠንካራ”የሚሏቸውን
ተጠርጣሪ ታሳሪዎች የተባሉትን እስላካደረጉ ድረስ ምንም እንኳን ስቅየቱ ቢከፋም
“አድርጉ!” የተባሉትን በግዳጅ ያደርጋሉ ብየ ባለመቀበሌ ስሜቴ የተባለውን ሁሉ
መቀበል ገዶታል! ይህኔ ነበር ግንቦት ሃያ ሲመጣ በዋዜማው አምናና ካች አምና የቀረቡ
የኢሃዲግ የታጋዮች ማዘከሪያ ፊልም ትዝ ያለኝ። በጽናት በግፍ የተገደሉ የእነ
አሞራውና የእነ ማንቴስ የቀደሞ ታሳሪዎች በምርመራ ወቅት ጽኑ ቃላቸው ሰጥተው
የሚያምኑበትን አላማ በልበ ሙሉነት ተናግረው ወደማይቀረ አለም መሸኘታቸው
አስታውሸ ቢያንስ በጥንካሬያቸው አስቀኑኝ፡፡ አንድ ታጋይ ይህን ያህል ጽናት
ሲያድርበት በሃይማኖት ትምህርቱ የጠለቀ እውቀት ያላቸው “እንዴት ቀላሉ ጽናት
ይጎላቸዋል?” የሚለውን ጥያቄ ከታጋዮች ጋር ጋር በማመሳሰል እንዴት ብየ ራሴን አጠየቅኩ. . . እህት ብርቱካን ሜዴቀሳና
አርቲስት ደበበ እሽቱ የሆኑትን አስታውሸም ተከዝኩ፤ አዘንኩ ! እናም ሃሳቤን ወደ እስልምና ሃይማኖት ደቀ መዛሙርቱ
ብመልሰውም ልሰማ የምችለው ምስክርነት “በድምጻችን ይሰማ ” ተጠቁሞኛልና በውስጤ ደስ የሚል ስሜት አልሰማህ ብሎኛል
! እንዲህና እንዲያ ብየ የምይዘው ባጣ ትናንትና ዛሬ በሃገሬ ምድር የማይቀየረው ፓለቲካና የመብት ገፈፋ እንደ አዲስ
አሳሰበኝና በሚሰራው ወደ በሃፍረት እንዳዘንኩ ማክሰኞ ደርሶ ዘጋቢውን ፊልሙን እስካየው ጓጓሁ . . .
አይደርስ የለም ቀኑ ደረሰና ዘጋቢ ፊልሙ ማክሰኞ ማታ ታየ !… የ”ጀሃዳዊ ሐረካት ” ዘጋቢ ፊልም ዋና ማጠንጠኛ
የሆነው በሃይል እሰላማዊ መንግስትን በኢትዮጵያ የመመሰረት እቅድ ትልም ቢሆንም በሙሉ
ፊልሙ የቀረቡት መረጃዎች አወዛገቡኝ፡፡ ፊልሙ አሃዱ ብሎ ጀምሮ እስኪጨርስ የቀረበው
መረጃና ማስረጃ ደረጃው እጅግ የወደረደ መሆኑ የተሰማኝ እኔ ብቻ ብሆን መልካም ነበር፡፡ ይህ
በድምጽና በስዕል ተከሽኖ ብቻ የቀረበው የደህንነትና የፖሊስ መረጃ ቀድሞ ፍርድ ቤትን
የጣለውን “የእስላማዊ መንግስት ምስረታ ” የአቃቤ ህግ ክስ ይግባኝ ማለት ያላስቻለ መሆኑ
አስታወስኩ፡፡ በፊልሙ ውንጀላውን አየር ላይ ከማዋል ባለፈ የሚጨበጥ ነገር አለመኖርና ቅጥ
አምባሩ የጠፋበት መሆኑን ብቻ ማሳበቁ ጠልቆ ተሰምቶኛል፡፡ ብቻ . . . በፊልሙ ግራ
እንደተጋባን ተጀምሮ አለቀ፡፡ ይልቁንም “ከብት ባልዋለበት ኩበት ለቀማ ” እንዲሉ የመንግስቱ ህግ አስከባሪ ከፍተኛ አካላት
በዘጋቢ ፊልሙ እንደማናውቀውና እንደ አዲስ ሶማሊያ ፤ ማሊ ጨምሮ አልቃኢዳና ርዝራዦቹ ያጠፉትን ጥፋት እያሳዩ
አቡበክር በምሽቱ ስርጭት
ከኮሚቴው ጋር ከተያያዙት ተወንጃዮች
አንዱ| ገ ጽ 2
እየተረኩ አደከሙን፡፡ የአሸባሪነትን ክፉነት ከምንም በላይ በስሙ ለሚረዳና የሆነውን እስከ በቂ ማስረጃ ለመስማት ለቋመጠ
ወገን የተበጣጠሰ፤ የተገመሰ፤የተቆራረጠ የሰው ገላና የፈራረሰ ህንጻ ማሳየቱ ድግግሞሽ እንጂ ለተባለው ክስ ግብአት በቂ
አለመሆኑ አናወዘኝ ! ዘግናኝ የጥቃት ምስሎች የተዛመደበት ፊልም ነዋሪው ብዙሃን ሙስሊሞች ይወክሉኛል ብሎ “ለመብት
ጥያቄው መፍትሄ አፍላላጊ ኮሚቴነት” የመረጣቸውን ግለሰቦች መንግስት “አሸባሪ ተጠርጣሪ ” ከማለት አልፎ “በኢትዮጵያ
እስላማዊ መንግስት ለመመስረት ሽብር ጠንስሰዋል” ያላቸው ተከሳሾች ህገ ወጥ እንቅስቃሴ ለማሳየት ኢቲቪ ፤ደህንነትና
ምርመራ ፖሊስ በሶስት ጉልበታሞች የቀረበው ትንታኔም ቢሆን አልተመቸኝም፡፡ ብቻ “ጀሃዳዊ ሐረካት ” በተኩስና በፍንዳታ
ደመቆ በመረጃ ማሰረጃ ሳያጠግበን ተጠናቀቀ !
“ድምጻችን ይሰማ” ቡድን ” ኮሚቴዎቻችን በጸናው አሰቃቂ ምርመራ “በሉ የተባሉትን ስለማለታቸው መረጃ አለን” ያሉት
የምስክርነት ቃል እንኳ ሳንሰማው ቀረ ፡፡ “ድምጻችን ይሰማ”ን ምን ነካቸው? ማለቴ ተጠርጣሪዎች ተገደውም ቢሆን የሰጡት
መረጃ እውነትነት ፍንተው ብሎ አልታየህ እንዳለኝ ስላመሸ ነበር ! በውስጤ ከሚብላሉት ጥያቄዎች መካከል ኡስታዝ አቡበክር
አምኖ የተናገረው እሰላማዊ መንግስት ምሰረታ ፣ በአንዋር መስጊድና በተለያዩ ቦታዎች ለአሸባሪዎች መጽሃፍ ሲበትኑና ድጋፍ
ሊሰጡ ተያዙ ተበለው በ48 ሰአት ከሃገር ተባረሩ ብሎ ኢቲቪ ራሱ የነገረን ሳውዲዎች ጉዳይ በዘጋቢ ፊልሙ በአንዲት መስመር
እንኳ አለመጠቀሱ አዙሮ ላሰበው ግራ ያጋባል ! በመንግስት በኩል ኮሚቴዎችና የህዝበ ሙስሊሙን ጥያቄ ከ”ወሃብይ” ጋር
ሲያያዝ መሞከሩ ብቻ ሳይሆን የአመጹ እንቅስቃሴ አራማጆች የ”ውሃብይ” አስተምሮት ተከታዮች አሸባሪዎች ተብለው
በአደባባይ ሲወንጀሉ ሰምተናል፡፡ ውንጀላው” የወሃብይ” አስተምሮትን ተከታዮች ዋና አላማና ስራቸው ጽንፈኝነትን ማራመድ
እንደሆነ የመንግስት ከፍተኛ ሃላፊዎች ሳይቀር ነግረውናል፡፡ ይህ ሲባል ቢከርምም
ከሳውዲ ጋር በተያያዘ በ”ጀሃዳዊው ሐረካት” ዘጋቢ ፊልም ቅንጣት መረጃ አለመቅረቡ
ጉዳዩን በቅርብ እንደሚከታተል ጋዜጠኛ አስገርሞኛል፡፡ አጠቃ ላይ ሂደቱ ሳይቀር
ከማስገረም አልፎ የተሰራውን ዘጋቢ ፊልም ጥራት፤ ብቃትና ተአማኒነት ዘጭ አድርጎ
የሚጥል አድርጎብኛል፡፡ ሌላው ያስገረመኝና ያሳቀኝ የቃጣር ስልጠና እና ብዙው
የዘጋቢው ፊልም ግብአት ሲሆን ጉዳዩ ከአልቃኢዳው የሶማሊያ ክንፍ አልሸባብንና
መንግስታቸው እየተሰነጣጠቀ አሳር መከራ እየበሉ አፍነው የሚንገላቱት የኤርትራው
ፕሬዚደንት የአቶ ኢሳያስ መንግስት እንደ ቅመም ከዚህም ክስ ዘገባ ማጣፈጫ መደረጉ
ግልጽ አልሆነልኝም! እንደኔ ግንዛቤ በዘጋቢው ፊልም የኢዲቲንግና የመሳሰሉት የድምጽ
ቅንብሮች ውስጥ ዘልቀን ሳንገባ በደምሳሳው የቀረበው ዘገባና ስንመለከተው ዝጋቢ
ፊልሙ በትልቅ የመረጃ ፍልሰት የታጨቀ ስለመሆኑ እኔ ብቻ ሳልሆን ከሰሞኑ የሰበሰብኳቸው የነዋሪው አስተየቶች ያመላክታሉ
!
በስህተት ተሰራጨ የተባለው የምርመራ ፊልም . . .
በስህተት እንደተላለፈ የተጠቆመው ለ18 ደቂቃ የፈጀው ተጨማሪ ፊልም ያየሁት ማክሰኞ ለሮብ ንጋት ላይ ነበር፡፡ በጉጉት
ጠብቄው ሃሞቴን ያፈሰሰውና ጊዜየን ያባከነው በህዝብ ገንዘብ የሚተዳደረው የኢቲቪ፤የብሔራዊ ደህንነትና የፖሊስ ተሰናድቶ
ምሽት ላይ የቀረበው “ጃሃዳዊ ሐረካት “ዘጋቢ ፊልም በደረቁ ሌሊት አምልጦ
ገሃድ ወጣ፡፡ ምሽት ላይ ካየነው ቅንብር የጸዳ በመሆኑ እውነቱን ፍንትው
አድርገን እንድናይ እንድንሰማ ያደርገ ነበር፡፡ የደረቅ ሌሊቱ መረጃ በዋናነት
የሚያሳየው ምሽት ላይ ” እስላማዊ መንግስት እንመሰርታለን!” የሚል እቅድ
እንዳላችው ምስክርነት ሰጭ የሆኑትን ኡስታዛ አቡቦክርን መሆኑ ደግሞ
ከሰማነው በምርመራ ላይ የተቀረጸ ፊልም “ጃሃዳዊ ሃረካትን” ክስና የእስልማዊ
መንግስትን የመመስረት እቅዱን ውንጀላ አራንባና ቆቦ አድርጎት አረፈው፡፡
በዚሁ ፊልም ጎልማሳው ተወዳጅ መምህር አቡበክር ቅሰሙ ስብር በሎ፣ ጠቁሮና
ገርጥቶ፤ አጆቹ በካቴና ተጠፍረው በግላጭ ያሳያል !
ከሃገር ከተባረሩ ሳውዲዎች ሁለቱ
ያመለጠው ምርመራ ! አቡበክር ከነሰንሰለቱ| ገ ጽ 3
አድናቂዎቹ “አቡኬ” የሚሉት አንደበተ ርቱዕ ወንድም አንደበቱ ተቆላልፏል፤ በብረት ሰንሰለት የታሰሩ እጆቹን አንዳንዴ
እያንቀሳቀሰና ራሱን እያወዛዎዘ ሲጠይቁት አጭር መልስ ይሰጣል ፤ ድምጹ የሰላለ ይመስላል፤ አልፎ አልፎ ሲጠይቁት
ቢመልስም የሚናገረው ደከም ባለ መንፈስ ነው፡፡. . . “እስላማዊ መንግስት በኢትዮጵያ የመመስረት እቅድ አለን” የሚለውን
በዚህ ባልተነካካ ፊልም ላይ ለመረዳት ጀሮየን የቆቅ አድርጌ ሰማሁት ! አንዳች ነገር ትንፍሽ አላለም ! እርሱ ከሚናገረው ይልቅ
ጠያቄዎች እንዲል የሚፈልጉትን እያነሱ ይጠይቁታል. . . . አቡበክር ግን በዚህኛው ፊልም ላይ ስለ
እስላማዊው መንግስት ምስረታ የሚለው ነገር የለም ! በቃ ይህው ነው ! ታዲያ የምሽቱ ንግግሩ
ከየት መጣ ? በዚህ ዙሪያ ያለችኝን የድምጽና የምስል ዲዛይን ቅንብር ቁንጽል እውቀት ተጠቅሜ
ሁለቱንም ፊልሞችና ድምጾች ለመፈታተሽ ጀምርኩ፡፡ ያገኘሁት ውጤት የጠረጠርኩት ነበርና
“ኤድያ” ስል ሳላስበው በብስጭት አልኩ ! ድምጽ መስሚያየን ወርውሬና የጀመርኩት “የጀሃዳዊ
ሐረካት” ዘባተሎ ጣጥየው በመውጣት የበኽር ልጀን 11ኛ አመት ልደት ለማሰብ ወደያዝኩት
ፕሮግራም አመራሁ፡፡ የልጅ እዮብን ልደት እንደወትሮው ጓደኞቹን ሰብስቤ ባላከብርለትም
ከታናሽ ወንድሙ ጋር ወደ ሚያማምሩት የጅዳ ትላልቅ አዳራሽ መገበያያና መዝናኛዎች ዞር ዞር
አድርጌ ልመልሳቸው በሚል ወደ ብላቴናዎች አቀናሁ !
ልጆችን ከቤት ላነሳቸው ጎዞ ከመጀመሬ ከጥቂት ደቂቃዎች በፊት በህዝብ ስልክ ተደውሎ የማስጠንቀቂያ ጥሪ አስተናግጀ
ነበርና ይህም ማስፈራሪያ ዛቻ ማስጠንቀቂያው ከፊቴ መጥቶ ተደቀነ ! ሁሉንም በማሰላሰልና ከራሴ ጋር ተሟገትኩ …ከማየው
ከምሰማው ተነስቸው ብዙውን ነገር አውጥቸው ማውረድ ያዝኩ ! ጀሃዳዊ ሃረካት ከተሰራጨ ወዲህ ከታሰበው ዝቅ ባለ
መልኩም ቢሆን ስጋት በነዋሪው መካከል ሰፍኗል፡፡ የሃሳብ መከፋፈል ግን ብዙም አይታይም! እዚህ ሳውዲ አረቢያ ማናቸውም
ዜጎች በአደባበይ ወጥተው ሻማ ለኩሰው ተቃውሞና ድጋፍ ማድረግ አይፈቀድላቸውም፡፡ ይህን ልበል እንጂ ኢትዮጵያውያን
የመንግስት ደጋፊዎች ባሻቸው ጊዜ ፍቃድ ሳይፈልጉ የሚደግፉበት የቆንስልና የኢንባሲ ቦታ
አላቸው ፡፡ ሃሳባቸውን የማይደግፍ ግን የሃገሩ ባንዴራ በተሰቀለበት ቦታ እንደ ደጋፊዎች
መሆን አይፈቀደትም! ከዚህ በተጨማሪ ኑሮው ፈሪ አድርጎታል፡፡ የሚሰራው የማይጥመው
ብዙሃኑ እለታዊ ኑሮን አሸንፎ ኑሮን ከመግፋት ባሻገር ኢንባሲና ቆንስል መስሪያ ቤቱ
ፓስፖርት ለማደስና ጉዳይ ለማስፈጸም ካልሆነ በስተቀር ማየት ያንገሸግሸዋል፡፡ እንዲህ
እያደረገ መከፋቱ ከመግለጽ አልፎ ብዙ መግፋት አይሻም. . . “ሃገር መግባት ትከላከላልህ፤
ትታገዳለህ” የሚለው ያላባራ የደጋፊዎች ማስፈራሪያና ዛቻው በፍርሃት እንዲኖር
አድርጎታል፡፡ ነዋሪው ይህና ያ መሰሉ ጋሬጣ በሸሪአ ከምትተዳደረው ሃገር ነባራዊ ሁኔታ
ጋር ቀፍድዶታልና ከዚህ ባለፈ መሄድን እንደ ማበድ ይስቆጠረዋል ! ያም ሆኖ ጎልማሳና ወጣቱ ስደተኛ በየካፍቴሪያና በየሽሻ
ቤት “ያሻው ይምጣ ብሎ!” ደፍሮ ልዩነቱንና ተቃውሞውን ከመግለጽ አልተቆጠበም፡፡ ይህ ቁጣ ከቀን ቀን ከፍ ይል ዘንድ
መንግስት ከሙስሊሞች ጋር የገጠመው ፍጥጫ ምክንያት ለመሆኑ በቅርብ የማውቀው ጉዳይ ነው ! ማክሰኞ ሌሊት ላይ
የተለቀቀው ሌላኛው ያልተቆራረጠ የኡስታዝ አቡበክር ምርመራ ደጋፊዎች የሚናገሩት ምላሽ ከማሳጣት አልፎ አንገታቸውን
ሰብረው እንዲቁለጨለጩ ምክንያት ሆኗል ማለት እችላለሁ ! የፍርድ ቤት እገዳ ጥሶ ኢቲቪ ያቀረበውን “ጃህዳዊ ሐረካት”
ዘጋቢ ፊልም “የሆሊውድ ፊልም ” በሚል ነዋሪው ያላግጥበት ይዟል፡፡ “ጀሃዳዊ ሃረካት
ዘጋቢ ፊልም ኢቲቪ ታላቅ ስህተትን በራሱ ላይ የሰራበትና እውነትን በፈጣሪ ሃይል
የተጋለጥበት ነው” በማለት አስተያየታቸውን የሰጡኝ አንዳንድ የጅዳ ነዋሪዎች ገልጸልኛል ፡
፡ “ኢቲቪ የታሰበው ግብ አልመታም!” ያሉኝ ነዋሪዎች ጉዳዩን በቅርብ መታዘብ ያልቻሉ
የክርስትያን ሃይማኖችት ተከታዮችና አንዳንድ ለመረጃ ቅርብ ባልሆኑ ወገኖች ዙሪያ ፊልሙ
ሊያድርሰው የሚችለውን አደጋ ስጋታቸው መሆኑ የገለጹልኝ መሆኑን እያስታወስኩ
ከልጆቸ ደረስኩ ! ልጆቸ ደረጃውን ተንደርድረው ወርደው ከፊት ወንበር ለመቀመጥ
በሚያደርጉት የለመድኩት እሽቅድድማቸው ሃሳቤ ተበተነ ! . . . አይ የልጅ ነገር አልኩና “እንቱ ፊን አና ፊን !” አልኩ በአረብኛ.
. . ! እናንት የት እኔስ ወዴት እንደ ማለት ነው ! እናም ትልቁ ቀድሞ ከፊት ተቀመጠ . . . ትንሹ መቀደሙን አምኖ ከኋላ ወንበር
ተቀመጠና ጉዞ ጀመርን ! ከዚያማ ከፊትና ከኋላ “አቤ ” የሚለው ስሜ እየተጠራ በጥያቄ መጣደፍ ያዝኩ ! ደስ የሚል ስቃይ . .
የአንድ ለአቅመ አዳም የደረሰ ጎልማሳ ታዳጊ ወጣት እድሜየን የገፋሁት በአረብ ሃገሩ ስደት በሳውዲ አረቢያ ነው፡፡
በረጅሙ ኑሮየ የሳውዲ ህግን አክብሬ በምኖረው በኔም ሆነ በቀረነው ላይ በሃይማኖት ዙሪያ በኢትዮጵያውያን ሙስሊም
ወንድሞች ቀርቶ በሳውዲዎች በኩል መድልኦ ሲደረግ አላየሁም፡፡ አላውቅምም፡፡ እርግጥ ነው አልፎ አልፎ በግለሰብ ደረጃ
የሚፈጸም በደልና አድልኦ ሊከሰት ይችላል ፡፡ እርግጥ ነው በጣም በጣት የሚቆጠሩ አልፎ አልፎ ሃይማኖታቸውን
የጅዳው አቤቱታ
የጣይፉ ተቃውሞ
የጅዳው ተቃውሞ| ገ ጽ 4
የሚያጠብቁት ኢትዮጵያውያን አሉ፡፡ እኒሁ ሙስሊማን በቤተሰባቸው ውስጥ ሳይቀር ወንድ ከሴት ጋር መቀላቀልን ሲያወግዙ ፤
“ሴት ልጅ ከእግር ጥፍሯ እስከ ራስ ጸጉሯ ትሸፋፈን!” የሚሉና “ቅዱስ ቁርአን የሚያዘንን የማድረግ ግዴታ አለብን!” የሚሉ
ኢትዮጵያውያን የሉም አልልም ፤ አሉ ! ይህ ደግሞ ለኔ የመብታቸውና የምርጫቸው ጉዳይ ነው ! ከዚህ ባለፈ አብዛኛው ነዋሪ
እያከላተመ ያለውን ኑሮ ለማሸነፍ ከሚያደርገው ግብግብ ወጥቶ እስላማዊ መንግስት የመመስረት ሃሳብ ቀርቶ ቃሉን ሲናገሩ
ላለመስማቴ ግን እግዚአብሔር ምስክሬ ነው! ለዚህም ነው ኡስታዝ አቡበክር “እስላማዊ መንግስትን የመመስረት” ሃሳብ
እንዳለው የሚገልጸውን ማስታወቂያ ሰምቸ የ”ጀሃድ ሐረካትን” ፊልም ለማየት ነፍሴ ቋምጣ የነበረው !. . . ዳሩ ግን እድሜ
ለኢቲቪ መረጃ ! ! ራሱ ኢቲቪ ባሰራጨው ደረጃው ባነሰ ዘጋቢ ፊልም ፈላሲ የመረጃ ግብአት የገመትኩት የፈራሁት ሳይሆን
ቀርቷል ! ወደ ቀዳሚው የሪያድ የሃሙስ ምሽት ተቃውሞ እናምራ!
ቀዳሚው ተቃውሞና ትኩረት ልንሰጠው የሚገባ ጉዳይ !
ባሳለፍነው ሃሙስ ማታ ምሽት በሪያድ አንድ አዲስ ነገር ተከስቶ እንደ ነበር አንድ ወዳጀ የላከልኝ መልዕክት ይጠቁማል፡፡
ከፍቷቸው ያመረሩ ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች ለአባይ ቦንድ እንዲገዙ የተጠሩትን ስብሰባ እንዳጨናገፉት ሰምቻለሁ፡፡ በሪያድ
ኢንባሲ የተጠራውን ስብሰባ በተቃውሞ ያመሱት ሙስሊማን ኢትዮጵያውያን በሃገር የሚካሄደውን ልማት ባይቃዎሙትም
እየተፈጸመባቸው ያለውን የመብት ረገጣ መፍትሄ ያገኝ ዘንድ መልስ ይስጠን በሚል እንባቸውን እያዘሩ ተቃውሟቸውን
የገለጹት በሪያድ የሚገኙ ትላልቅ አባቶች መሆናቸውንም መረጃው ደርሶኛል፡፡ በዚህ ተቃውሟቸውም መንግስት መፍትሄ
ከመስጠት ይልቅ ህግን በመጣስ ያስተላለፈውን የጀሃዳዊ ሐረካት ፊልም ስርጭት በጽኑ ሲያወግዙት እየወሰደ ያለውን እርምጃ
ተቃውመውታል፡፡ “በጀሃዳዊው ሃረካት”ን ስርጭት ተከትሎ በሪያድ ለቦንድ በተጠራው ሰበሰባ የተገኙት ኢትዮጵያውያን
ያሳዩትን ቀዳሚ ተቃውሟቸውን ያሳዩበት ተንቀሳቃሽ መረጃው የደረሰኝ ተቃውሞው ከመበተኑ ከጥቂት ደቂቃዎች በፊት ነበር !
ተቃውሞው አንድ ብሎ በሪያድ ሲጀመር ባሳለፍነውት የአርብ ጸሎት በአንዋር መስጊድና በተለያዩ የሃገሪቱ ከተሞች “የጀሃድ
ሃረካት” ዘጋቢ ፊልም መዘዝ ሆኖ የተበሳጩ ሙስሊማን በነቂስ በመውጣት ከፍ ያለ ተቃውሟቸውን በሰላማዊ መንገድ
አሳይተዋል !
“በጀሃዳዊ ሐረካት” ዘጋቢ ፊልም ጅምሩን ተቃውሞ ሊያበርደውና ሊቀለብሰው ቀርቶ ተቃውሞውን አቀጣጥሎታል፡፡
እውነቱ ይህ መሆኑን መንግስት እንደ መንግስት ጉዳዩን ሊመረምርና ሊያጤነው ይገባል ! ውሃ የማያነሳ መረጃ አቅርቦ ካሳየን
ከኢቲቪ ፤ ከደህንነትና ከፖሊስ ተቋማቱ የሚያገኘውን የመረጃ ተአማኒነት መንግስት በውል ይመረምር ዘንድ ግድ ይለዋል፡፡
በገሃድ ያየነው የተነገረንና የሆነውን መንግስት እንደ መንግስት ይመርምር ! ዘመኑ የደረሰበትን እድገትና የትውልዱን የማሰብ
ደረጃ ካለማገናዘብ ፤ ካለበቂ ጥናትና በማን አለብኝነት የሚሰሩት “ጃህዳዊ ሐረካት” እና ተመሳሳይ ዘጋቢ ፊልሞች መፍትሄ
ሳይሆኑችግሩን አቀጣጣይ መሆናቸውን መንግስት ልብ ሊል ይገባል፡፡ “ጃህዳዊ ሐረካት” ከተለቀቀ ወዲህ በመገናኛ ብዙሃን
በግላጭ ሃሳባቸውን በመግለጽ የምናውቃቸው ወንድሞች አፍናውን በመፍራት ስም፤ አድራሻና ፎቶ ሳይቀር ለመቀየር
የተገደዱት ወደው አይመስለኝም፡፡ የስለላ ተቋሙ ጭፍን አካሔድና ጥርጣሬ ነግሶ ይህን ለማድረግ መገደዳቸውን እየነገሩን ነው
፡፡ “መብታችን ተነካ!” የሚሉ ዜጎች ህቡዕ መጓዝ ከጀመሩ አደጋው ብዙ ነው፡፡ ከዚህ አልፎ ህቡዕ መደራጀቱ በኢትዮጵያ ጂሃድ
እውን ይሆናል ከሚልና ወደ ለየለት የጀሃድ ጦርነት ጥሪ ይሸጋገራል ባልልም ሀገር በተቃውሞ ሲታመስ ሊደርስ የሚችለው
የኑሮ ምስቅልቅል ብቻ ሳይሆን ልዩነቱ አድጎ ልንፈታው ወደማንችለው አደጋ እንዳይጨምረን ያሳስበኛል፡፡ ይህን ሰሞን ቀን
በየፌስ ቡክ ገጾቻችን “ጂሃድ ጂሃድ ” የሚሉ መጣጥፎችንን ብቻ ሳይሆን የተለያዩ የጀሃድን አስፈላጊነት የሚያስተምሩ
መታጥፎች እያነበብን ነው ፡፡ ጥንቃቄ ካልተደረገ አደጋው ብዙ ነው ፡፡ መንግስት እንደ መንግስት ተቃውሞን በሃይል
ለመግታት ከመሞከር ይልቅ የተቃውሞ አንድምታውን በውል አጢኖ የሰከነ ምላሽ በመስጠቱ ረገድ ሊያተኩርበት ይገባል፡፡
መንግስት ሆደ ሰፊ ሆኖ በመቻቻል ጥያቄዎችን ሊመረምርና መፍትሄ ሊሰጥ ይገባል ባይ ነኝ እንደ ዜጋ ! ይህ መሆን ካልቻለ
ወዳልተፈለገ የልዩነት አዙሪት እንዳንገባ ጥንቃቄ ማድረግ ከሁላችንም ይጠበቃል ፡፡ በሃይማኖት ጉዳይ ጠልቀን ከመግባያችን
በፊት ስንዴውን ከእንክርዳዱ እንለይ ዘንድ ግድ ይለናል ! ብዙሃኑን ከጥቂቶች መለየት የመንግስት ታላቅ ሃላፊነት ነው ! እናም
መንግስት ይህን ማድረግ ካልተቻለ ግን ኢትዮጵያ ባትጠፋም ልጆችዋ እንደከፋን እንደተለያየን መኖር ግድ ሊሆንብን
እንገደዳለን ! እስልምና ፤ክርስትናና የተለያዩ ሃይማኖቶችን መከተል የመለያያታችን አንድነት ውበት ናችው ! ልዩነታችን ጌጥ ፤
የኢትዮጵያና ኢትዮጵያውያን ክብር ኩራት እንጂ መለያያ መጠፋፊያችን አይደሉም ፤ አይሆኑም ! ይህ እንዳይሆን ደግሞ
መንግስት ትልቁን ሃላፊነት መወጣት ይጠበቅበታል ! አንድየ ከከፉ ይሰውረን ! እግዚአብሔር ኢትዮጵያን ይባርክ !
ቸር ይግጠመን !
የካቲት 2. 2004

ሚስት ነኝ ሚስት እፈልጋለሁ!

ሚስት ነኝ ሚስት እፈልጋለሁ
ባለታሪኳ
ትላንት ልብን ከሚያደክም የሶስት ሰዓት ስብሰባ በኋላ ለዓርባ አምስት ደቂቃ ያህል ነድቼ ነበር ከምሽቱ ሶስት ሰዓት ቤቴ የገባሁት፡፡ ባለቤቴን ከልጆቹ ጋር እየተጫወተ አገኘሁት፡፡
ቦርሳዬን ወርወር አድርጌ ‹‹እርቦኛል ራት እፈልጋለሁ፤›› አልኩኝ፡፡
ሞግዚቷ አንገቷን አቀረቀረች፡፡ ‹‹ምነው?›› አልኋት ገርሞኝ፡፡ ‹‹ሰራተኛዋ ሄዳለች፤ ራት አልተሰራም፡፡›› አለችኝ፡፡ መቼም የዚህ አገር የቤት ሰራተኛ እና የዚህ አገር ዋጋ ያለማስጠንቀቂያ ኾኖል የሚወጡት፡፡
ምን ራት ብቻ ጠዋት ልጆቹ ወደ ትምህርት ቤት ይዘውት የሚሄዱትንም መስራት አለብኝ ለካ፡፡
ጓዳ ገብቼ ጉድ ጉድ ስል
ሞግዚቷ፣‹በርበሬ አልቋል፤› አለችኝ፡፡ በዚህ ብታበቃ ምን ነበረበት፡፡ በቤቱ ውስጥ ያላለቀ ነገር የለም፡፡ ምን ማድረግ ይቻላል? የቤት ሰራተኛ እንጂ የሰራተኛ ልብ መቅጠር አይቻል፡፡
ደመወዝ መጨመር እንጂ ህሊና መጨመር አይቻል፡፡
እየተነጫነጭኹም፣ እየተማረርኹም የምችለውን ያህል ማሰናዳቴን ቀጠልኹ፡፡ በመካከል ግን አንድ ሐሳብ መጣብኝ፡፡
ምግብ እንደሌለ ከታወቀ እኔን መጠበቅ ለምን አስፈለገ?
ባለቤቴ ወደ ጓዳው ገባ ብሎ ለምን ሰርቶ አልጠበቀኝም? ሁለታችንም ስራ ነው የዋልነው፡፡
ሁለታችንም ልጆቻችን በልተው ማደር እንዳለባቸው እናውቃለን፡፡
ሁለታችንም በጾታ እኩልነት እናምናለን፡፡
የሁለታችንም የትምህርት ደረጃ ተመሳሳይ ነው፡፡ ምክንያቱ አንድ ብቻ ይመስለኛል እርሱ ባል እኔ ሚስት መሆናችን፡፡
ከእርሱ በላይ እንዲያውም እኔ ነኝ ስደክምና ስታክት የዋልኩት፡፡ እኔም እንደ እርሱ ሚስት ቢኖረኝ ምን አለበት ብዬ ተመኘሁ፡፡
ገንዘቤን በሙሉ ሰጥቻት በታማኝነት ቤቴን የምታስተዳድር፣ በርበሬውን፣ ሽሮውን መጥና፣ ደቁሳ፣ አዘጋጅታ፣ ጤፉን መርጣ፣ ገዝታ፣ አስፈጭታ፣ ቅቤውን አንጥራ፣ ቅመማ ቅመሙን መጥና፣ በቤቴ ውስጥ ምን ጎደለ ምን አለ ብዬ ሳልጨነቅ እንዲሁ ያለሐሳብ የምታኖረኝ ሚስት ብትኖረኝ እኔስ እጠላለኹ እንዴ?
የቤት ሰራተኞች እንኳን ከባሎች ይልቅ ሚስቶችን ይጠላሉ፡፡ ወጥተው እንኳን ሲሄዱ፣
‹‹እርሷ ናት እንጂ እርሳቸውማ የእግዜር ሰው ናቸው ከአፋቸው አንዲት ነገር አትወጣም፤››
ብለው ባሎችን ነው የሚያመሰግኗቸው፡፡ ጨቅጫቃ፣ ነገረኛ፣ ገብጋባ፣ በትንሹ የምንናገር ተደርገን የምንቆጠረው እኛ ሚስቶች ነን፡፡ ከእነርሱ ጋር ክፉ ደግ የምንነጋገረው እኛው ነን፡፡ ታዲያ ይህን ሁሉ ጥርግርግ አድርጋ ወስዳ የምትጨቃጨቅልኝ፣ ስድቤን ወስዳ ምስጋናውን የምትሰጠኝ ሚስት ብትኖረኝ እኔስ እጠላለኹ እንዴ፡፡
በርበሬ ተራ፣ ሽንኩርት ተራ፣ ቅቤ ተራ፣ አትክልት ተራ፣ ምናለሽ ተራ ፣ እህል በረንዳ፣ ሸቀጥ ማከፋፈያ ሄዶ፣ ተከራክሮ እና መርጦ ለመግዛት የግድ ሚስት መኾንን ይጠይቃል?
አንዳንድ ጊዜኮ ይገርማችኋል ባሎች፡
በአስር 10 ብር የሚገዙትን ሚስቶች በአምስት 5 ብር፣
ባሎች 100 ብር የሚያወጡበትን ሚስቶች በ40 ብር፣
ባሎች 50 ብር የሚያወጡበትን እኛ በ20 ብር ገዝተን እንመጣለን?
ለምን? እነርሱ ግዴለሽ ስለሆኑ እና እኛ ስለምንጠነቀቅ?
ወይስ
እኛ ገብጋባ ኾነን እነርሱ ቸር ስለሆኑ?
ለመሸከም፣ ስራ መስራት እና ዕቃ ለመሸጥ የሚመጡ ሰዎች እንኳ፣
ከእኛ ከሚስቶች ይልቅ ከባሎች ጋር መነጋገርን ይመርጣሉ፡፡ እናም ዘወር ሲሉ፤ ሚስቲቱ ግግም አሉ እንጂ ባልየውስ ዓርፈው ነበር፡፡ ይሏችኋል፡፡ ይህን ስትሰሙ ባልኾናችሁ ‹‹ማረፍ›› አያምራችሁም፡፡
እንደ እውነቱ ከሆነ ብዙ ባሎችኮ የቤታቸውን ሳሎን እና መኝታ ቤት እንጂ ጓዳውን አያውቁትም፡፡
አንጀት የሚልጠው እና ጨጓራ የሚያቆስለው ደግሞ ጓዳው ነው፡፡
ስራ ውላችሁ፤ደክሞችሁ ርቧችሁ፣ታክቷችሁ ወደ ጓዳ እንደ መግባት ያለ ቅጣት በትዳር ውስጥ የለም፡፡ አንዱ ተሰብሮ፣ ሌላው ተደፍቶ፣ ምግቡ ክፍቱን ተቀምጦ፣ ዕቃው ተደበላልቆ፣ ለዓመት የተባለው በስድስት ወር፣ ለወር የተባለው በሳምንት አልቆ፣ ጨው ስኳር ጋራ፣ ሩዝ ከክክ ጋራ ተደበላልቆ ስታገኙት እርር ድብን ትላላችኹ፡፡ አትተውት ነገር ቤታችሁ ነው፤ አትናገሩ ነገር ሰሚ እንጂ አድማጭ አታገኙም፡፡ በዚህ ጊዜ ነውኮ ባል መኾን የሚያምራችኹ፡፡
ሚስቴ ከቤት ሰራተኛዋ ጋር ስትጨቃጨቅ እና ስትጣላ፤ ይህ ለምን አለቀ፤ ይህ ወዴት ሄደ፤ ይህን ለምን አልተናገራችኹም፤ ይህን ማን ሰበረው ፤ ይኽኛው ወጥ ለምን ፍሪጅ ውስጥ አልገባም፤ ይኽኛው ለምን ተበላሸ፤ ለምን አልተቦካም፤ ለምን አልተጋገረም፤ ለምን አልተፈጨም፤ እያለች
ሚስቴ ስትከራከር እኔም ባል ኾኜ አትጨቃጨቂ በቃ ተያት በትንሽ በትልቁ መነታረክ ምን ያደርግልሻል ደመወዟን አትንኪባት እያልኩ መምከር ናፈቀኝ፡፡
ሌላው ቀርቶ
ከልጆች ጋር ብሉ አትብሉ፣
ልበሱ አትልበሱ፣
ታጠቡ አትታጠቡ፣ ይህን አድርጉ አታድርጉ ፣ ቅባት ተቀቡ አትቀቡ እያሉ መከራከር እና ሲብስም መጨቃጨቅ የሚስቶች ስራ ነው፡፡
እኔ ለምን አባቴን እንደ ወደድኹ አሁን ነው የገባኝ፡፡ የሚጨቀጭቀውን ድሮስ ማን ይወድዳል፡፡ ባሎች እንደሆነ መጫወቻ መግዛት፣ ከረሜላ እና ቸኮሌት ማምጣት፣ መዝናኛ መውሰድ እና ማጫወት ነው የሚችሉበት፡፡ ታዲያ የአሁን ዘመን ልጆች አባታቸውን ቢወድዱ ይፈረዳል፡፡ እኔም ልጆቼን የምትለብስ፣ የምታስጠና፣ የምታጥብ፣ ተከራክራም ይሁን ተጨቃጭቅ ልጆቼን የምታበላ ሚስት ብትኖረኝ ምናለ? እኔም ባል ኾኜ ልጆቼ ያለጭቅጭቅ የሚበሉትን ቸኮሌት እና አይስክሬም ብቻ እየዛኹ ልጆቼ በወደዱኝ፡፡
‹‹ጹድቁ ቀርቶ በወጉ በኮነነኝ›› አለች እናቴ፡፡ ብቻዬን የወለድኋቸው ይመስል
ለልጆቼ ምን መጠጣት ፣ምን መብላት፣ ምን መልበስ እንዳለባቸው እንኳን የምወስነው እኔ ነኝ፡፡
ባሌማ መብላታቸውን እንጂ ምን እንደሚበሉ የሚያውቅ አይመስለኝም፡፡ ምንም ያህል ስራ ቢበዛብኝ ቤት ደውዬ ማን ምን እንደበላ ማን ምን መብላት እንዳለበት ለሞግዚቷ መመርያ መስጠት አለብኝ እኔ እኮ ነኝ ፡፡
ልጆቼን ሰውነታቸውን ነካክቼ
ማተኮሳቸውን እና መቀዝቀዛቸውን
በሰውነታቸው ላይ ለውጥ መኖሩን እና አለመኖሩን የማየው እንኳን እኔ ነኝ፡፡
አብረን ቤት ብንገባም እንኳን ዛሬ እንዴት ኾነው ዋሉ? የሚለው የስስት ጥያቄ ከእኔ ነው የሚመጣው፡፡ እና ይህን ሁሉ ሸክም ተሸክማ ያለ ሐሳብ እንድኖር የምታደርገኝ ሚስት ባገኝ መመረቅ አይደለም ትላላችኹ፡፡
ወልጄ ለምን አልጠየከኝም፣ ልቅሶዬ ላይ የእዝን እንጀራ ለምን አላመጣኽም ቡና አብረኽኝ ለምን አልጠጣኽም፣ ስትወጣ ለምን ሰላም አትለኝም፣ ለምን ልቅሶ ቤት ሄዶ፣ ጓዳ ገብቶ ወጥ አልሰራም፣
ሰርግ ቤት ተጠርቶ ለምን ስራ አላገዝንም? ብሎ ባልን የሚቀየመው አላጋጠመኝም፡፡
ልቅሶም ሰርግም ብቅ ብሎ ከታየ እንደ ትልቅ ውለታ ይቆጠርለታል፡፡ ሚስት ስትኮን ግን ብዙ ይጠበቅባችኋል፡፡ እናም አንዳንድ ጊዜ ሰርግ እና ልቅሶ ላይ ዕድር እና አራስ ቤት እኔን ኾና የምትጠይቅልኝ፣ የሚወሰደውን ወስዳ የሚሰራውን ሰርታ፣
የሚከፈለውን ከፍላ ውለታ የምትገባልኝ እኔም ሲመቸኝ ብቅ እያልኩ ኮራ ብዬ በኀዘንተኛው መካከል ጋቢዬን ለብሼ ከቻልኩም ካርታ ተጫውቼ፣ ሰርግ ላይ ከቻልኩ አስተናግጄ ካልቻልኩም እንደ አድባር መሀል ላይ ጉብ ብዬ ባል ኾኜ መመስገን አማረኝ፡፡
ሌላው ቀርቶ ባል በሚስት ቤተሰቦች ዘንድ ከሚያጋጥመው ማኀበራዊ ችግር ይልቅ ሚስቶች ከባል ዘመዶች የሚያጋጥማቸው ችግር ይብሳል፡፡
አንዳንድ ጊዜ ሚስት መኾን ብቻውን እንደ ነገረኛ፣ ሰው በቤቷ ለመቀበል እንደማትፈልግ ፣ አንደ ገብጋባ ያስቆጥራል፡፡
ምናልባትም ለቤቷ መልፋቷ ሳያንሳት በቤቷ ላይ ሌላ ሰው ሲያዝዝ እና ሲያላሽ ስለሚይናድዳት ሊሆን ይችላል፡፡
አንድ ሰውኮ በቤታችሁ ጥልቅ ብሎ ገብቶ ስልጣኑኑ ይወስድና ኃላፊነቱን የቆየ መጥፎ አመለካከት የመጣም ሊኾን ይችላል፡፡ በዚያም ተብሎ በዚህ ሚስት በባሏ ብቻ ሳይሆን በዘመዶቹም ለመወደድ የመጣር ተጨማሪ ስራ አለባት፡፡
ያለበለዚያ እርሱማ የእግዜር በግ ምኑን ያውቀዋል እርሷ ናት እንጂ ትባላላችኹ፡፡ አይ ሚስት መኾን በተለይማ ወይ የሚረዳ ወይ የሚረዳ ባል ካልተገኘ፡፡
አንዳንድ የስራ ባልደረቦቼ እገሊትኮ ባልዋ እንዴት የተባረከ መሰላችሁ፣ ገንዘቡን ሁሉ አምጥቶ ለርሷ ነው የሚይስረክባት፡፡ እንዲያውም ከርሷ ጠይቆ ነው የሚወስደው እያሉ ሲያመሰግኑ እሰማለኹ፡፡
በርግጥ ዋርካ በሌለበት እምቧጭም ዋርካ ነው፡፡ ግን ምናለ እኔም ደመወዜን በሙሉ አምጥቼ አስረክቤ፣ ስፈልግ ከእርሱ እየወሰድኩ ባሌ ቤቱን ባስተዳደረልኝ፡፡
እኔም ባል ሆኜ፣ ገንዘብ ብቻ ሰጥቼ የቀረው ነገር ሁሉ ተዘጋጅቶ በጠበቀኝ?
ባሎችኮ ቤታቸውም ገንዘብ ሰጥተው ምግብ ይበላሉ፣ ሆቴልም ገንዘብ ሰጥተው ምግብ ይበላሉ፡፡
ሚስት ስትሆኑ ግን ቤታችሁ ውስጥ በገንዘብ ብቻ ምግብ አታገኙም፡፡ ጉልበት እና ጨጓራችሁንም ካልጨመራችሁ በቀር፡፡
ይህን ሁሉ ሳብሰለስል ሳላስበው ሰዓቱ ነጉዷል ለካ፡፡ ስራዬን ጨርሼ ወደ ሳሎን ብቅ አልኩ፡፡ ልጆቼ ፈንግል አንደያዘው ደሮ እዚህም እዚያም ወድቀው ዕንቅልፍ ወስዷቸዋል፤ ባለቤቴም ሶፋው ላይ ጋደም ብሎ ያለሐሳብ ተኝቷል እርሱ ምን አለበት በደህና ጊዜ ባል ሆኗል፡፡
ከዚህ ምን እንማራለን
ባል ከሚስቱ የሚስትነትን እንጂ የእናትነትን ፍቅር አይፈልግም
ሰዎች ብዙውን ጊዜ ስለትዳር በቂ እውቀት ሳይኖራቸው ይጋባሉ፡፡ ሰው እየገጩ፣ ልጆቻቸውን እየገጩ፣ ሚስቱን እየገጨ፣ ባሏን እየገጨች፣እየተገጫጩ ነው የሚኖሩት፡፡ ስታያቸው ግን ጤነኞች ይመስላሉ፡፡
ሴትና ወንድ በአስተሳሰብ ደረጃ ይለያያሉ
መታየት ያለበት ነግር ቢኖር
ወንድ የሚባል ሰው አለ፤ሴት የምትባል ሰው መኖራቸው ነው፡ በግልጽ ይታያል
ወንድ የሚያስብበት መንገድ፣ሴትም የምታስበበት መንገድ አለ፡፡ ወንድ እንደ ወንድ፤ ሴትም እነደ ሴት የተሰጣቸው ማንነት አለ፡፡ ይህም ይመስለኛል ወንድ ሴትን አብሮ ያኖራቸው ነገር፡፡
ሁለቱም ተመሳሳይ ከሆኑ ምን ፍለጋ ነው የሚጣመሩት የተለያዩ አስተሳሰብ ስላላቸው ነው፡፡ አንድ የሚያደርጋቸው የአስተሳሰብ መጠን አለ በትክክል ወንድና ሴት የተለያየ የአስተሳሰብ መጠን አላቸው፡፡
ወንድ ልጅ መከበር ይፈልጋል፡ የኢትዮጵያዊም አውሮፓዊም ወንድ ይህን ይፈልጋል፡
ወንድ ልጅ ችግር ሲገጥመው የሚፈታበት የራሱ መንገድ አለ፡፡ ወንድ ልጅ ደግሞ ተፈጥሮው ጠባቂ ነው፡፡ በቤቱ ውስጥ ማገር የመሆንና ሁሉን የመጠበቅ ስጦታ ተሰጥቶታል፡፡
ሴት ልጅ ደግሞ በተፈጥሮዋ እንክብካቤ ትፈልጋለች፡ በቃ እንቁላል ነች፣ ንግስት ነች፣ ሴት መደመጥ በጣም ትፈልጋለች ይሄ ተፈጥሮዋ ነው፡
የማዳመጥና የመደመጥ ክህሎታቸው ተፈጠሯዊ ነው፡ ወንድ ልጅ ይህ ተፈጥሮ የለውም ፡፡ መረጃ ሲሰጥህ እንኳን ጠቅለል አደረጎ ነው፡፡
በዝርዝር የሚያስቀምጠው ነገር የለም፡፡ የተ ነበርክ ስትለው እዚህ ቦታ ነው የሚልህ፡፡ ሴቷ ግን እዚያ ሄጄ፣ እንትናን አግቼው እንትን ጋብዞኝ ፍቀረኛውም አብራው ነበረች መዓት ነግር ልትልህ ትችላለች፡፡
ሚስት እንደ ሚስት ባልም እንደ ባል አለመሆኑ ይመስለኛል፡፡ ባል ከሚሰቱ የሚስትነትን እንጂ የእናትነትን ፍቅር አይፈልግም!