Girma Wolde-Giorgis:”Assab belongs to the Afar and Afars are Ethiopians”

SBS

Former Ethiopian President Girma W/Giorgis on SBS radio says:


” Now Assab is in the hands of Eritreans, but it shouldn’t be like that because Assab belongs to the Afar and Afars are Ethiopians. . . Afars can’t be Eritreans, they were free people from Ethiopian side . . .”

Listen here from SBS Radio

This is what he said in 2002/1994 ETH

Source:People Daily

Last updated at: (Beijing Time) Tuesday, April 09, 2002

Ethiopian President Not Supports Acquiring of Assab Port

Ethiopian President Girma Wolde-Giorgis has expressed his disagreement to acquire Assab portby saying that the issue raised by some parties under the cover that Ethiopia is a land locked country should not have connection with the Ethio-Eritrea border demarcation.
Ethiopian President Girma Wolde-Giorgis has expressed his disagreement to acquire Assab portby saying that the issue raised by some parties under the cover that Ethiopia is a land locked country should not have connection with the Ethio-Eritrea border demarcation.In a recent interview with local newspaper issued on Monday, the president noted the measures taken by the incumbent governmentwith regard to Assab “are correct and consistent with principles.”In his first public remark on the issue of border demarcation since he took the post of president last year, Girma said, “you cannot claim that something is not yours and go to war.”

Accepting peacefully the ruling of the Hague tribunal due to beannounced later would enable the country to accelerate its economic development, he stressed.

Economic development and social transformation are unthinkable in the absence of peace and stability, he said, adding that Ethiopians should pool their ideas and resources to reduce the level of poverty in the country.

The Boundary Commission is expected to declare the border demarcation on April 13, and some Ethiopian opposition parties have launched rallies in some cities of the country to protest against the coming decision, saying the Assab port in Eritrea should be returned to Ethiopia.

Demanding Assab port means derecognizing the sovereignty of Eritrea and thereby violating the U.N. charter which strictly prohibits and condemns any attempt at forcible occupation of an independent state’s territory.

 

ኃይልዬ ታደሠ የኢትዮጵያ አምላክ Hailye Tadesse – yeEthiopia Amlak

ኃይልዬ ታደሠ በአዲሱ “የኢትዮጵያ አምላክ” በሚለው ዘፈኑ ውስጥ ከቋጠራቸው ስንኞች ውስጥ:-

“ነፃነት ተገፎ ድንበር አስቆርሶ
አያልፍ ለትውልድ ባርነት አውርሶ”

http://youtu.be/gnHcrlp4X8U

 

ኢትዮጲያ የምትባል አገር የማልሰማበት አገር ውሰዱኝ ! Alex Abreham

By Alex Abreham

በናታችሁ ከዚች አገር አውጡኝ ! በቃ ሱማሌም ኧረ ምናምን ሱዳንም ይሁን ብቻ ኢትዮጲያ የምትባል አገር የማልሰማበት አገር ውሰዱኝ !
አሁን ቤት አከራየ መጣና የቤት ኪራይ አምስት መቶ ብር ጨምር ሲለኝ ቤት አከራየ ሳይሆን ኢትዮጲያ አስጠላችኝ !! የቤት ኪራዩ ብቻ እንዳይመስላችሁ የግፍ አገር ናት ! ምንም ፍትሃዊ ነገር የላትም ! እንደድመት ወልዳ የምትበላ ጉድ !

እስካሁን የኖርኩበትን እድሜ ቢያንስ ሶስት አራተኛውን አንገቴን ደፍቸ በመማር አሳልፊያለሁ በተማርኩት ሙያም እችን ለዛዋ የተሟጠጠ አገር አገልግያለሁ ! በምሰራው ስራ በመስሪያ ቤቴ የተመሰገንኩ ባለሙያ ነኝ ! ግን አንድ ቀበሌ ለቀበሌ እያውደለደለ በአፉ የሚኖር መሃይም የቤት ባለቤት አፉን ሞልቶ ወይ ልቀቅ ወይ አምስት መቶ ብር ኪራይ ጨምር ይለኛል! የዛሬ አራት ወር ሁለት መቶ ብር አስጨምሮኛል እውነቴን ነው በአገሬ ላይ የማልጠቅም ዜጋ የመሆን ስሜት ነው የተሰማኝ ፡፡

እኔ ማንም ብር እንዲሰጠኝ አልፈልግም ሰርቸ ማግኘት የምችል ጤነኛ የተማርኩ ወጣት በመንግስት ችግር ምክንያት እንደለማኝ መመፅወት አለብኝ እንዴ እንደገና ለፍተው ያሳደጉ ቤተሰቦቸ ለእኔ ብር መደጎም አለባቸው እንዴ እንደህፃን ልጅ ለኔ ልብስ መግዛት አለባቸው እንዴ…. ውለታየን መክፈል ቢያቅተኝ እንኳን እንዳልችል እንዴት በማንም ሆዳም እገፋለሁ መብቴን እቀማለሁ

አንድ የሱማሌ ወይም የኤርትራ ስደተኛ ከእኔ የተሸለ እኔ አገር ላይ ይኖራል ! እንደዜጋ መብራት ውሃ በስርአት አላገኝም ያውም ከፍተኛ የሚባል የስራ ግብር እየከፈልኩ ! እንደዜጋ ትክክለኛ መረጃ አላገኝም ! እንደዜጋ ደፍሬ ስለችግሬ አላወራም ! ላቤን ጠብ አድርጌ የምኖር ዜጋ አባትና እናቴ እድሚያቸውን ሙሉ በፍፁም ታማኝነትና ትጋት ያገለገሏት ኢትዮጲያ ላይ እንደሁለተኛ ዜጋ መንከራተት እጣ ፋንታየ ሁኗል …… ኧረ የምን ሁለተኛ ምንም ደረጃ የሌለኝ ውዳቂ ዜጋ ነኝ እንጅ ! በእውነት ግን እኔ ትላንት ዩኒቨርስቲ ሁኘ ኢትዮጲያን የብርሃን ኩሬ አድርጌ ሳልም የነበርኩት ልጅ ነኝ …..ኦህህህ እውነቴን ነው እንደዛሬ መሮኝ አያውቅም !

ከአቅሜ በላይ እየሰራሁ የለፋሁበት ደመወዝ አምስት ሳንቲም ለመንግስት ግብር በማይከፍል ቤት አከራይ ሲቀማ መንግስት አድገሃል ልማት ምናምን እያለ ይቀባጥራል ! ወጣት ነኝ ጥሩ መልበስ ጥሩ መመገብ አለብኝ ለፍቸ ያገኘሁትን ብር በስርአት ልጠቀምበት መብት አለኝ …. በተዘዋዋሪ የመንግስት ስንፍና እና ሃላፊነቱን አለመወጣት ለማንም ስግብግብ መጫወቻ እያደረገን ነው !

የዛሬ አርባ አመት እች አገር እዛ ትድረስ እዚህ ስሜት አይሰጠኝም ወጣትነቴን እንደቀልድ በባዶ ተስፋ የምትበላ አገር ለኔ ምኔ ናት ጠልቻታለሁ አገሬን !! በውጭ አገር የሚኖሩ እንዴት የታደሉ ናቸው ! እየሸሹ ባህር የበላቸው ከፎቅ የተወረወሩ ምንኛ እድለኛ ናቸው !

ኢትዮጲያ ተስፋችንን የምታኮስስ ተስፋ ቢስ አገር ናት !! እንደዜጋ በደልን ድህነትን ፍርሃትና መሸማቀቅን ብቻ የምታሸክም አገር ናት አገሬ ! ሽ አመት በባርነት መኖር ይሻላል ኢትዮጲያ ውስጥ ከመኖር ! ስንት ጊዜ ችግሯን እንዳላየን በእናትነት ሸፋፍነን አለፍናት ስንት አመት ሙሉ ቻልን በባዶ ተስፋ ተምራችሁ ያልፍላችኋል እያሉን ዶክተር ብትሆን ኢንጅነር ምን በትሆን ምን ወፍ የለም ! ሙሰኛ አጭበርባሪ ውሸታም አስመሳይ ስትሆን ከሰውነት ክብርህ ዝቅ ስትል ብቻ እንደለማኝ ፍርፋሪ ትወረውርልሃለች !

አገሬን ጠልቻታለሁ ! ሰርቸ ለምኖር ለፍቸ ለምኖር ለእኔ ኢትዮጲያ ያደረገችልኝ ነገር ቢኖር የለፋሁበትን ገንዘብ በስግብግብነት መቀማት ብቻ ነው ! እግዚአብሄር እዚች አገር ላይ የፈጠረኝ ለምንድን ነው ? ማንም ሰው ከዚህ አስቀያሚና የግፍ የበደል የአድሎ አገር ቢያስወጣኝ እግሩ ላይ ወድቄ ከመሳም አልመለስም ! አገሬን ጠልቻታላሁ ! መልስ የሚሰጥ የሚጨነቅልኝ መንግስት የለኝም !! አገሬ ዛሬ በውስጤ ሙታለች !

“ለኢትዮጵያ ህዝብ አማራጭ ሆነን እንቀጥላለን” -EDP

“ለኢትዮጵያ ህዝብ አማራጭ ሆነን እንቀጥላለን” 

-By    Andebet Kassa

በኃይለስላሴ ዘመነ መንግስት የኢትዮጵያ የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር፤ በአሜሪካ የኢትዮጵያ አምባሳደርና የገንዘብ ሚኒስትር ከነበሩት አቶ ይልማ ደሬሳ የተወለዱት ወይዘሮ ሶፊያ ይልማ፤ ላለፉት 22 አመታት በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ ተሳትፈዋል፡፡ በአሁኑ ሰዓትም ለሁለተኛ ጊዜ የኢዴፓ ምክትል ፕሬዚደንት ሆነው በመመረጥ ፓርቲውን እያገለገሉ ነው፡፡ በደርግ እጅግ የተጎዳሁ ነኝ የሚሉት ወይዘሮ ሶፍያ፤ ኢህአዴጐችን “ደርግን የጣሉ ጀግኖች” ብለው እንደተቀበሏቸው ጠቅሰው፤ወደ ፖለቲካ የገባሁትም እነዚህን ሰዎች ለማገዝ ነበር ይላሉ። “በኋላ ግን ተስፋ መቁረጥ መጣ” ባይ ናቸው። የአዲስ አድማስ ጋዜጠኛ ኤልሳቤት እቁባይ፤ ከፖለቲከኛዋ ሶፊያ ይልማ ጋር ባደረገችው ቃለምልልስ፣ተስፋ ያስቆረጣቸውን ጉዳይ ጨምሮ በአጠቃላይ በአገሪቱ ፖለቲካዊ ጉዳዮች ዙርያ አነጋግራቸዋለች፡፡

የአገራችን የምርጫ ሥርዓት በሚያሳዝን መልኩ እየተበላሸ ነው…
ኢዴፓ ቅንጅትን አፍርሷል የሚለውን ውንጀላ አይቀበሉትም …
ንጉሱ “ጀግና መሪ”፣ ደርግ “የጥፋት መልዕክተኛ”፣ ኢህአዴግስ?

ስለራስዎ ይንገሩኝ….
ተወልጄ ያደግሁት አዲስ አበባ ነው፡፡ በትንሽነቴ እንግሊዝ ትምህርት ቤት ነው መማር የጀመርኩት፡፡ በዘጠኝ አመቴ አባቴ በአሜሪካ የኢትዮጵያ አምባሳደር ሆነው በመሾማቸው እዚያም ተምሬአለሁ፡፡ አባቴ ወደ ኢትዮጵያ ሲመለሱ ኮከበ ፅባህ ትምህርት ቤት ትምህርቴን ቀጠልኩ። አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲም ገብቼ ተምሬያለሁ፡፡ ነገር ግን ትምህርቴን ሳልጨርስ ወደ ጀርመን ሄድኩ። ምዕራብ በርሊን ውስጥ የጋዜጠኝነት ትምህርት ተምሬ መጣሁ፡፡ ትምህርቴን ከጨረስኩ በኋላ የጋዜጠኝነት ሙያን ስለምወድ በጋዜጠኝነት መስራት ጀመርኩ፡፡
ስራው እንዴት ነበር?
ስጀምር ሪፖርተር ነበርኩ፡፡ መንገድ ለመንገድ እየሮጥኩ ዜና እሰራለሁ፡፡ ጫማ ጠራጊውም ባለሱቁም ያውቀኝ ነበር፡፡ ባለፍኩበት መንገድ ሁሉ ሶፊ እያሉ ይጠሩኝ ነበር፡፡ ሬዲዮ እያለሁ ወይዘሮ ሮማንን አውቃቸው ነበር፡፡ ከሳቸው ስር ስር እያልኩ ሙያዬን በተግባር አዳብሬያለሁ፡፡ በጣም የማደንቃቸው ጋዜጠኛ ነበሩ፡፡ ነገር ግን የኔ ፍቅር የህትመት ጋዜጠኝነት ላይ ስለነበር በወቅቱ የነበሩትን ባለስልጣኖች ተማፅኜ ወደ ሄራልድ ጋዜጣ ተዛወርኩ፡፡ እዛም ስጀምር ሪፖርተር ነበርኩ፡፡ በኋላ ላይ ሹመት አገኘሁና የሴቶች አምድ አዘጋጅ ሆንኩ፡፡ ከዛ በአጋጣሚ የጋዜጣውን ኤዲተር አገባሁ፡፡ አንድ መስሪያ ቤት ውስጥ አንድ ላይ መስራቱ አይመችም ብዬ እኔ ሥራ ቀየርኩ፡፡
በስራዎ ከባለስልጣናት ጋር ተጋጭተው ያውቃሉ?
የሚያጋጭ ስራ ሰርቼ አላውቅም፡፡ መንግስት ነኝ ብሎ የተቀመጠውን መንካት ወንጀል እንደሆነ አውቅ ነበር፡፡ እኔ ብዙ አደላ የነበረው ለማህበራዊ ጉዳዮች ነው፡፡ በጃንሆይ ጊዜ ብዙ ብሩክ ነገሮች ቢኖሩም ብዙ ጥሩ ያልሆኑ ነገሮችም ነበሩ፡፡ ጥሩ ካልሆኑት ውስጥ አንዱ የፕሬስ ነፃነት አለመኖር ነው፡፡
ከዚያስ የት መስራት ጀመሩ?
የኢትዮጵያ ቴሌኮሙኒኬሽን መስሪያ ቤት ውስጥ በህዝብ ግንኙነት ቦታ ገባሁ፡፡ ረጅም አመት የሰራሁት ቴሌ ነው፡፡ ከዛ በኋላ ግን ስራውን ተውኩትና እቤቴ ቁጭ አልኩ፡፡ ከዛም ሲስተር ጀምበር ተፈራ ለሚሰሩት ትልቅ ፕሮጀክት ከሌሎች ጋር ተወዳድሬ እንድሰራ ጠየቁኝና እዛም የህዝብ ግንኙነት ሆኜ ለስምንት አመት ከሰራሁ በኋላ፣ ስራውን አቁሜ ቤቴ ቁጭ አልኩ፡፡
ወደ ፖለቲካ እንዴት ገቡ?
እኔ በደርግ መንግስት እጅግ የተጎዳሁ ሰው ነኝ። በልጅነት እድሜዬ ያገባሁት ያልኩሽ ባለቤቴ ደርግ ከገደላቸው “ስልሳዎቹ” አንዱ ነው፡፡ ተገኘ ተሻወርቅ ይባላል፡፡ ከመገደሉ በፊት ምክትል የማስታወቂያ ሚኒስትር ነበር፡፡ ከሱ ቀደም ብሎም አባቴ ታሰሩ። ታመው ለአንድ ሳምንት ያህል ሆስፒታል ከገቡ በኋላ እስር ቤት እንደሞቱ ቁጠሪው፤ ሞቱ፡፡ ከዛም እኔና እናቴ ታሰርን፡፡ እጅግ በጣም አስከፊ በሆነ ሁኔታ ነበር የታሰርነው፡፡ ጣሊያን በሰራው የድንጋይ ንጣፍ ላይ እየተኛን ክፉ ዘመን አሳለፍን። ስታሰር የመጀመሪያ ልጄ በጣም ትንሽ ነበር፡፡ እኔን ከመስሪያ ቤት ስለሆነ የወሰዱኝ ከትምህርት ቤት የሚመልሰው ሰው በማጣቱ፣ ከምሽቱ ሶስት ሰአት ነበር የተገኘው፡፡ ብዙ ችግሮች ላይ ወድቀን ነበር፡፡ ይሄ ቁስል ሆኖብኝ ስኖር ደርግ ወደቀ፡፡ እኔም በምችለው አቅም ለዚች አገር ፖለቲካ ውስጥ ገብቼ መስራት አለብኝ አልኩና በወቅቱ “ኢድሃቅ” የሚባለውን ድርጅት ተቀላቀልኩ፡፡ ወቅቱ ፓርቲዎች እንደ እንጉዳይ የፈሉበት ጊዜ ነበር፡፡ ብዙ ፓርቲዎች ነበሩ፡፡ ያንን አየንና ጠንካራ ለመሆን፣ ለምን ከጠንካራ ፓርቲ ጋር ውህደት አድርገን አንሰራም በሚል፣ በአቶ ልደቱ አያሌው ጋባዥነት “ኢድሃቅ” የወቅቱን “ኢዴአፓ” ተቀላቀለ፡፡ ከዛን ጊዜ ጀምሮ በፓርቲው ውስጥ እያገለገልኩ ነው፡፡
በምን ሀላፊነት?
አሁን ለሁለተኛ ጊዜ የኢዴፓ ምክትል ፕሬዚደንት ነኝ፡፡ በተለያዩ የአለማችን ክፍሎች ፓርቲዬን እየወከልኩ እሄዳለሁ፡፡ ፓርቲያችንን አስተዋውቃለሁ፡፡ የኢዴፓ ጠንካራ ቡድን የሚገኘው እንግሊዝ አገር ነው፡፡
ምርጫ እየደረሰ ነው?
አዎ ኢዴፓ በመተዳደሪያ ደንቡ መሰረት በየሁለት አመቱ ጠቅላላ ጉባኤውን ያደርጋል። የስልጣን ማራዘምም ካለ ጠቅላላ ጉባኤው ይወስናል፡፡ በቅርቡም ጠቅላላ ጉባኤ ይኖራል፡፡ የስራ ዘመናቸውን የጨረሱ በምርጫ ለሚመጣው ያስረክባሉ፡፡ ይህ እንደ ፖለቲካ ባህል እንዲያዝ እንፈልጋለን፡፡ አንድ ሰው ምንም ያህል ብርቱ እና አዋቂ ቢሆን ከሱ ሌላ የለም ብሎ ማመን ትክክል አይደለም፡፡ በውስጣችን ብዙ ጠንካራ ሰዎች እንዳሉ ስለምናውቅ እድሉ ይሰጣል፡፡ ያለበለዚያ ፓርቲው በአንድ ሰው ብቻ የሚታወቅና የሚታይ ይሆናል። ፓርቲ ደግሞ የግለሰብ ሳይሆን ተስማምተው የሚሰሩ ሰዎች ስብስብ ነው፡፡
የፖለቲካ ጉዞው ምን ይመስላል?
የተቃዋሚው ፖለቲካ በየወቅቱ ይለያያል። አንዴ ጠንካራ ይሆናል፤ ሌላ ጊዜ ይዳከማል፡፡ ለዚህ ከመንግስት በኩል ያለው ተፅእኖ ከፍተኛውን ድርሻ ይይዛል፡፡ ፖለቲካውን ከተቀላቀልኩ በኋላ ባሉት አመታት የሚያስደስቱም የሚያሳዝኑም ሁኔታዎችን አይቻለሁ፡፡ በጣም አስደሳች የነበረውና በኋላ ሳያምርበት ቀረ እንጂ አራት ፓርቲዎች ሆነው የመሰረቱት ቅንጅት ነው፡፡ ቅንጅት በኢትዮጵያ ህዝብ ትልቅ ተስፋ የተጣለበት ፤ ከህዝብ ትልቅ ፍቅር የተሰጠው ፓርቲ ነበር፡፡ ነገር ግን ያንን ይዞ አልቀጠለም፡፡ ነገሮች ከመበላሸታቸው ጋር ተያይዞ የተፈጠሩ ሁኔታዎች በተለይ በኢዴፓ እና ኢዴፓ ውስጥ ባሉ ግለሰቦች ላይ ማነጣጠሩ ደግሞ እጅግ በጣም ፈታኙ ጉዳይ ነበር፡፡ ኢዴፓ የቅንጅት አፍራሽ ሆኖ ልደቱ አያሌው ላይ የተካሄደውን ዘመቻ ሳስበው፣ ሁልጊዜም እንቆቅልሽ የሚሆንብኝ የኢትዮጵያ ህዝብ ያንን መቀበሉ ነው፡፡ አፍሪካ ውስጥ በሀይል ከማመን ቀጥሎ ትልቁ በሽታ ስም ማጥፋት ነው፡፡ ከኔልሰን ማንዴላ በስተቀር ብዙዎቹ አፍሪካውያን ጀግኖች በተካሄዱባቸው የስም ማጥፋት ዘመቻዎች ነው ተጠልፈው እንዲወድቁ የተደረጉት፡፡ ያ ክፉ ጊዜ ለኢዴፓ የማይረሳ ነው፡፡
ኢዴፓ ቅንጅትን አላፈረሰም የሚሉባቸው ማስረጃዎች ምንድን ናቸው?
ጥሩ ጥያቄ ነው፡፡ በወቅቱ እውነታችንን እንናገር ብንል ማን ተቀብሎን! ቅንጅትን የመሰረቱት ፓርቲዎች ወደ ውህደቱ ለመሄድ ከምርጫ ቦርድ የተሰጣቸውን ሰርተፊኬት እና ማህተም መመለስ ይጠበቅባቸው ነበር፡፡ ኢዴፓ በዛው ውህደቱ ሊካሄድ በታሰበበት ጊዜ ጠቅላላ ጉባኤውን አድርጎ ነበር፡፡ ውህደቱን በተመለከተም ጠቅላላ ጉባኤው የወሰነው ውሳኔ ቅንጅቱ ውስጥ ያሉ አንዳንድ ያልጠሩ ጉዳዮች እስኪጠሩ ድረስ የፓርቲው ሰርተፊኬት እና ማህተም እንዳይመለስ የሚል ነበር፡፡ ይህ ግን ከውህደቱ ሂደት ስለማያግደን እንቀጥል ተባለ፡፡ ከጠቅላላ ጉባኤው ውሳኔ በላይ መሆን እንደማይቻል ሁሉም እያወቁት፣ ውሳኔው በሌላ ተመንዝሮ ከአሉባልታ ጋር ተዳምሮ ዘመቻ ተከፈተብን፡፡ እውነት ሰሚ አጣች፡፡ ህዝቡም እንዴት ብሎ ሳይጠይቅ፤ ምንድን ነው የሆነው ብሎ ሳይመረምር ተቀበለው፡፡ አንዳንድ ጋዜጦችም እውነቱን ስሙ ብንላቸው “የእናንተ እውነት ጋዜጣ አያሸጥም” የሚል ምላሽ ሰጡን፡፡ በፖለቲካ ውስጥ ዋናው ነገር አለመቀደም ነው፡፡ እኛ ለተፈጠረው ነገር አልተዘጋጀንም ነበር፡፡ እነሱ ቀደሙን፡፡ በወቅቱ የቅንጅቱ ሁኔታም ችግር ላይ ስለነበር፣ ነገሮቹን የሚሸከም ይፈለግ ነበር፡፡ ስለዚህ ውድቀቱ ኢዴፓ እና በተለይ ልደቱ ላይ እንዲሆን ተደረገ፡፡ አሁን ድረስ የሚሞግቱኝ ሰዎች አሉ፡፡ ምን አይነት ስር የሰደደ ነገር ነው እላለሁ፡፡ እስቲ መከራከሪያችሁን ወይም እውነታችሁን ንገሩኝ ስል የለም፡፡ ለነገሩ የተወነጀልንበትን ጉዳይ እውነት አድርገነው ቢሆን ኖሮ ምንኛ በከበደን ነበር፡፡ ህዝቡ ሁኔታዎቹን በሂደት እያያቸው፣ ወደ ኢዴፓ እየተመለሰ ያለውም ለዛ ነው፡፡ በወቅቱ እንግዲህ አውቆ የተኛን መቀስቀስ ባይቻልም በብዙ መልኩ ብዙዎችን አሳዝኗል፡፡
ቀጣዩ አገራዊ ምርጫ እየደረሰ ነው፡፡ የኢዴፓ ዝግጅት ምን ይመስላል?
ምርጫ በዲሞክራሲ ላይ የተመሰረተ ነው፡፡ እምነታችን ስለሆነ በምርጫ ገብተን እንወዳደራለን። ምርጫዎቹ ላይ ያለውን ችግር ጊዜ ይፈታዋል። የምርጫ ሁኔታዎች ከጊዜ ወደ ጊዜ በሚያሳዝን መልኩ እየተበላሹ ነው፡፡ ነገር ግን ራስን ማኩረፍ ካልሆነ በስተቀር ሳትሳተፊ ብትቀሪ ገደል ግቢ ነው የምትባይው እንጂ የሚመጣ ነገር የለም፡፡ በምርጫው ተሳትፈን እውነቱን ቆሞ መናገር ትልቅ ነገር ነው፡፡ ለኢትዮጵያ ህዝብ አማራጭ ሆነን ምንግዜም እንቀጥላለን፡፡
በምርጫ እጩ ሆነው ያውቃሉ?
አዎ በ1993ቱ አገራዊ ምርጫ ቦሌ ክፍለከተማ ተወዳድሬ ነበር፡፡ ምርጫዎቹን ሳያቸው የመጀመሪያው ምርጫ ከኋለኞቹ የተሻለ ነበር ለማለት ያስደፍራል፡፡ ሰዉ ነቅቶ በቅቶ ነበር። መንግስት ያንን እየተሻሻለ የመጣ ባህል እንዲጎለብት አልፈቀደም፡፡ ህዝቡ የመምረጥ እና በፖለቲካ የመሳተፍ ስሜት የሚኖረው በመጠኑም ቢሆን ትክክለኛ ነገር አገኛለሁ ብሎ ሲያምን ነው። ያለበለዚያ ከቤቱ ምን ሊያደርግ ይወጣል? የሱን ፍላጎት እና የሰጠውን ምላሽ ለማወቅ 1997ትን መለስ ብሎ ማየት ነው፡፡
ከተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር ያላችሁ ግንኙነት ምን ይመስላል?
እኛ ምንግዜም ከተቃዋሚ ፓርቲዎች ጋር ጥሩ ግንኙነት እንዲኖረን እንጥራለን፡፡ ሲሆን ሲሆን የህብረት ሁኔታ ቢፈጠርም በጣም ፈቃደኞች ነበርን፡፡ ግን የገጠመንን ስናይ፣ አልፎ አልፎ ባደረግናቸው ሙከራዎች ችግሮች ገጥመውናል፡፡ ወደ ውህደት ለመግባት መቸኮሉ ዋጋ ያስከፍላል፤ አስከፍሎናልም፡፡ ለመዋሃድ ቢያንስ በመሰረታዊ ነገሮች ላይ መመሳሰልና መግባባት ያስፈልጋል። ስለዚህ ከበፊት ልምዳችን በመነሳት ነገሮችን በጥንቃቄ ነው የምናየው፡፡ ዘው ብለን ስምምነት ውስጥ መግባት አንፈልግም፡፡
በሦስት መንግስታት ውስጥ አልፈዋል፡፡ ሶስቱን እንዴት ያይዋቸዋል?
የማወዳደር ሁኔታ ሊኖር አይችልም፡፡ በኔ አመለካከት ምናልባት ልጅነቴንም በሳቸው ዘመን ስላሳለፍኩ ይሆናል፡፡ ንጉሱ ጀግና መሪ ነበሩ፡፡ ዛሬ ኢትዮጵያ ላይ ያሉ ብዙ መሰረታዊ ነገሮችን ያስቀመጡ መሪ ናቸው፡፡ ሰው ናቸውና ስህተት አልነበራቸውም ማለት አይደለም፡፡ እንደ እግዚአብሄር እንቁጠራቸው፣ እንከን አይኑራቸው የሚለው ዝም ብሎ ሀሳብ ነው፡፡ እንደ ሰው የተሳሳቱት ነገር ሊኖር ይችላል፡፡ እውነት ለመናገር ስህተታቸው እጅግ የጎላ አይደለም፡፡ ሁሉ ነገር የሚዛን ጉዳይ ነው፡፡ ሚዛኑ የሚደፋው ወዴት ነው ያልሽ እንደሆነ ወደ ጥሩ ነገራቸው ነው ብዬ ነው የማምነው፡፡ እዚች አገር ላይ ጠንካራ የትምህርት፤ የጤና፤ የመንገድ መሰረት ያስቀመጡ ናቸው፡፡ የወታደር መንግስት ኢትዮጵያ ውስጥ ብቻ ሳይሆን በየትኛውም አለም ላይ በጅቶ አያውቅም፡፡ ግሪክን ያህል ዲሞክራሲያዊት አገር ያጠፋው ወታደራዊ አገዛዝ ነው፡፡ ላቲን አሜሪካንም ተመሳሳይ ነው፡፡ ኢትዮጵያም የተለየ ነገር አልገጠማትም፤ ኢትዮጵያ አፈር ድሜ የጋጠችው በደርግ ነው፡፡ የተማሩ ሰዎች (ያለቁበት፣ ተስፋ የሰነቁ ወጣቶች በጠራራ ፀሀይ ተገድለው፣ መሬት ለመሬት የተጎተቱበት ዘመን ነው፡፡ ወደ ሚዛኑ ስመጣ ደርግ ምንም ሰራ ቢባል ጭካኔው ሁሉንም ነገር ያፈርሰዋል፡፡ ሰውን የሚጨርስ መንግስት ምንም ዋጋ የለውም። አገራቸውን በእጃቸውና በእግራቸው ያገለገሉ፣ ኢትዮጵያውያንን የገደለ ነው፡፡ በእኔ በኩል ደርግን የማየው እንደ መንግስት ሳይሆን እንደ “የጥፋት መልእክተኛ” ነው፡፡
የመንግስቱ ኃይለማርያምን መፅሀፍ አንብበዋል?
አላነበብኩም ማለት ፊደል ከቆጠረ ሰው የማይጠበቅ ቢሆንም አላነበብኩም!! ምክንያቱም እሱ ከውሸት ውጪ ምን ሊፅፍ ይችላል?!
ወደ ሶስተኛው መንግስት እንምጣ?…
የኢህአዴግ መንግስት ሲመጣ በኔ በኩል ትልቅ ተስፋ ነበረኝ፡፡ ደርግን የጣለ መንግስት ጀግና ነው ብዬ ነበር የተቀበልኳቸው፡፡ ወደ ፖለቲካ የገባሁበት ምክንያትም እነዚህን ሰዎች ለማገዝ ነበር፡፡ በሂደት ግን ተስፋ መቁረጥ መጣ፡፡ አሁንም የሚዛን ጉዳይ ነው። የሚያጠፉትን እያጠፉ፣ የሚያለሙትን ያለማሉ፡፡ እንደ ደርግ ሙሉ በሙሉ የጥፋት መልእክተኛ ብቻ አይደሉም፡፡ ጥፋቱ ምን ያህል ነው ስንል ፖለቲካው ላይ፣ የሰዎች መብት ላይ፣ ፍትህ ላይ ብዙ ደካማነት ይታይባቸዋል፡፡ ይህ ደግሞ በጣም ያሳፍራል፡፡ ኢህአዴግ እነዚህን ነገሮች ለመለወጥ እድል የነበረው መንግስት ነው፡፡ አልተጠቀመበትም፡፡ ባለፉት ሀያ ሁለት አመታት ኢትዮጵያ አልተለወጠችም የሚል ካለም ጭፍንነት ነው፡፡ ብዙ ነገሮች ተለውጠዋል። ነገር ግን ለሰው ልጅ የቁሳቁስ ለውጥ ብቻ አያረካውም፡፡ ተስፋ ያስፈልገዋል፡፡ መብቱን ይጠይቃል፡፡ ፍትህ ይፈልጋል፡፡ አለአግባብ መነጠቅ እና መባረር ሊደርስበት አይገባም፡፡ ስለዚህ ሚዛኑ ላይ ሳስቀምጠው መሻሻሉን ያጨልመዋል፡፡
ወደኋላ ልመልስዎትና…ከአሜሪካ ስትመለሱ አገርዎ ላይ ምን ገጠምዎት? የባህል ግጭትና ሌሎች ጉዳዮችን በተመለከተ…
አባቴ በአምባሳደርነት የቆዩት ስምንት አመት ስለነበር፣ ከዛ ስንመለስ በሁለቱ አገሮች የባህል ልዩነት ምክንያት አንዳንድ ነገሮች አጋጥመውን ነበር። አሜሪካን አገር ምንም ያልሆኑ ነገሮች እኛ አገር በሌላ መልኩ የሚታዩባቸው ሁኔታዎች አሉ፡፡ እኛ ወላጆቻችን የተማሩ ስለነበሩ ነፃነትን አጣጥመን ነው ያደግነው፡፡ አባቴ የለንደን ዩኒቨርሲቲ ምሩቅ ነበሩ፡፡ እናቴም በጦርነቱ ምክንያት ትምህርቷ ተቋረጠ እንጂ የህክምና ተማሪ ነበረች፡፡ ብዙ ገፋ አድርጎ መሄድ ሳይጨመርበት፣ አሜሪካን አገር በአስራ አራት አመት የወንድ እና የሴት ጓደኝነት ተፈጥሮአዊ ነው፡፡ እኛ አገር ደግሞ እንደዛ አይነት ባህል የለም፡፡ ለነገሩ እኛም የማያስቀይም እንደሆነ ብናውቅም በባህላችን የማይፈቀድ ነገር አናደርግም ነበር፡፡ አባባም አይፈቅዱም፡፡ እንደመጣን ግን እኛም በጓደኞቻችን ሁኔታ ደነገጥን፤ እነሱም በኛ ደነገጡ፡፡ የሩቅ ዘመዶቻችንም ምን ጉዶች መጡብን ብለውን ነበር፡፡ እንዳልኩሽ እኛ ቤት “Can I take your daughter to dinner?” (ልጅዎትን እራት ልጋብዛት?) የተለመደ ነው፡፡
በአባትዎ በአቶ ይልማ ደሬሳ ዙሪያ ብዙ ነገሮች ይባላሉ፡፡ ለምሳሌ የታህሳስ ግርግር ጊዜ እነ መንግስቱ ነዋይ ሲገደሉ አባትዎም “እቴጌ ታመዋልና ይምጡ” ተብለው ተጠርተው እንደነበርና እሳቸውም “እኔ የገንዘብ ሚኒስትር እንጂ ሀኪም አይደለሁም” በማለታቸው ከሞት እንደተረፉ ይነገራል፡፡ እውነት ነው?
ቀልድ ነው፡፡ በፖለቲካ ዙሪያ ብዙ ቀልዶች ይነገሩ የለ፡፡ አባባ እንደዚህ ጮሌ አፍ የላቸውም። እንዲህ እንኳን አይሉም፡፡ እውነትም ተጠርተው ነበር፡፡ በዛን ቀን በአጋጣሚ “ጌቶች” (ንጉሱ ለማለት ነው) ብራዚል ስለነበሩ፣ አልጋወራሽን አስፈቅደው ከእናቴ ጋር ወደ ጅማ ይሄዱ ነበር፡፡ አባቴ ምንም የጠረጠሩት ነገር የለም፡፡ ይፈለጋሉ ሲባሉ፣ “ኧረ እኔ መንገድ እየሄድኩ ነው” ብለው መለሱ፡፡
የደራሲ ስብሀት ገብረእግዚአብሄር ባለቤት የነበረችው ሀና ይልማ የእርስዎ እህት ናት፡፡ ከተፋቱ ረጅም ጊዜ ቢሆንም በህይወት እያለ ትጠያየቁ ነበር?
በሚገባ እንጠያየቅ ነበር እንጂ! ልጁ ከውጭ ሲመጣም ተገናኝተን ድሮ የምንሄድባቸው ቦታዎች በመሄድ አብረን እናሳልፍ ነበር፡፡

የተደናበረው ማነው!

ግልጽ ደብዳቤ ለአቶ ሀይለ ማሪያም ደሳለኝ
ከብርሃኑ ተስፋዬ

ይድረስ ለአቶ ሀይለ ማሪያም ደሳለኝ ፖ.ሳ. ቁ. 1031 አዲስ አበባ

ጉዳዩ፣ የተደናበረው ማነው!

እንደ ጠቅላይ ሚኒሰትር ሳይሆን እንደ ተራ ካድሬ ከዋልታ ኢንፎርሜሽን ጋር ያደረጉትን ቃለ ምልልስ አዳመጥሁት ገረመኝ፣ ፣ አግራሞት የፈጠረብኝ ደግሞ ከአፋዊ ህግ መንግስት አንቀጽ ቀንጨበው ጉዳዩን ለማስረዳት መሞከርዎ ሳይሆን ጠያቂዎ ያጎረሰችዎትን ቃላት እንዴት ለመጠቀም መሞከርዎ እሱዋ ሃላፊዎት እንጂ ጠያቂዎት ሳትሆን መሪ ካድሬዎት መሆኑዋን ማረጋገጥዎ ነው።
ይህ የተደናበረ መልስዎ ያጫረብኝ በሃይማኖት ሺፋን የፖሊቲካ እንቀስቃሴ ሃገሪቱ ውስጥ አለ ብለው አፍዎን ሞልተው የሸሪያ መንግስት ለመመስረት የተነሱ ናቸው ብለው መናገርዎ አንድን ጣልቃ አትግቡን የራሳችንን መጅሊሰ ያለ መንግስት ጣልቃ ገብነት ራሳችን እንምረጥ ያለን የሙስሊም ማህበረ ስብ ጥያቄ እንደዚህ ከፖሊቲካ ሃሳብ ጋር ማጋባተዎ የባጃጅነትዎን መጋረጃ ቀደው ለህዝብ ባደባባይ ራስዎን ያሳዩበትን በማየቴ ነው።

ለመሆኑ እየመራሁት አለሁት የሚሉትን መንግስት በዝርዝር እንመልከተው እስቲ፣

ገና ተጠባባቂ ተብለው ባቶ በረከት ስምኦን ከተሰየሙና የዱዳ ፓርላማ ማህተም ከማድረጉ በፊትና ካደረገልዎት ወቅት ጀምሮ የተዘጉ የሜዲያ ዉጤቶች ከደቡብና ሌሎች ክልሎች የተፈናቀሉ ኢትዮጵያዉያን ሁኔታ በመንግስት ወጪና ከቀረጥ ነጻ መብት ያለው ሃገሪቱን ያለወደብ ላስቀረና ማህበረ ሰባችንን በጎሳ ላከፋፈለ ህዝቡን አፈናቅሎ በሳንቲም ደረጃ መሬታችንን ላከራየና ለገደለ አርዮስ መታሰቢያ ድርጅት ለፓርላማ አቅርበው እንዲጸድቅ ማድረግዎ የሚጠቀሱት ናቸው።

ልብ ይበሉ በህዝብ ገንዘብ በሀገርም ሆነ በዉጭ እድሉን አግኝቶ ለተማረና የምእራብን የዴሞክራሲ አሰተዳደር ለማየት እድል ካጋጠመው እርስዎን ከመሰለ ግለሰብ በሺዎች የሚቆጠሩ ልጆቻችን እህቶቻችን ወንድሞቻችን እናትን አባቶቻችን በጠራራ ጸሃይ ሲደበደቡ ሲታሰሩና ሲገድሉ እይኔን ግንባር ያድርገው ብለው ምንም ያልተፈጠረ አድርገው እንዲህ አይነት ቃለ መጠይቅ ያሰደምማል።

ትንሽ ላሰታውሰዎ እስቲ አዋሳ እያሉ ሎቄ ላይ ሃሳባቸውን በመግለጻቸው በፌደራል አባላት ያስገደሉዋቸውና ያሰፈጁዋቸው የሲዳማ ብሄረ ሰብ አባላት ደም በእጅዎ የለም ከህዝብ በተሰበሰበ ታክስ ወጋጎዳ የሚባል አዲሰ ቑንቓ ፕሮጀክት መሃንዲሰነት መጫወትዎን እረሱት እንዴ።

መንግስትና ሀይማኖት በህገ መንግስታችን የተከበረ ነው ብለው ያፌዙና ሙስሊም ወንድሞቻችን ያነሱትን ጥያቄ ከፖሊቲካ ድርጅቶች እንቅስቃሴ ጋር ማጋባትዎና ከራስዎ አንደበት የወጡትን ቃላት ለመጥቀስ “…. አቃጥየ ፣ ደብድቤ፣ ገድየ፣ መስጊድ ማቃጠል ቤተ ክርስቲያን ማቃጠል…..የሸሪያ ህግ የበላይ መሆን አለበት፣ ህገ መንግስት መናድ” አምጥተው እድንጎርሳቸው ለምን ፈለጉ።

አቶ ሀይለ ማርያም እስኪ ከሰሞኑ የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ያሰተለለፈውን ላሰታውሰዎት የተቀደደ ሰንደቅ አላማ በሙስሊሙ የአንዋር ተቃውሞ መሃል አሳይቶ ተቃጠለች የሚል ዘገባና አስተያየት በቤኒ መስጊድ እንደተደረገ ማናፈስ… ኮፈሌ ህዝብን ለመጨፍጨፍ ቅድመ ዝግጅት አጠናቆ ረብሻ አስነስቶ በመቅረጽ ያልሆነ ዘገባ ለህዝብ ማሰተላለፍ ፣ ሀዝበ ሙስሊሙ የሮመዳን ጾም ፍችን ከዚህ ቀደም እንደሚያደረጉት ሁሉ ሰታዲዮም ለማክበር ሲዘጋጅ ሙስሊሙን ለሁለት በመክፈል ላንዱ መግቢያ መስጠት ለሌላው መከልከል ሲተገበር የርሰዎ ቢሮ አያውቅም ነበር ቢሉኝ፣ በሰላማዊ መንገድ የተቃወሙ የሙስሊሙ ማህበር ሰብ በልዩ ሃይል እንዲደበደቡ ሲደረግና አዲሰ አበባ ሰው ሲፈነከትና ህጻናትና እርጉዞች ሲደበደቡ፣ ከአውሮፓ ፓርላማ ቃሊቲ ከሄዱ በሁዋላ የፖለቲካ እስረኞችን ለመጎበኘት መከልከላቸው የራስዎን መደናበር ከማመላከቱ ባሻገር አንድም ሀገሪቱን የምትመራበት ብለው የሚያላዝኑለት ቃላዊ ህገ መንግሰትን ወይ ያላነበቡት አሊያም እንደ ሌሎቹ ካድሬዎች በህወህት እንደ ኮካ ኮላ የተሞሉ ሆነው ነው የማይዎት።

በመሆኑም ይህንን ስጽፍ ውሃ ቢወቅጡት እንቦጭ መሆኑን ባልረሳውም እንደተናገሩት

ሳልሸራርፈው የተሞላሁትን ለመተግበር የተነሳሁ ነኝ ዲያቢሎሱ ቢሞትም ከላይ ኮቴን ከውስጥ የሱን ሰደርያ ለብሼ እንደምቀጥል እወቁት ያሉትን የመጀመሪያ ንግግርዎ ትዝ ይልዎት ይሆን?

ታዲያ እራሱን ሆኖ ከማይኖር ግለሰብ ህዝቡን ለመምራት ሳይሆን ራሱ ተደናብሮ ህዝብ ማደናገርን ከሚፈልግ የሚጠበቅ በመሆኑ እባክዎን ወደ ህሊናዎ ይመለሱ እላለሁ።

44ቱ ጎንደር

44ቱ Gondar Churches

Tradition states that the ancient Ethiopian capital of Gondar had 44 churches. The number of churches in this list is less than that — Stuart Munro-Hay provides some evidence that shows the number was meant to be taken symbolically, rather than literally — and not all of them are, properly speaking, in Gondar.

Name Date founded (if known) Comments
Abba Antons 1715 Located west of Gondar. Original paintings removed in 1933 by Marcel Griaule, now on display at theMusée de l’Homme.[2]
Abajale Tekle Haymanot Original church built during reign of Emperor Fasilides
Abhorra Giyorgis Located 3 kilometers south of Gondar
Abyegzi Original church founded by an aristocrat in the reign of Tekle Haymanot II. Present structure is a round church
Adababay Iyasus Located in Adababay, the market place outside the southern gates of the Royal Enclosure. Founded by Emperor Fasilides.[3]
Adababay Tekle Haymanot Located in Adababay. Founded by Emperor Iyasus I[4]
Asasame Qeddus Mikael Located inside the Royal Enclosure. Dedicated by Emperor Dawit II.[5]
Ba’eta Maryam 1775
Cherkos Located on southeast end of Adababay, and named after the child martyr Quiricus of Tarsus. Original church founded by Emperor Tekle Haymanot II
Dafacha Kidane Mehret “Convent of Mercy” Founded by Bakaffa; by 1973 this church was in ruins
Debre Berhan Selassie 1693 Best known of the churches of Gondar for its interior paintings. Avoided destruction by the Mahdists in 1888, this church “offers some idea of what other treasures might be in Gonder today had it not been for the Mahdist War.”[6]
Debre Metmaq Mariyam Founded by Emperor Tekle Giyorgis in late 18th century.
Dibabo Also known as the “Church of the Apostles of Deva”
Elfin Giyorgis Located inside the Royal Enclosure. Constructed by Emperor Fasilides.[5]
Ewostatewos Named for the Ethiopian saint. Founded by Bakaffa
Egziabeher Ab Founded by Emperor Fasilides, but destroyed in the Mahdist sack of Gondar. According to Solomon Getahun, the site is now occupied by a mosque built during the rreign of Emperor Menelik II.[7]
Fit Qeddus Mikael Old church of St Michael, burned down in 1725. A modern round church stands on this site, although an old archway from the original church still stands
The Four Saints Also known as the church of the Four Animals. Now vanished, but the site is marked by a fig tree.
Gemjabet Mariyam Located inside the Royal Enclosure. Constructed by Emperor Fasilides.[8]
St. George of Damot Burned down in 1695
Hamara Noh (“Noah’s Ark”) 1710 Also known as Selestu Mit. Founded by Emperor Tewoflos. Mentioned numerous times in the 18th century, this church since vanished without a visible trace.
Hawaryat By 1938, all that remained were traces of the enclosure wall and a mound of stones.
St. John of Guara Perhaps founded by one of the relatives of Empress Mentewab
Lideta Mariyam 1713
Mariyam Seyon Munro-Hay doubts this church ever existed
Mariyam Sihor Church southwest of Gondar
Medhane Alem Seat of the Ethiopian Orthodox bishop of Gondar
St. Mikael of Aira Unidentified
St. Mikael of Belageo Also known as Bilajig Mikael
Peter and Paul Unidentified
Qaha Iyasus church May have existed before the founding of Gondar.
Qeddus Abbo Also known as Fit Abbo. First church built by Emperor Fasilides in Gondar.
Qeddus Fasilides Munro-Hay believes this “was actually nothing other than a re-use of the pavilion in the lake usually called the Bath of Fasiladas.”
Qeddus Gabrael Original church said to have been built by Emperor Fasilides; location now occupied by a large square church. Solomon Getahun notes this was the seat of the Abuna, and served as a refuge for asylum-seekers. The Abuna moved his residence to Medhane Alem (see above) during the Italian occupation.[9]
Qeddus Rafael 1722 Adjacent to the Royal Enclosure. Burned during unrest in Iyasus II’s reign; present structure a new building
Qeddus Yohannes Built by Ras Wolde Leul during the reign of Iyasu II, currently all that remains of this structure is the stone-built pedestal. Reconstruction planned.
St Simeon of Tzaamdi Munro-Hay suggests two different churches this might be: either a church of Samuel southwest of Gondar, or the church of “Tzemba” located on the Lesser Angereb
Wolleka Ba’ata Located three kilometers north of Gondar
Wrangeb Giyorgis May have existed before founding of Gondar[10]
Yohannes Wolde Nagwadgwad Founded by Emperor Tekle Haymanot II

References

  1. ^ Unless otherwise indicated, information for this list taken from Munro-Hay, Ethiopia, the unknown land: a cultural and historical guide (London: I.B. Tauris, 2002), pp. 142-156.
  2. ^ David Buxton, The Abyssinians (New York: Praeger, 1970) p. 151
  3. ^ Munro-Hay, Ethiopia, pp. 140f
  4. ^ Munro-Hay, Ethiopia, p. 141
  5. a b Munro-Hay, Ethiopia, p. 140
  6. ^ Philip Briggs, Ethiopia: The Bradt Travel Guide, 5th edition (Chalfont St Peters: Bradt, 2002), p. 233
  7. ^ Solomon Getahun, History of the City of Gondar (Trenton: Africa World Press, 2005), pp. 17f
  8. ^ Munro-Hay, Ethiopia, p. 139
  9. ^ Solomon Getahun, City of Gondar, pp. 22, 31
  10. ^ Solomon Getahun, City of Gondar, p. 3

ወንጀለኛ የህወሃት ጀሌዎችን በህግ ለመፋረድ ድጋፍዎን ይስጡ

ወንጀለኛ የህወሃት ጀሌዎችን በህግ ለመፋረድ ድጋፍዎን ይስጡ
ኢትዮጵያዊያን በሀገራቸው ጭቆና፣ አድልኦ፣ ግፍና በደል አንገሽግሿቸው ተሰደው በሚኖሩበት ምድር ሁሉ ክብራቸውና ነጻነታቸው ተጠብቆ
መኖር እንደሚገባቸው ፈጽሞ አጠያያቂ አይደለም። የህግ ልእልና በሰፈነባቸው አገሮችም ይህንን መሰረታው መብት ለማስጠበቅ ከህግ በላይ
ምንም ሀይልና ጉልበት ያለው መሰሪያ የለም።
ህወሃት መራሹ የኢትዮጵያ መንግስት “አሰረን አሳደደን” በማለት በአውሮፓና በአሜሪካ የፖለቲካ ጥገኝነት በመጠየቅ
በስደተኛ ስም በተለያየ የማምታቻ ሽፋን ተደብቀው ኢትዮጵያዊያን ያለስጋት የነጻነት አየር እየተነፈሱ እንዳይኖሩ
ለማድረግ የሚጥሩ ሰላዮችና የጨቋኙ ስርአት አቀንቃኞች መኖራቸው በተለያየ ጊዜ የተረጋገጠ ሃቅ ነው።
ምንም እንዃን በርካታ ኢትዮጵያዊያን በተደጋጋሚ የነዚህ ወንጀለኛና አሸባሪ ግለሰቦች ሰለባ ቢሆኑም
እስካሁን ጠንካራ ህጋዊ እርምጃ እንዲወሰድባቸው በቂ ጥረት አልተደረገም።
ባለፈው ግንቦት 10 2004 (May 18, 2012) ጋዜጠኛ እና የሰብአዊ መብት ተሟጋች የሆነው አበበ ገላው
የቀድሞው አንባገነን መለስ ዜናዊን ወንጀሎች በአለም መሪዎች ፊት ስላወገዘ እና ስላጋለጠ እንዲሁም የታፈነ
የኢትዮጵያን ህዝብ የነጻነት ጩኸት ስላሰማ በተለያዩ የህወሃት ጀሌዎች የሽብር ፈጠራ ወንጀል ሰለባ ሆኗል።
በቅርቡ ከነዚህ በህገወጥ የወንጀልና የስለላ ተግባር ከተሰማሩ የህወሃት ጀሌዎች መሃል ጥቂቶቹን ያጋለጠው ጋዜጠኛ አበበ ገላው፣ ጠበቃ ይዞ
በህግ ለመፋረድ እንቅስቃሴ ጀምሯል።
ይሄንኑ አላማ ለማሳካት እና ወያኔዎች የፈጠሩትን የጸጥታ ስጋት አቅም በፈቀደ መንገድ ለመቅረፍ ጥቂት የECAD የፓልቶክ መድረክ አባላት
በራሳቸው አነሳሽነት ባዋጡት ገንዘብ ለዚሁ አላማ ማስፈጸሚያ የሚሆን ልዩ የባንክ ሂሳብ ተከፍቷል::
ነጻነትና የህግ ልእልና በሰፈነባቸው አገሮች ከህግ በላይ ወንጀለኞችን የመፋለሚያ መሳሪያ ባለመኖሩ፣ ጉዳዩ ይመለከተናል የሚሉ ኢትዮጵያዊያን
ሁሉ የገንዘብ ድጋፍ በማድረግ ይህንን ጥረት አቅማቸው የፈቀደላቸውን ያህል እንዲያግዙ ወገናዊ ጥሪ ቀርቧል።
ህግን ተጠቅሞ ህገወጦችን መፋረድ አንድ የትግል ስልት በመሆኑ ለአንድ ሰው ብቻ የሚተው ጉዳይ አለመሆኑ ለማንም ግልጽ ነው። እርስዎም
ለዚሁ እንቅስቃሴ የገንዘብ ድጋፍ ማድረግ አስፈላጊነቱን ካመኑበት ከታች ከተዘረዘሩት አማራጮች በአንዱ መንገድ አስተዋጽኦ ማድረግ
ይችላሉ:::
1/ በማንኛውም አሜሪካ በሚገኝ የWells Fargo ቅርንጫፍ AG Legal Fund, Acc. No. 3525090746 በቀጥታ ገንዘብ ማስገባት
ይቻላል።
2/ አሜሪካ በሚገኝ ማንኛው Bank of America ቅርንጫፍ በኩል በቀጥታ ገንዘብ ማስገባት ይቻላል:
AG Legal Fund, Acc. No. 485010192701
3/ ከሌሎች አሜሪካ የሚገኙ ማንኛውም ባንኮች ለማስተላለፍ (wire) ለማድረግ AG Legal Fund, Acc. No. 485010192701 , ABA
121000248 መጠቀም ይቻላል::
4/ ከአሜሪካ ውጭ ከሚገኙ ባንኮች ገንዘብ ወደ AG Legal Fund ለማስተላለፍ Acc. No. 3525090746 SWIFT- WFBIUS6S
መጠቀም ይቻላል::
5/ በኢንተርኔት አማካኝነት በ Paypal አስትዋጾ ማድረግ ከፈለጉ ከታች ያለውን ድር (link) በመጫን አስተዋጾ ማድረግ ይችላሉ።
https://www.paypal.com/cgi-bin/webscr?cmd=_s-xclick&hosted_button_id=UHPF5RPB2PBSN
6/ ከዚህም በተጨማሪ በWestern Union ከላይ በተጠቀሱት የባንክ ሂሳቦች በአንዱ አማካኝነት ገንዘብ ማስተላለፍ ይችላሉ።
ስለጉዳይ ተጨማሪ መረጃ ከፈለጉ በስልክ ቁ. (001) 5718829882 በመደወል ወይንም በ ethlegalfund@gmail.com ኢሜይል ማድረግ ይችላሉ።
እናመሰግናለን!!

በሌሎች ተክዶ ራሱንም የካደው ትውልድ

በሌሎች ተክዶ ራሱንም የካደው ትውልድ
የዘመናዊ ትምህርት ወይም “ቀለም ቀመስ” የሆነው የዐማራው ትውልድ በሌሎች ነገዶች/ጎሣዎች ቀለም ቀመስ
ትውልድ ተክዷል። በሌሎች መካዱን ያልተረዳውና ሊረዳም ያልፈለገው ቀለም ቀመሱ የዐማራ ትውልድ፣ የራሱን ማንነት
ክዶ የገዛ ትውልዱን ከጥፋት ለመከላከል የሚያስችለውን አቅሙን ላለመጠቀም የተለያዩ ምክንያቶችን በመደርደር ራሱንና
ወገኖቹን ለጥፋት አጋልጦ፣ “የራሷ ሲያርባት የሰው ታማስላለች” ዓይነት ሆኖ ይታያል። ልብ እንበል ፣ ልብ በሉ!
የኢትዮጵያ ቀለም ቀመስ የሆነው ትውልድ ፣ በ1960ዎቹ “መሬት ላራሹ!” የሚለውን መፈክር ሲያነሣ፣ በመካከሉ
ልዩነት አልነበረም። በ”መሬት ላራሹ” መፈክር መሪነት ሕዝባዊ ትግሉ እየገፋ ሲሄድ ቀለም ቀመሱን ትውልድ በአቋም
ከሁለት የከፈለ መሠረታዊ ጥያቄ ተነሣ። ያም ጥያቄ፦ “የኢትዮጵያ መሠረታዊ ችግር ምንድን ነው?” የሚለው ነበር። ለዚህ
ጥያቄ ሁነኛ መልስ ለመስጠት በተደረገ የኃሣብ ፍጭት ሁለት ʻበሰሜንና ደቡብ ያህል ተራርቀው የቆሙʼ አቋሞች ጎልተው
ወጡ። አንደኛው አቋም “የኢትዮጵያ መሠረታዊ ችግር ብሔራዊ ጭቆና ነው፤ ጨቋኙም የዐማራ ነገድ (በእነርሱ ቋንቋ
ብሔር) ነው፤ የዐማራው ነገድ ሲወገድ ችግሩ ይፈታል፤” ከሚል መደምደሚያ ደረሰ። ሁለተኛው ጽንፍ ደግሞ፦
“የኢትዮጵያ መሠረታዊ ችግር የመደብ ልዩነት ነው፤ ጨቋኝ መደቦች፣ በተለይም ገዥው ጨቋኝ የዐማራ መደብ ሲወገድ
የኢትዮጵያ ችግር ይፈታል፤” ብሎ አመነ። እንደ አለመታደል ሆኖ በሁለቱም አቋሞች የተለያየ ስም ይሰጠው እንጂ፣
እንዲጠፋ የተፈረደበት የዐማራው ነገድ ነበር፣ ነውም። ስለዚህ ዛሬ በዐማራው ነገድ ላይ እየተፈጸመበት ያለው የዘር
ማጽዳት ዘመቻ የተጠነሰሰው በዚያን ወቅት እንደነበር የድርጊቱ ሂደት ቁልጭ አድርጎ ያሳያል።
የነበረውን የአቋም ልዩነት ተከትሎ “ሕዝባዊ እንቅስቃሴውን እንመራዋለን” ያሉ ድርጅቶች ብቅ አሉ።
በመጀመሪያው አቋም ዙሪያ የተኮለኮሉት፦
(1) በቅኝ ገዥዎች ዓላማ የተጠመቁትና “ኤርትራ በኢትዮጵያ ቅኝ ግዛትነት ተይዛለች፣ ከቅኝ ገዥዋ ከኢትዮጵያ ነፃ
መውጣት አለባት”ብለው የተነሱት ጀብሃና ሻዕቢያ፣
(2) ትግራይን በመገንጠል “የትግራይን ሪፐብሊክ እመሠርታለን” ያለው ሕወሓት (ወያኔ)፣
(3) “የዐማራው ነገድ ኃይማኖታችንን ፣ ባህላችንን እና ቋንቋችንን አጥፍቷል፣ በመሆኑም ዐማራው ከሚያስተዳድራት
የአቢሲኒያ ኢምፓዬር ነፃነታችን ማግኘት አለብን፣” ያለው ኦነግ እና በዚህ አቋም ዙሪያ የተደራጁት የነገድና የጎሣ
ድርጅቶች ነበሩ።

በሁለተኛው አቋም ዙሪያ ተሠባስበው የነበሩት ደግሞ፦
(1) የኢትዮጵያ ሕዝባዊ አብዮታዊ ፓርቲ (ኢሕአፓ)፣
(2) የመላው ኢትዮጵያ ሶሻሊስት ንቅናቄ (መኢሶን)፣
(3) በኢማሌድኅ ሥር የታቀፉት ድርጅቶች፦ አብዮታዊ ሠደድ ፣ ወዛደር ሊግ ፣ ማሌሪድ እና ኢጭአት ሆነው
እናገኛቸዋለን።

ይህ ሁለተኛ ስብስብ በመሠረታዊው ጥያቄ ዙሪያ አንድ ዓይነት መልስ ቢኖረውም፣ በችግር አፈታቱ ታክቲክ አመራረጥ
ረገድ ድርጅቶቹ የተለያዩ መንገዶችን መረጡ። በዚህም የተነሣ “የአገሪቱ መሠረታዊ ችግር ነው” ላሉት “የመደብ ልዩነት”
ጉዳይ አጥጋቢ መልስ አልሠጡም። ከዚያ ይልቅ አንዱ ሌላውን አሸንፎ የበላይ ሆኖ ለመውጣት ከፕሮፓጋንዳ አልፎ እስከ
ትጥቅ ትግል ባደረጉት ግብግብ እርስ በራሳቸው በመጠላለፋቸው አጥፊና ጠፊ ሆኑ። የተፈጠረውም ግብግብ ከአባሎቻቸው
አልፎ ለአንድ ዘመን የኢትዮጵያ ወጣት ትውልድ ዕልቂት ምክንያት ሆነ።በዚያን ዘመን በአቋም ደረጃ ሁሉም ኃይሎች የተስማሙበት አንድ መሠረታዊ ነጥብ “ጨቋኙ ገዥ መደብ የወጣው
ከዐማራው ነገድ ነው። ስለዚህ የዐማራው ነገድ የበላይነት መሠበር አለበት፤” የሚል ነበር። ይህንን መፈክር አንግበው
የዐማራውን ነገድ ተወላጆች የኃብትና የፆታ ልዩነት ሣያደርጉ እያደኑ ጨፈጨፏው። ይህም ዕርምጃ ውሎ አድሮ ለኢትዮጵያ
ዘብ ቆሞ የኖረውን የዐማራውን ነገድ ኃይል አዳከመው። በተቃራኒው ፀረ-ኢትዮጵያ አቋም ለያዙት ብሔርተኛ ድርጅቶች
ብርታትንና ጉልበትን በማጎናጸፍ የፈለጉትን ኢትዮጵያን የማፈራርስ ድርጊት እንዲገፉበት ሠፊ ዕድል ሰጣቸው።
በሌላ በኩል ደግሞ “የኢትዮጵያ መሠረታዊ ችግር ብሔራዊ ጭቆና ነው፤ ጨቋኙም ዐማራው ነው፤” ብለው
የተነሡት የነገድና የጎሣ ድርጅቶች በአቋማቸው ፀንተው ሲቆሙ፣ የዐማራው ነገድ ልጆች ግን በአቋም ከሁለት፣ በታክቲክ
ረገድ ከሁለት በላይ በሆኑ ቡድኖች ተከፋፍለው ቆሙ። ለዚህ አስተዋፅዖ ያደረገው የኤርትራ ገንጣይ ቡድኖች አባሎች
የብሔራዊ ፖለቲካ እንቅስቃሴ ያደርጉ በነበሩት ድርጅቶች ውስጥ ሠርገው በመግባት የሩቅ ግባቸውን ለማሣካት ያደረጉት
አሻጥር ነው። በጀብሃና በሻቢያ እምነት ትግላቸው የሠመረ የሚሆነው፦ ʻየትውልዱን የኢትዮጵያዊነት መንፈስ አዲስ-ገብ
በሆነው የማርክሣዊ-ሌኒኒናዊ-ማዖአዊ ርዕዮተ-ዓለም በማደንዘዝ የራሱን ማንነት አስትቶ የሌሎችን ባዕድ ማንነት
እንዲከናነብ ሲደረግ፤ ጠንካራ ማዕከላዊ መንግሥት ሲዳከም፤ በነገዶችና በጎሣዎች መካከል የነበረው ነባር የአንድነት እና
የአብሮነት ስሜት ሲላላ፤ “ለኢትዮጵያ አንድነት ጠበቃ ነው” ብለው የሚወነጅሉትን የዐማራው ነገድ ሌሎች ነገዶች
በጠላትነት ፈርጀው ያለ የሌለ ኃይላቸውን እንዲያነሱበት ሲደረግ፤ በኢትዮጵያ አንድነት የሚያምነው ኃይል እንዲከፋፈል
ማድረግ ሲቻል ነው፤ʼ ብለው ሥልታቸውንና ታክቲካቸውን ነድፉ። የዐማራው ነገድ ቀለም-ቆጠር ትውልድ ግን
የተደገሠለትን ሣያውቅ “አያ በሬ ሆይ፣ ሣሩን አየህና ገደሉን ሳታይ፤” ሆኖበት በተገንጣዮቹና ብሔርተኞቹ ወጥመድ ውስጥ
ሰተት ብሎ ገባላቸው። ይህም አካሄድ የጠነከረ የኢትዮጵያዊነት አቋም የነበራቸውንና ያላቸውን የዐማራውን ነገድ ልጆች
አሠናክሎ በአንድ መሶብ እንዳይመገቡ፣ ባንድ ኮዳ እንዳይጠጡ፣ በአንድ እንዳይመክሩና እንዳይዘክሩ፣ በአንድ ቃል
እንዳይቆሙ አደረጋቸው።
የሚያሣዝነውና የሚያስቆጨው በዐማራው ነገድ ልጆች መካከል “በዘመነ-አብዮት” የተዘራው የጠላትነት ስሜት
ዛሬም አልደበዘዘም። ከሁሉም የሚያሣዝነው ደግሞ የሁሉም ቡድኖች የርዕዮተ-ዓለም ካባ የነበረው ማርክሲስዝም-
ሌኒኒዝም-ማዖኅዝም እንደ ʻአጥፊ አመለካከትʼ ተቆጥሮ በዓለም ዙሪያ ተወግዞ ተትቷል። የርዕዮቱ ግንባር-ቀደም አራማጅና
አስፋፊ የነበረችው ሶቪዬት ኅብረት፣ ርዕዮቱን ጭራሹኑ ከመተው አልፋ፣ በሥሯ የነበሩት የተለያዩ ግዛቶቿ ተገነጣጥለው 15
ራሣቸውን የቻሉ አገሮች ከተፈጠሩ ከ20 ዓመታት በላይ ሆኗቸዋል። የማዖ ዜዱንግ አገር ሕዝባዊት ቻይና ኮሚኒዝም
ለአገዛዝ እንጂ ለኢኮኖሚ ብልፅግና እንደማይበጅ ተገንዝባ በቅይጥ ፍልሥፍና መመራት ከጀመረች 30 ዓምታት አለፋት።
የኛዎቹ የዐማራው ነገድ ልጆች ግን “ጅልና ወረቀት ያስያዙትን አይለቅም” ሆኖባቸው ዛሬም ያ ተምኔታዊ ʻየመደብ ጠላትነትʼ
ስሜታቸው ከኅሊናቸው ባለመውጣቱ ይቅር ለመባባልና በአንድነት ለመቆም አልቻሉም።
በሌላ አቅጣጫ ሲታይ ደግሞ በፖለቲካ ትግል የአንዱ ቡድን ድክመት ለተቀናቃኙ የጥንካሬ ምንጭ ነው። በዚህም
ረገድ በነገድና በጎሣ ልዩነት ሥር የተደራጁት ቡድኖች ትላንት እነርሱ አብረው ያነሱትን “የመሬት ላራሹ” መፈክር በግንባር
ቀደምትነት ተሸክሞ የጮኸውን እና ወላጆቹን ሰድቦ ለሰዳቢ የሰጠውን የዐማራውን ነገድ ልጆች የትግል አስተዋፅዖ
ክደውታል። አልፈው ተርፈውም የየራሳቸውን የሥልጣን ድርሻ ይዘው በየጎሣቸውና በየነገዳቸው ሠንደቅ ዓላማቸውን
እያውለበለቡ ጎጆ ወጥተዋል። ይህንን ሲያደርጉ ካለምንም ኃፍረትና ይሉኝታ የዐማራውን ነገድ ልሂቃን “አናውቃችሁም ፣
ከየጎጇችን ውጡልን” ብለው ማረፊያ ዛፍ ያጣ ጉሬዛ አድርገዋቸዋል። ነገር ግን ዛሬም የአንድ የዐማራው ነገድ ልጆች፣ ድሮ
በአንድ ክፍል የተማሩ፣ በአንድ ማዕድ የተመገቡ፣ ውኃ ተራጭተው፣ አፈር ፈጭተው አብረው ያደጉ ሰዎች ከሁሉም
አቅጣጫ ለሚደርስባቸው ጥቃት በአንድነት መቆም አልቻሉም። ብሔርተኞቹ የዐማራውን ልሂቃን ከፋፍለው በመጨረሻም
ክደው፣ አገራቸውንና ነገዳቸውን ለማጥፋት ረጅም ርቀት መጓዛቸውን እያዩ፣ በሌሎች ነገዶች ልሂቃን መከዳታቸውን እንኳን
ካለመገንዘባቸውም ሌላ፣ ማንነታቸውን ባስካደው ጎዳና እስከመጨረሻው ለመጓዝ የወሠኑ ይመስላሉ።

የዐማራው ልሂቃን ʻራስን የመካድ አባዜʼ ዋና መገለጫው ሌላ ምንም ሳይሆን የዐማራው ነገድ በወያኔ አገዛዝ
ላለፉት 22 ዓመታት እየደረሰበት ያለውን የዘር ማጥፋት እርምጃ ልጆቹ እንዲታደጉት ለሚያቀርበው የተደጋገመ ጥሪ
ʻየዝሆን ጀሮ ስጠኝʼ ማለታቸው ነው። እንዲያውም የዐማራው ምሁር የበቀለበት የራሱ ነገድ ʻእንደ ክፉ አድራጊʼ ከመወገዝ
አልፎ ሲገደል፣ ሲታሰር፣ ከሥራ ሲፈናቀል፣ በአገሩ አትኖርም ተብሎ ሲባረር እያየ ʻለምን እንዲህ ይደረጋል?ʼ ለማለት ወኔ
አጥሮት ይታያል። የወኔው እጥረት ምክንያትም ሌላ ሣይሆን የዐማራው ነገድ ምሁራን በሌሎች መካዳቸውን፣ ነገዳቸው
በሁሉም ነገድ ልሂቃን በጠላትነት ተፈርጆ እንዲጠፋ የተከፈተበትን ዘመቻ በተከተሉት የመደብ ማጽዳት ርዕየተ-ዓለም
የተነሣ ʻዐማራውን በገዥ መደብነትʼ አብረው ፈርጀው እንዲጠፋ የተስማሙና እነርሱም ራሳቸውን የካዱ ከመሆኑ የመነጨ
ሊሆን እንደሚችል መገንዘብ አይገድም። ይህ ባይሆንማ ኖሮ የቀረው ቢቀር ስብሐት ነጋ፣ ዐባይ ፀሐዬ፣ ሣሞራ የኑስ እና
ሌሎችም ቀንደኛ የወያኔ መሪዎች በመደጋገም “ዐማራውን ገድለን ቀብረነዋል” ሲሉ፤ ዐማራው ʻበደቡብ፣ በምሥራቅና
በምዕራብ ኢትዮጵያ መኖር አትችልምʼ ተብሎ ሲባረር፤ ʻለምን? እንዴት?ʼ ብሎ መጠየቅ የአባት ነበር። የዐማራው ነገድ
ቀለም ቆጠር ትውልድ ይህን ሲያደርግ አለመታየቱና አለመሰማቱ፣ በሌሎች ነገዶች ልሂቃን ተክዶ እንኳን ራሱንም የካደ፤
እንዲሁም የያዘውና እያራመደው ያለው አቋም ካሉት ከነባራዊ ሁኔታዎች ጋር ያልተገናዘበ እንቅስቃሴ እንደሆነ ያስረዳል።
ድርጊቱ የራስን ጥላ የመሸሽ፣ ማንነትን በቅጡ ያለመገንዘብ፣ ከታሰረበት የድርጅትና የአመለካከት እሥር ቤት ለመውጣት
ፈቃደኛ ያለመሆን አመልካች ነው።
እኒህ የዐማራው ልሂቃን ከዚህም አልፈው፦ “በዐማራነት መደራጀት ዘረኛ መሆን እና ወያኔ በከፈተው ቦይ ገብቶ
መፍሰስ ነው፣ ወዘተርፈ” በማለት ተደራጅተው ጥቃቱን ለመመከት በመፍጨርጨር ላይ የሚገኙትን የገዛ ወገኖቻቸውን
ያወግዛሉ። አልፈው ተርፈውም ለዐማራው ኅልውና መቀጥል ተደራጅተው በመታገል ላይ የሚገኙት ኃይሎች ተቀባይነት
እንዳይኖራቸው የተለያዩ መሠናክሎችን እያጠመዱባቸው ይገኛሉ። በሌሎች ነገዶች ልሂቃን ተክደው፣ ራሣቸውንም የካዱት
የዐማራው ልሂቃ ያልተረዱት አንድ ነገር ቢኖር፦ ኢትዮጵያን በማጥፋት፣ ከኢትጵያዊነት እምነቱና ከዜግነቱ እየለየው ያለው
የትግሬ-ወያኔ አገዛዝ ግቡን ከማሣካቱ በፊት ፣ ኢትዮጵያ መጥፋት የለባትም። ለኢትዮጵያና ለኢትዮጵያዊነት መቀጠል
ምሦሦ የሆነው የዐማራው ነገድ በተያዘው የዘር ማፅዳት ዘመቻ ከጠፋ፣ ኢትዮጵያ አትኖርም። ስለሆነም ኢትዮጵያን ለማዳን
“ኢትዮጵያዊ ነኝ” ብሎ ያመነው የዐማራው ነገድ ራሱን አደራጅቶ በመጀመሪያ የራሱን ኅልውና ማስጠበቅ አለበት።
ከ1950ዎቹ አጋማሽ እስከ ጀምሮ ያለው የኢትዮጵያ ቀለም ቆጠር ትውልድ “የአገሪቱ መሠረትዊ ችግር ምንድን
ነው?”ብሎ ላነሣው ጥያቄ ሁለት የተለያዩ ምክንያቶችንና መልሶችን ሰጥቶ በመልሶች ልዩነት ምክንያት ከሁለት መከፈሉ ከፍ
ሲል ተጠቅሷል። በተሰጡት ሁለት መልሶች ዙሪያ የተሰለፉት የፖለቲካ ቡድኖች በለስ ቀንቷቸው የፖለቲካ ሥልጣን ይዘው
ለችግሩ መፍትሔ ይሆናሉ ያሏቸውን መፍትሔዎች በተግባር አውለዋል። ሆኖም ያቀረቧቸው መፍትሔዎች የአገሪቱን ዜጎች
ችግሮች በማቃለል ፈንታ እንዲያውም ሁኔታዎችን እጅግ ወደተወሣሠበ አዘቅት የሚያሠምጥ ሆኗል። “ግን ለምን?” ተብሎ
ቢጠየቅ ችግሮቹ ከመቃለል ይልቅ የተባባሱበት መሠረታዊ ምክንያት፦ ቀለም ቀመሱ ትውልድ የአገሪቱ መሠረታዊ ችግሮች
መነሻ “የመደብ ልዩነትና ብሔራዊ ጭቆና ነው” ሲል የሰጠው መልስ ፍፁም የተሳሳተ በመሆኑ ነው። ማንም መሠረታዊ የሆነ
የአመክንዮ (ሎጂክ) ዕውቀት ያለው ሰው ሊገነዘበው እንደሚችለው፣ ከስሕተት የመነሻ ኃሣብ ላይ ተነስቶ ትክክል የሆነ
መደምደሚያ ላይ መድረስ አይቻልም። ወይም ደግሞ ከውሸት ምክንያት ላይ ተነስቶ እውነተኛ መፍትሔ ላይ መድረስ
አይቻልም። በአብዮቱ መጀመሪያ ጊዜም ሆነ ዛሬ፣ የመደብና የነገድ/ጎሣ ልዩነት የኢትዮጵያ ሕዝብ መሠረታዊ ችግሮች
አልነበሩም ፣ አይደሉምም። ቀለም ቀመሱ ትውልድ ለአገሪቱ ሕዝብ ችግሮች የሰጠው መልስ መለያየት በራሱ፣ ትውልዱ
የአገሩን ታሪክና ነባራዊ ሁኔታዎች በቅጡ ያላወቀ መሆኑን ከማስረዳት ባሻገር፣ የተሰጡት መልሶች ርዕዮተ-ዓለማዊ
አመለካከትን እንጂ፣ የአገሪቱን ነባራዊ ሁኔታዎች መነሻ ያላደረገ መሆኑን ያሣያል። ስለሆነም በሁለቱም ቡድኖች የተሞከሩት
መፍትሔዎች ተሞክረው የተገኘው ውጤት የተፎከረለት “እኩልነት ፣ ፍትህ ፣ ሰላም ፣ ፈጣን ዕድገት ፣ ወዘተርፈ የተጎናፀፈ
ሕዝብ” ሣይሆን በዓለም ዙሪያ ካሉ የምድራችን ኗሪዎች በሙሉ ʻበችጋር ፣ በረሃብ ፣ በሥደት ፣ በድንቁርና ፣ በሰብዓዊ
መብት ረገጣ የሚማቅቅ ፣ እጅግ ኋላቀር ሕዝብ ፣ ወዘተርፈʼ ዜጎች ያሏትን አገር ነው። በእርግጥ የኢትዮጵያን የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚ እና የማኅበራዊ ዕድገት ታሪክ በቅጡ የሚያውቅ ሰው፣ ትናንትም ሆነ
ዛሬ፣ የኢትዮጵያ መሠረታዊ ችግሮች “የመደብ ልዩነትና ብሔራዊ ጭቆና”ያለመሆናቸው ከላይ ተመልክቷል። ስለዚህ የአገሪቱ
ችግሮች የሚፈቱት “ጨቋኝ መደብና ብሔር/ብሔረሰብ” የተባሉትን በመደምሰስና በማጥፋት አይሆንም። ትክክለኛው
የመፍትሔ አቅጣጫ በኢትዮጵያ በሕግ የበላይነት የሚገዛ፣ የግለሰብ ነፃነትና መብት የተረጋገጠበት፣ የግል ኃብት
የተከበረበትና ዋስትና የሚያገኝበት፣ የመንግሥት ሥልጣንና ኃላፊነት በምርጫ ውድድር ከሕዝብ ድምፅ የሚመነጭበት፣
ዲሞክራሲያዊ ሥርዓትና ተቋሞች በመገንባት ነው። ቀለም ቀመሱ ትውልድ ላለፉት 40 ዓመታት እርስ በራሱ የተጠፋፋውና
አሁንም ከመጠፋፋቱ የስሕተት ሂደት ሊላቀቅ ያልቻለው አንዴ የተቀበለውን የማርክሣዊ-ሌኒናዊ-ማዖአዊ ርዕዮተ-ዓለም ልክ
እንደ ኃይማኖት ቀኖና የማይቀየር ዕውነት አድርጎ በመውስዱና ካለፈው የስሕተት ጉዞው ሊማር የማይፈልግ በመሆኑ ነው።
እንደዚያ ባይሆንማ ኖሮ በኢትዮጵያ ዕድገት እንኳን ባይገኝ፣ ቢያንስ የነበረንን ማስጠበቅ ይቻል ነበር። ስለሆነም የዛሬው
ወጣት የተማረ ትውልድ ከእርሱ በፊት የነበረው ቀለም ቀመስ ትውልድ የተጓዘበትን የስሕተት ጎዳና ጠብ እርግፍ አድርጎ
በመተው አዲስ ራዕይ ሠንቆ፣ አዲስ ጎዳና መቀየስ ይጠበቅበታል። ለዚህም ለአገሪቱ ሕዝብ መሠረታዊ ችግሮች መንስኤዎች
ምን እንደሆኑ ከታሪካዊ ዳራ ተነስቶ፣ ሣይንሳዊ በሆነ መንገድ በማጥናት፣ ትክክለኛ ወደሆኑት መፍትሔዎች መድረስ
ይኖርበታል። የችግሮቹ መሠረታዊ ምንጮች ምን እንደሆኑ በትክክል ካልታወቀ፣ ተገቢ መልስ ላይ መድረስ አለመቻሉ ገሃድ
ነው። ምክንያቱም ያለፈውም ቀለም ቀመስ ወጣት አብዮተኛ ትውልድ እርስ በእርሱ ፊትና ጀርባ ከመቆሞ አልፎ ደም
ያቃባው ለመሠረታዊ የአገሪቱ ሕዝብ ችግሮች መንስኤዎች ናቸው የተባሉት ምንጮችና የተሰጡት መፍትሔዎች ስሕተት
በመሆናቸው ነው።
ማንም ንጹሕ ኅሊና እና አስተዋይ ልቦና ያለው ሰው ሊገነዘበው እንደሚችለው፣ ዛሬም ሆነ ትናንት የነገድ/ጎሣም
ሆነ የመደብ ልዩነት የአንድ አገርና ሕዝብ መሠረታዊ ችግሮች ሆነው የሚታዩ አይደሉም። ምክንያቱም ሁለቱም የነባራዊ
ማኅበራዊ ዕድገት ሂደት ውጤቶች በመሆናቸው፤ ከሰዎች ፍላጎት ውጪ በምርት ኃይሎች ዕድገት ሣቢያ የሚፈጠሩ ስለሆኑ፤
“አያስፈልጉም፣ ይወገዱ፣ ይጥፉ” ቢባሉ እንኳን በመፈክር ብዛት በማውገዝና የተወሠነውን “ጠላት” ተብሎ የተፈረጀ የአንድ
አገር የሕዝብ ክፍል በመፍጨፍጨፍ ብቻ በፍፁም ሊወገዱ ስለማይችሉ ነው። ስለሆነም የመደብና የነገድ/ጎሣ ልዩነቶች
የነባራዊ ዕድገት ሂደት ውጤቶች መሆናቸውን አውቆና አምኖ መቀበል ያስፈልጋል። የሚሻለው አማራጭ አንዱ
መደብ/ነገድ/ጎሣ በሌሎች ላይ ጤናማ ያልሆነ ተፅዕኖ እንዳያሣድር ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ማኅበራዊ ግንኙነቶች ተገቢ
ሚዛናቸውን ጠብቀው እንዲጓዙ የሚያስችል ሁሉም ዜጎች መጫዎት ያለባቸውን ድርሻ በሥርዓት እንዲወጡ የሚያደርግ
የመልካም አስተዳደር ሥርዓት በመዘርጋት ነው። በመሆኑም አንዱን የሕዝብ ክፍል የሆነ መደብ/ነገድ/ጎሣ ነጥሎ በማጥፋት
ሊገኝ የሚችል ሰላምና መረጋጋት፣ እንዲሁም ሚዛኑን የጠበቀ ዕድገት ሊመጣ እንደማይችል ግልጽ ሊሆን ይገባል። ከዚህ
አንፃር በሌሎች ተክዶ ራሱንም የካደው የዐማራው ቀለም ቀመስ ትውልድ ላለፉት 40 እና 50 ዓመታት የተጓዘበት የትግል
ጉዞ ለእርሱም ሆነ ለትውልዱ አልፎም ለአገሩ ያልበጀ በመሆኑ፣ ከታሰረበት የድርጅትና ግትር ግራ-ዘመም ርዕዮተ-ዓለም
የቀኖና እሥር ቤት ወጥቶ ወገኑን ከፈጽሞ ጥፋት ሊታደግ ይገባዋል።
ዐማራን ከፈፅሞ ጥፋት እንታደግ!
ፈለገ-አሥራት የተውልዳችን ቃልኪዳን ነው!
ኢትዮጵያን እግዚአብሔር ይጠብቅ!