የእስራኤል አምላክ የኢትዮጵያም አምላክ ነውን?

By TEDDY GIRUM

ክርስትያኖች ስለኢትዮጵያ ሲነሳ ሁሌ እነደ ዳዊት የሚደግሙት አነድ ጥቅስ አለ። “ኢትዮጵያ እጆችዋን ወደ እግዚአብሔር ትዘረጋለች” በርግጥ የእስራኤል አምላክ ለኢትዮጵያም አምላክ ነዉ? መፅሃፍ ቅዱስ ስለኢትዮጵያና ኢትዮጵያዉያን ምን አንደሚል በጥልቀት ለማጥናት ሞከረኩ። ግኝቴ ግን እጅግ አስደንጋጭ ነበር።
(መጽሐፈ ዜና መዋዕል. 14:13)
አሳም ከእርሱም ጋር ያለው ሕዝብ እስከ ጌራራ ድረስ አሳደዱአቸው፤ ኢትዮጵያውያንም ፈጽመው እስኪጠፉ ድረስ ወደቁ፥ በእግዚአብሔርና በሠራዊቱ ፊት ተሰባብረዋልና፤ እጅግም ብዙ ምርኮ ወሰዱ።ከእግዚአብሔርም ዘንድ ታላቅ ድንጋጤ ስለ ወደቀባቸው በጌራራ ዙሪያ የነበሩትን ከተሞች ሁሉ መቱ፤ በከተሞቹም ውስጥ እጅግ ብዝበዛ ነበረና ከተሞቹን ሁሉ በዘበዙ። የከብቶቹንም በረት አፈረሱ፤ እጅግም ብዙ በጎችንና ግመሎችንም ማረኩ፥ ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሱ።
እዚህ ክፍል ላይ እንደምንመለከተው ንጉስ አሳ ኢትዮጵያውያን ማርኮ ግመሎቻቸውንም ሳይቀር በዝብዞ ወደ ኢየሩሳሌም እነደተመለሰ ይተርካል። ጦርነት ጦርነት ነዉ ያኔ አልፏል ምንድነዉ ነጥብህ የሚል አይጠፋም። ነገር ግን ማስተዋል ያለብን በጦርነቱ እግዚአብሔር የእስራኤል እነጂ የኢትዮጵያ ቲፎዞ አልነበረም። ስለዚህ በእግዛብሔርና በሰራዊቱ ፊት የሚለዉ ሃረግ በደንብ ይሰመረብት! ይህን ነጥብ በደነብ የምያፀና ሌላ ጥቅስ ካስፈለገ “ኢትዮጵያውያንና የልብያ ሰዎች እጅግ ብዙ ሰረገሎችና ፈረሰኞች የነበሩአቸው እጅግ ታላቅ ጭፍራ አልነበሩምን? በእግዚአብሔር ስለ ታመንህ በእጅህ አሳልፎ ሰጣቸው፥” 2ዜና16: 8
(ትንቢተ ኢሳይየስ 20 : 4-6)
4፤ እንዲሁ የአሦር ንጉሥ የግብጽንና የኢትዮጵያን ምርኮ፥ ጐበዛዝቱንና ሽማግሌዎቹን፥ ራቁታቸውንና ባዶ እግራቸውን አድርጎ ገላቸውንም ገልጦ፥ ለግብጽ ጕስቍልና ይነዳቸዋል። እነርሱም ከተስፋቸው ከኢትዮጵያ ከትምክሕታቸውም ከግብጽ የተነሣ ይፈራሉ ያፍሩማል፤
(ኢሳይየስ 45 : 14)
14፤ እግዚአብሔርም እንዲህ ይላል። የግብጽ ድካምና የኢትዮጵያ ንግድ ቁመተ ረጅሞችም የሳባ ሰዎች ወደ አንተ ያልፋሉ፤ ለአንተም ይሆናሉ እጆቻቸውም ታስረው ይከተሉሃል፤ በፊትህም ያልፋሉ፥ ለአንተም እየሰገዱ። በእውነት እግዚአብሔር በአንተ አለ፥ ከእርሱም ሌላ አምላክ የለም ብለው ይለምኑሃል።
እንደ ኢሳይየስ የኢትዮጵያን ውድቀት የተመኘ ነብይ የለም። አንዴ ራቁታቸውን ወደ ግብፅ ጉስቁልና ይሰዳቸዋል አለ ከዛ ያ አልበቃ ሲለው ማአራፍ 45 ላይ እጆቻውን ታስረው እንደ ባርያ ይነዳሉ አለ። ይሄ ያንድ የዘረኛ(የፅንፈኛ) ፉከራ ነው ማለት ነው የሚቀለው ወይስ የፈጣሪ ትክክለኛ ትንቢት? ፍርዱን ለእናንተው።
(ትንቢተ ሕዝቅኤል 30 : 4)
፤ ሰይፍ በግብጽ ላይ ይመጣል፥ ሁከትም በኢትዮጵያ ይሆናል፤ የተገደሉትም በግብጽ ውስጥ ይወድቃሉ፥ ብዛትዋንም ይወስዳሉ፥ መሠረትዋም ይፈርሳል። ኢትዮጵያና ፉጥ ሉድም የተደባለቀም ሕዝብ ሁሉ ኩብም ቃል ኪዳንም የገባችው ምድር ልጆች ከእነርሱ ጋር በሰይፍ ይወድቃሉ። እግዚአብሔር እንዲህ ይላል። ግብጽን የሚደግፉ ይወድቃሉ፥ የኃይልዋም ትዕቢት ይወርዳል፤ ከሚግዶል ጀምሮ እስከ ሴዌኔ ድረስ በእርስዋ ውስጥ በሰይፍ ይወድቃሉ፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር።
የኢትዮጵያና የግብፅ ስልጣኔ እጅግ በጣም ጥንታዊ እንደነበር የታሪክ መዛግብት የሚያስረዱት ሃቅ ነው። ሕዝቅኤል ከግብፅ ጋር የነበርን ጠንካራ ግኑኝነት አልወደደውም መሰል የግብፅ ቲፎዞ ሁሉ ገደል ይገባል ብሎ ተነበየ። በዛ ዘመን ግን በስልጣኔም በሃብትም ከብት ጠባቂና ዘላን ከነበሩት አይሁዳውያን አስር እጥፍ የተሻልን ነበርን። ታድያ አቶ ሕዝቅኤል የያዘው ፖለቲካዊ ፕሮፓጋንዳ ነበር ወይስ ትክክለኛ ትንቢት? አሁንም ፍርዱን ለእናንተው።
(ትንቢተ ሶፎንያስ 2 :11)
እግዚአብሔር በእነርሱ ላይ የተፈራ ይሆናል፥ የምድርንም አማልክት ሁሉ ያከሳቸዋል፤ በአሕዛብም ደሴቶች ሁሉ ላይ የሚኖሩ ሰዎች ሁሉ በስፍራቸው ሆነው ለእርሱ ይሰግዳሉ። እናንተም ኢትዮጵያውያን ደግሞ፥ በሰይፌ ትገደላላችሁ።
አሁንም ቅድም እንደገልፅኩት ኢትዮጵያና እስራኤል ጠላቶች ነበሩ አይደለም ትልቁ ቁም ነገር። ሶፎንያስ በሰይፌ ትገደላላችሁ አለ እንጂ ሰይፋችን ኢትዮጵያን ያጠፋል አላለም። ስለዚህ አስተውሉ፣ ጥሉ በእስራኤል አምላክና በኢትዮጵያውን መካከል ነው ማለት ነው። እስካሁን ያልኩት ባይዋጥልህም፣ ልጆችህን ኢሳይየስ፣ ሶፎንያስ፣ ሕዝቅኤል ብለህ መሰየም ትንሽ ቅር ይበልህ 🙂
(ኦሪት ዘኍልቍ12፥1 )
ሙሴም ኢትዮጵያይቱን አግብቶአልና ባገባት በኢትዮጵያይቱ ምክንያት ማርያምና አሮን በእርሱ ላይ ተናገሩ።
ሙሴ ኢትዮጵያዋዊ ማግባቱ ለምን ማርያምና አሮንን አስቆጣ? ኢትዮጵያውያን እንደ ኩሽ ዘር ነበር በእስራኤላውያን የሚቆጠሩት ስለዚህ አንድ አይሁዳዊ ኢትዮጵያዊን ማግባቱ ተቀባይነት ያለው ነገር አይደለም። ምክናያቱ ዘረኝነት አይደለም የሚል ካለ፣ እስቲ ይሄን ጥቅስ እንመልከት፣ ትንቢተ ኤርምያስ 13፥23 “በውኑ ኢትዮጵያዊ መልኩን ወይስ ነብር ዝንጕርጕርነትን ይለውጥ ዘንድ ይችላልን? በዚያን ጊዜ ክፋትን የለመዳችሁ እናንተ ደግሞ በጎ ለማድረግ ትችላላችሁ።” አያችሁ ልጅ ኤርምያስ ጥቁረነታችንን መለወጥ ማንችል መሆኑን ሲያሳስበን ፣ ከዚ በላይ አይኑን ያፈጠጠ ዘረኝነት አለ? አስተወሉ ጉማሬ ዝንጕርጕርነቱን ማለት ሲችል ኢትዮጵያዊ ዝንጕርጕርነቱን አለ።
ከዚህ ሁሉ ድብደባ ብህዋላ ‘ኢትዮጵያ እጆችዋን ወደ እግዚአብሔር ትዘረጋለች’ ብተልኝ መልሴ ወዳ አይደለም ነው። ከዛ ምን ጠቀማት ብለህ ጠይቀኝ
(መዝሙረ ዳዊት 74:14)
አንተም የዘንዶውን ራሶች ቀጠቀጥህ፤ ለኢትዮጵያ ሰዎችም ምግባቸውን ሰጠሃቸው።
የእስራኤል አምላክ ልክ ቢሆን ኖሮ ዳዊት እንዳለው በርሃብ ሳይሆን በጥጋብ እንታወቅ ነበር። ከተኛህበት ንቃ! የጃጀ ፅረ-ኢትዮጵያ የእስራኤል ጋዜጣ ማንበብ አቁም!

Nubian Pyramids
የተጠቀምኩት ምስል ላይ ያሉት ፒራሚዶች የግብፅ ፒራምዶች እንዳይምስሉህ። በኢትዮጵያውያን የተሰሩ ናቸው። በጥንታዊቷ ኑቢያ ከታማ አሁን በናይል ወንዝ አቅራብያ በሱዳን ውስጥ እንገኛቸዋለን። መቼም ኢትዮጵያ ስል ያሁኑን ጠባብ የኢትዮጵያ ካርታ እንዳማታስብ ተስፋ አደርጋለሁ ። ኑቢያ አሁን የሱዳን ግዛት ወስጥ ብትሆንም፣ ያአክሱማዊት ሥረወ-መንግስት ስታረቴጂካዊ የንግድ ከትማ እንደንበረች ማስታወስ ግድ ይላል። ፒራሚዶቹ የተሰሩት ከክርስቶስ ልደት በፊት በ 2600 አመተ ዓለም ነው።