Gondaronline.com

አቤቱ የሆነብንን አስብ- ሀገር ስለተነፈጋቸው ባላገሮች እንማልዳለን!

By Muluken Tesfaw
=================================================
Click to view video.

ለኔ እስከሚገባኝ አማራነትም ባላገር መሆንም ወንጀል አይደለም፡፡ የፍትህ ያለህ እያሉ ይጮሃሉ- ባላገሮቹ፡፡
ባላገር= ባለ ሀገር የቁም ትርጉሙ ‹‹የሀገር ባለቤት፣ ባለንብረት፣ ወይም ሀገር ያለው›› ማለት ሊሆን ይችላል፡፡ በሌላ በኩል ባላገር በእርሻ እና በከበት እርባታ የሚተዳደር ገጠሬ ህዝብንም ይወክላል፡፡
አሁን ስለ ባላገር አንድምታ የመፈላሰፍ ጊዜውም ፍላጎቱም የለኝም፡፡ የኔ ጭንቅ በስም ‹ባለ ሀገር› ሆነው አገር የተነፈጋቸውን ባላገሮች ችግር ነው፡፡
በአለፉት 20 አመታት ብዙ ባላገሮች ‹አገር አልባ› ሆነዋል፡፡ አንዳንዴ አንድ ችግር ወዲያዉኑ እንደተከሰተ በየቦታው ‹ዋይ ዋይ› ከተባ በኋላ ይረሳሉ፡፡ አሊያ ደግሞ ችግሩ እንደ እግር እሳት የሚያንገበግባቸው ‹አገር አልባዎቹ ባላገሮች› ብቻ ይሆናሉ፡፡
እነዚህ ባላገሮች ለዘመናት በተለያየ የሀገሪቱ ክፍሎች ተባረዋል፡፡ እንደ እንስሳም ዝቅ ተደርገው ተቆጥረዋል፡፡ በገደል ተጥለዋል፡፡ ሀብት ንብረታቸው ወድሟል፣ ተዝርፏልም፡፡
ይህ እንደ ችግር እስከ መቼ እንደሚቀጥል አይታዎቅም፡፡ ምናልባትም ባላገሮች በሙሉ እስኪያልቁ ሊሆን ይችላል፡፡ ይህ ደግሞ የወላድ ማህጽን እስካልመከነ ድረስ የሚሆን አይደለም፡፡ ሰሞኑን በጋምቤላና በከፋ አካባቢዎች የከፋ (እጅግ አሳዛኝ) መፈናቀል እየደረሰባቸው ነው፡፡ የሚከተለውን ቪዲዮ ተመልከቱና ስለሚፈናቀሉ ሰዎች ማልዱ!!
አቤቱ የሆነብንን አስብ!!

Exit mobile version