ተጠናቀቀ
ተው በለው ተው በለው
ቴሬ ጠረፍ ሽፈራው
ከልብ አስደስተሽኛል እህቴ ይሄ ነው የኢትዮጵያዊነት
እንዴት ባሳደገዉ ባጎረሰው ወገን
ህሊናስ ይፈቅዳል ብረት ለመደገን
ያበቀለህ ምድር ህዝቧም ጨዋ ናቸዉ
እጆችህ ጭካኔን ማን አስተማራቸዉ
ከወንድሜ ፊት ላይ አይቼዉ እግርህን
እንዳላምን አረከኝ ከሰው መፈጠርህን
የዛሬን ተዉእና በል የነገን አልም
ታዝዤ ነዉ ማለት ከፍርድ አያድንም
ለህሊናህ ታዘዝ ባክህ እወቅበት
ያንተም ቀኑ ሲመሽ መልስ እንዳታጣበት
መንገድ ላይ የጣልካት ልጄን ብላ ወታ
እስኪ እናቴ ብትሆን ብለህ አስብ ላፍታ
ጠላት ብታደርግኝ በልተን በአንድ ሞሰብ
ከብዶኛል ስራህን ለደቂቃ ማሰብ
ቸር አውለኝ ብለህ የምትማፀነው
ጌታ አይቆጣም ወይ ወንድምክን ስትገድለው
የማትፈቅደዉን እንዲደርስ አንተ ላይ
በሰው አታድርገው ይቆጣሃል ከላይ
ምትለምንልህን እንዲሰጥህ እድሜ
እህትክን ገደልካት ምን ነካህ ወንድሜ
በወገኖችህ ደም ታጥበከዉ እጅህን
እንዴት ነዉ ሚሰማዉ ፈጣሪስ ፀሎትህን
ጨክነህ ከሳብከዉ የብረትክን ላንቃ
ከሰዉ መፈጠርክን ዘንግተሃል በቃ
ከ ሄኖክ ነጋሽ